2016-01-08 13:31:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ:"በውይይት ብቻ ነው አለመቻቻልን ጥልንና ልዩነትን የምናስወግደው"


በትላንትናው ዕለት ማለትም እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በጥር 7.2016 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳጳስ ፍራንቸስኮስ በቪድዮ መልዕክታቸው እንደገለፁት “በሓይማኖት ተቋማት መካከል የሚደረግ ማንኛውም  ግልጽ ውይይት ሰላምንና ፍትህን ለማሰገኘት ከፍተኛ ሚና ይጫወታል” ብለዋል።

በማስከተልም በዝህ በያዝነው የጥር ወር የፀሎታቸው ትኩረት የምሆነው በሓይማኖት ተቋማት መካከል ሰላምን ለፍጠር  ቀጣይነት ያለው ገልፅ ውይይት ማደርግ እንድችሉ ፈጣሪ እንዲረዳቸው በምሆኑ ሌሎችም በፀሎት እንዲተባበሯቸው አደራ ብለዋል። ባስተላለፉት የቪድዮ ምልዕክታቸው ላይ ከእርሳቸው በተጨማሪ የአይሁድ፣ የሙስሊም እና የቡዳዐ እመንት ተከታይ ተወካዮች እናዳሳሰቡት ሁልም እንደ ምያምኑት አምልክና እንደ እምነታቸው አስተምሮ በፍቅር እና በመተባበር መኖር እንዳለባቸው አሳስበዋል ሲል አሌሳንድሮ ጅዞቲ ዘግቧል።

“በአብዛኛው በዓለማችን የሚኖሩ የሰው ልጆች የተለያየ እምነት ያላቸው በመሆኑ ልዩነታቸውን ለመፍታትና አብሮ በሰላም ለመኖር መወያየት ግድ ይላል ያሉት ቅ.ር.ሊ ጳጳስ ፍራንቸስኮስ በተለይም ደግሞ ጦረነትና ጥል በእግዚአብሔር ስም የተከናወነ ባለበት ዓለማችን ሰላምን እና ፍቅር ለማስፈን ሁላችንም እንደየ እምነታችን ስረዓት እና ወግ ፀሎት ልናደግ ያስፈልጋል ብለዋል።

በመቀጠልም “በውይይት ቢቻ ነው አለመቻቻልን፣ ጥልንና ልዩነትን የምናስወግደው” ካሉ ቡኋላ በሃይማኖት ተቋማት መካከል የሚደረገው ውይይት ብቻ ነው ለዓለማችን ዘላቂ መፍትሄና ሠላም የሚያስገኘው ብለው በዚህ በሓይማንት ተቋም መካከል ለሰላም እና ለፍቅር በሚደረገው ውይይት መታቅፍ ላልፈለጉ ወገኖችን ከማግለል ይልቅ ያለማቋረጥ ልንፀልይላቸው ይገባል በለዋል።

በመጨረሻም በዚህ በያዝነው የጥር ወር የአይማንት ተቋማት በሰላምና በአንደንት መኖር እንድችሉ እግዚአብሔር ፀጋዉን እንድልክልን በምናደረግው ፀሎት እናንተም ሁላችሁም ከእኛ ጋር እንደምትፀልዩ እተማመናለው ካሉ ቡኋላ በተለያየ መልክ እግዚአብሔርን ላምግኘት በሚደርግ ሙከራ በምሳሌንት ሲጠቅሱም አግኖስቲክ ማለትም ከሕይወት ቡኋላ ሌላ ሕይወትና የአምላክ መኖር ማወቅ አይቻልም ብሎ የሚያምኑ፣ ሌሎች ደግሞ እግዚአብሔር የለም ብለው የሚያምኑም ቢኖሩም እውነታው ግን አሉ ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮስ በዚህ ብዙ የተለያየ ሓይማኖት ባለበትና ሓይማኖት የሌለው ሰው በሚገኝበት አላማችን እዉነታው ግን አንድና አንድ ቢቻ ነው እርሱም ሁላችንም የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን ነው ብለው ንግግራቸውን አጠቃልለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.