2016-01-08 15:18:00

በካናዳና በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ለሶሪያ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ኤጳርቅና ቅዋሜ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የሶሪያ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አዲስ ሐዋርያዊ ኤጳርቅና እንዳቆሙ የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።

እስካሁን ድረስ በካናዳ ለሚኖሩት የሶሪያ ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ዋና ሐዋርያዊ መንበር በካናዳ ኵይበክ ሆኖ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ቅድስት እመቤተ የሶሪያ ሥርዓት በሚከተለው ኤጳርቅና ሐዋርያዊ መሥተዳድር ሥር ሲመራ መቆየቱ የቅድስት መንበር መግለጫ በማብራራት፣ ቅዱስ አባታችን በገዛ እራሱ በሐዋርያዊ ኤጳርቅና ሥር እንዲተዳደር ውሳኔ በማስተላለፍ በሊባኖስ ለሚገኘው የቻርፈት ዘረአ ክህነት ትምህርት ቤት አለቃ በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙትን እ.ኤ.አ. የካቲት 21 ቀን 1969 ዓ.ም. በበይሩት የተወለዱ አባ አንቶኒዮ ናሲፍ የኤጳርቅናው ሐዋርያዊ መሥተናብር እንዲሆኑ መሰየማቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

አባ ናሲፍ እ.ኤ.አ. በ 1992 ዓ.ም. ማዕርገ ክህነት የተቀበሉት በቻርፈት የሶሪያ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ቤት ዋና አስተዳዳሪና ምክትል ቆሞስ በመሆንም እንዳገለገሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ጠቁሞ ፈረንሳይኛ ኢንግሊዝኛና ጣልያንኛ ቋንቋዎችን ጠንቅቀው የሚያውቁ መሆናቸውም አስታወቅ።








All the contents on this site are copyrighted ©.