2016-01-04 15:35:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ የቤተ ክርስቲያን ምኅረት እንደ የእግዚአብሔር ምኅረት ለሁሉም ነው


እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሮማ በሚገኘው ኣቢይ ቅድስተ ማርያም ባዚሊካ በተገባው የምኅረት ዓመት ምክንያት ቅዱስ በር በመክፈት በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ፦ ምኅረት መስተጠት የማያውቅ የፍቅር ሙላት ጨርሶ አላወቀም ማለት ነው በሚል ቅውም ሃሳብ ዙሪያ ስብከት መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፋውስታ ስፐራንዛ ገለጡ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዚያኑ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እ.ኤ.አ. ጥር 1 ቀን ቅድስተ ቅድሳት ማርያም እመ እግዚአብሔር ዓመታዊ በዓል ባከበረችበት ቀን  ሁሉም ማርያም የምኅረት እናት መሆንዋ ተወክፎ ወደ የእግዚአብሔር ታማኝ ፍቅር አለ ምንም ፍርሃት በሙላት ገዛ እራሱ ያስገባ ዘንድ ማርያምን ይመልከት ያሉት ቅዱስ አባታችን፦ ማርያም እንደ ቤተ ክርስቲያን ምኅረትን ለሚሹ ምኅረት የምታበዛ ነች፣ የእግዚአብሔር እናት የምኅረትና የይቅርታ እናታ ነች፣ ሕግም ጥበብን ምህረትን አይገታም።

በጎልጎታ የተጸገወው ምኅህረት ወሰን የለውም። ማንም የዚህ ዓለም ጥበብም ይሁን ከሳሽ ሕግም ምኅረትን ሊገታ እይችልም ምኅረትን የሚገታ ማንምና ምንም ነገርም የለም፣ ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠው ምኅረት ልክ እንደዚያ ኢየሱስ ማርያም እግር ሥር በተገኘችበት መስቀል ላይ ሆኖ የዘረጋው ምኅረት ነው። ሌላ አማራጭ የሌለው ምኅረት ነው።

የከፈትነው ቅዱስ በር ይላሉ ቅዱስ አባታችን፦ የምኅረት በር ነው። ስለዚሁ ሁሉም በዚህ ቅዱስ በር ውስጥ የሚያልፍ በፍቅር ውስጥ በሙላት በመግባት በሰማይ እንዳለው አብ በታማኝነት አለ ምንም ፍርሃት መኃሪ እንዲሆን ተጠርተዋል። በዚህ ጉዞ ማርያም እንደምትሸኘውም የተረጋገጠ ነው።

የእምነት ትውልድ ዓይናቸውን ወደ የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ምስል ላይ በማኖር የእርእሷ አማላጅነትንና አጽናኝነትን ይጸልያል፣ ማርያም በማህፀንዋ መለኰታዊ ምኅረት እርሱም ኢየሱስን የጸነሰች በመሆንዋ የምኅረት እናት ነች። ማርያም ከእኛ ጋር ሆና በዚህ በምድራዊ ጉዞአችን ለብቻችን እትተወንም፣ በተለይ ስንጠራጠርና ስንሰቃይ ከጐናችን ነች።

በመስቀል እግር ሥር ሆና መላውነቱን ለሰጠው ልጅዋ በማየት እግዚአብሔር እንዳፈቀረው ማፍቅር ምን ማለት መሆኑ ትመሰክራለች፣ በዚያች ሰዓት ማለትም ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሳለ ምናልባት ገና ሕፃን እያለ በቃልና በሕይወት ያስተማረቸው የእምነት ክብር አንዱ ልሆን ይችላል፣ አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው (ሉቃ. 23፣ 34) ይላል። በዚያች ሰዓት ማርያም ለሁሉም የምኅረተ እናት ሆነች፣ ማርያም በኢየሱስ አብነትና በጸጋ በደል የሌለውን ንጹሕ ልጅዋን ለሞት ለዳረጉት ሁሉም ይቅር ለማለት በቅታለች።

በኢየሱስ መሥዋዕት (ሞት) የተጸገወው ወደ ሁሉም ሰዎችና ወደ ሁሉም ዘመናት እንዲደርስም መንፈስ ቅዱስ ደቀ መዛሙርትን የምኅረት መሣሪያ ለመሆን አበቃቸው። የምኅረት ኃይል ያንን ቂም በቀልተኝነትና ብቀላን ለሚቀሰቅሰው ትካዜ ፍውስ ነው። ምኅረት መንፈስን ከሞት እሳቤ፣ ሰላምንና እርጋታን ከልብ ከሚነጥቀው ከብቀላ ከቂመኛነት ነጻ በማውጣት ወደ ሐሴት ክፍት ያደርጋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ብቀላና ቂመኝነት ምንኛ አስከፊ መሆኑ በማብራራት ውዳሴ ማርያምን ጠቅሰው፣ ማርያም የጥበብ የጸጋ የቅዱስ ሓሴተ እናት ብለው፣ ያንን የኤፌሶን ጉባኤ ቅድስት የእግዚአብሔር እናት ሲል ከሰጣት የአንቀጸ እምነት ውሳኔ ጋር በማያያዝም እዛው በቅዳሴው ሥነ ሥርዓት ለተገኙት ምእመናን ሁሉ በሙሉ ልብ ሦስቴ ቅድስት የእግዚአብሔር እናት የሚለውን ቃል እንዲደግሙ ጋብዘዋል።

ማርያም አብራ ከእኛ ጋር ሆና እንደምትሸኘን ታምነን በምኅረት ቅዱስ በር ውስጥ እንለፍ፣ ከልጅዋ ኢየሱስ ጋር መገናኘት ያለው ውበት ዳግም ለይቶ ለማወቅና ለመኖር በእርሷ እንሸኝም ዘንድ እንፍቀድ፣ ሕይወታችን ዕለት በዕለት የእግዚአብሔር ፍቅር መሣሪያ እንዲሆን የሚያበቃው ተስፋ ዳግም እንደሚጸግወን ታምነን ልባችንን ለምህረትና ለሓሴት በርግደን እንክፈት።

ቅዱስ አባታችን የለገሱት ስብከት፦ ተስፋ ጸጋና ቅዱስ ሓሴት እህታማቾች ናቸው፣ ማርያም ያ ምኅረት በመስጠት ሕይወትን የሚያድሰው የእግዚአብሔር ፈቃድ እንድንፈጽም በእውነተኛ ሓሴት የሚሞላን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ በመስጠት ታድለናለች በማለት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ስፐራንዛ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.