2016-01-08 15:26:00

ላምፐዱዛ፦ ሰብአዊ ፍጡር የአቅርቦት ምርት አይደለም


በኢጣሊያ ላምፐዱዛ በሚገኘው የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙት በብዛት ከኤርትራ የተሰደዱ ዜጎች የሚገኙባቸው በጠቅላላ 200 ስደተኞች የኤውሮጳ ኅብረት የሚጠይቀው ስደተኛው በገባበተ አገር አሻራ ተወስዶበት የጥገኝነት ጥያቄው ያቅርብ የሚለው ሕግ በመቃወም እሻራ አንሰጥም በማለት ለሁለት ቀናት ያካሄዱት አድማ ሰላማዊ መፍትሔ ማግኘቱ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ ሳባቲነሊ ገለጡ።

ስደተኞቹ ምንም’ኳ የአየሩ ሁኔታ ዝናብ አዘል ብርዳማ ቢሆንም ቅሉ ሁለት ቀናት ላምፔዱዛ በሚገኘው ቤተ ክርስቲያን ውጭ ያካሄዱት አድማ መፍትሔ እንዲያገኝ የደሴቲቱ ከንቲባ ጁዚይ ኒኮሊኒ ከሚመለከታቸው የኢጣሊያ መንግሥት አካላት ጋር በመወያየት ሁኔታው እንዲረጋጋ ያደረጉ ሲሆን፣ ስደተኞቹ በነዋሪው ሕዝብና በቆሞስ አባ ሚሞ ዛምቢቶ ድጋፍ እንደተደረገላቸው ሳባቲነሊ አስታውቀዋል።

አባ ሚሞ ዛምቢቶ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ስለ ሁኔታው በማስደገፍ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ስደተኞቹ ማንነታቸው እንዲለይና አሻራም ለመስጠት አምቢ አላሉም፣ ጥያቄያውቸው ጉዳያችን በሚገባ እንዲጣራና ለሚያቀርቡት የጥገኝነት ጥያቄ ባፋጣኝ ተገቢ መልስ እንዲሰጠው የሚል ነው። ስደተኛው ለማስተዳዳር ብቃት ያለው ሕግና መስተዳድራዊ ደንብ የለም ይኽ ጉዳይ የስደተኛው ሁኔታ እንዲወሳሰብ ከማድረጉም አልፎ የስደተኛው ጉዳይ የሚከታተሉ የትብብርና የድጋፍ ማኅበራት አገልግሎት ጭምር እንዲወሳሰብ እያደረገ ነው ብለዋል።

ስለዚህ የስደተኛው ጥያቄ የዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ የሚመለከተው ሕግ አማካኝነት ተገቢ ምላሽ ካላገኘ በሕገ ወጥ መንገድ ስደተኞች ከቦታ ወደ ቦታ ለሚያዘዋውሩ የወጀል ቡድኖች እጅ አሳልፎ እንደ መስጠት ነው የሚሆነው። ደልቶትና ተመችቶት የሚሰደድ ማንም የለም። በመሆኑም የኤውሮጳ ኅብረት አገሮች ሰብአዊነት ልክ ያለው መልስ የሚሰጥ ደንብና ሕግ ሊኖረው ያስፈልጋል በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.