2015-12-31 11:12:00

የምህረት ዓመት የሚያሳየው እግዚአብሔር ፈጣሪ፣አዳኝ እና መሀሪ መሆኑ ነው።


ቅዱስ አባታችን ር. ሊ. ጳጳስ ፍራንቸስኮስ ያውጁትን የምህረት ዓመት ምክንያት በማድረግ  በዓሉ በሀገራችን በሚገኙ የካቶሊክ አብያተ ክርስትያናት በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል። ይህ የምህረት ዓመት በመቂ ሀገረ ሰብከት ለየት ባለ መልኩ እንደሚከበር የገለፁት ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣  በተልይም ደግሞ “ልባችንን ለሓጥያት እና ለክፋት ዘግተን ለፍቅር እና ለይቅርታ ክፍት በማድረግ፣  በተጨማሪም ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች የተቃረኑ እና የተጋጩ የህብረተሰብ ክፍሎች ካሉ ይህንን የምህረት ዓመት ምክንያት በማድረግ ይቅር እንዲባባሉና ይቅርታን እንዲለማመዱ ቤተ ክርስትያን ጠንክራ ትሰራለች” ብለዋል ስትል ማክዳ ዩሓንስ ለቫቲካን ራድዮ ዘግባለች።

ይህ የምህረት ዓመት የሚያሳየው እግዚአብሔር ፈጣሪ፣አዳኝ እና መሀሪ መሆኑ ስሆን፣ ምዕመኑ ይህን በመረደት በእግዚአብሔር ምህረት እንዲጓዝ፣ እርስ በእርሱ ይቅርታ እንዲደራረግ እና በፍቅር እንድኖር ቤተ ክርስትያን ይህንን የቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮን ሓሳብ ተቀብላ በመተግበር ባለፈው እሁድ ማለትም እ.አ.አ በታህሳስ 27.2015 ይህን የምህረት በር በመቂ ሀገረ ስብከት ካህናት፣ ደናግላን፣ ካታኪስቶች እና ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ የፀሎት እና በንስሓ መንፈስ በይፋ ተከፍቷል ብለዋል።

በዚሁ የመክፈቻ ስነ ስረዓት ወቅት ብፁዕ አባታችን አቡነ አብራሃም እንዳሳሰቡት ክርስትያኖች እንዲፀልዩ እና ምህረት እንዲያደርጉበተለይም ደግሞ ከሌሎች የእምነት ተከታዮችም ጋር በሰላም እንዲኖሩ እና ይቅርታን በተግባር የሚያስተሚሩ እንዲሆን በስርዓተ ቅዳሴ የወንጌል አስተምሮ ላይ ብይፋ በማሳሰብ የምህረት በሩን በታልቅ የፀሎት መንፈስ ጀምረናል ብለዋል።በተጨማሪም በዚህ የጀመርንው የምህረት ዓመት፣ የምህረት በሩን እንዲሁ ለይስሙላ ከፍቶ መዝጋት ቢቻ ሳይሆን በዚህ የምህረት ዓመት ከፍተኛ ትኩረት የምንሰጥባቸው ጉዳዮች በመኖራቸው እና በተለይም ደግሞ በበተሰብ፣ በወጣቶች፣ በአዛውንቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ያዘኑትን በማፅናናት፣ የታመሙትን በመጠይቅ እና በመደገፍ የእግዚአብሔር ምህረት ከምዕመናን እና በምዕመን መካከል በተግባር እንድታይ ከፍተኛ ጥረት የምናደርግበት ወቅት በመሆኑ ይህንንም ለማሳካት እያንዳንዱ የሀገረ ስብከቱ ቁምስናዎች ማዕከል ባደረገ መልኩ ባዘጋጀነው ከአምስት ዓመቱ የሀገረ ስብከታችን የሓዋሪያዊ ሥራ እቅድ ጋር በማዛመድ በርከት ያሉ ተጋባራትን ለማከናወን አቅደናል።

በስተመጨረሻም በዚህ የምህረት ዓመት ሁላችንም ቅዱስ ር.ሊ. ጳጳስ ፍራንቸስኮስ ባስተላለፉት መልዕክት ላይ ተመርኩዘን ምዕመኑ እለታዊ ሕይወቱን ከወንጌል ጋር እንዲያገናኝና የቅዱስ ወንጌልን ሕይወት እንዲኖር፣ ምዕመኑን እንደየ እድመው በመከፋፈል ለማስተማር ከፍተኛ ዝግጅት ተደርጓል ብለው ይህ የምህረት ዓመት የሰጠንን እንድል ተጠቅመን ሰላም ለጎደላቸው ቤተሰቦች እና የማህበረሰብ ክፍሎች ሰላምን እና እርቅን በማምጣት በክርስትያኖች ዘንድ ምህረትን እና ሰላምን በተግባር ለማስተማር ታጥቀን ተነስተናል በማለት ንግግራቸውን አጠቃለዋል።  








All the contents on this site are copyrighted ©.