2015-12-30 16:41:00

ብፁዕ አቡነ ቶሶ፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በ 2015 ዓ.ም.


ጳጳሳዊ የፍትህና ሰላም ጉዳይ ተንከባካቢ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ በመሆን ያገለገሉት በሮማ ክልል የፋኤንዛ ሞዲሊያና ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማሪዮ ቶሶ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አስተምህሮ ምዕዳን መልእክት ባጠቃላይ እ.ኤ.አ. የ 2015 ዓ.ም. የቅዱስ ጴጥሮሳዊ ተከታይነት ሐዋርያዊ አገልግሎት ምን ተመስሎው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ሐዋርያዊ አገልግሎታቸው ማእከል ተፈጥሮና ፍጥረት መንከባከብ እንዲሁም ሰላም የሚልና ይኸንን ሁሉ ከእግዚአብሔር ምኅረት ጋር ያለው ትሥሥር የሚገልጥ መሆኑ አብራርተዋል።

ቅዱስ አባታችን እንደሚሉትም ግደ የለሽነት ስግብግብነት ለእኔ ብቻ ባይነት ዓለማዊነት ለበስ እየሆነ ላምሳያ ጀርባ ሰጥቶ መኖር ልሙድ ሆነዋል፣ ስለዚህ በዚህ ዓይነት በሽታ የተጠቃው ኅብረተሰብ ሰብአዊ መንፈሳዊና ሥነ አዕምሮአዊ ፈውስ ያሻዋል። ስለዚህ አዲስ ሰብአዊ ራእይ እንደሚያስፈልግ ያስገነዝባሉ። ሕንጸት የሰው ልጅ ልብ ማእከል ካላደረገ ዓመጽ ግድ የለሽነት የመሳሰሉት የኅብረተሰብ እክሎች ለማስወገድ እጅግ አስቸጋሪ ይሆናል፣ ወንድማማችነት እኩልነት ነጻነት ለጥቂት ብቻ ሳይሆን ለሁሉም በማረጋገጥ ሰብአዊነትና ምኅዳርን መፈወስ ይቻላል። የተፈወሰ ሰው የሚኖርባት ዓለም ፍትህ  ሰላም ይነግስባታል፣ ሰላም የሁሉም ጥረት የሚጠይቅ እንጂ የአንድ ሰው ብቻ ሊሆን አይችልም፣ ቅዱስ አባታችን የሚያስተላልፉት መልእክትም እርሱ ነው።

በዚህ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባወጁት ልዩ የምህረት ዓመት የእግዚአብሔር ምሕረት ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር የምንቀበለው ምሕረት እርስ በእርሳችን በምንሰጣጠው ምሕረት የሚያልፍ መሆኑ የሚያስገነዝብ ነው። የእግዚአብሔርን ምህረት ያጣጠመ ምሕረት ሊሰጥና ሊቀበል ዕለት በዕለት ምሕረት ለመኖር የሚችል ይሆናል፣ ምሕረት የማይሰጥ ከእግዚአብሔር ምሕረት እንደ ተሰጠው የሚጠራጠርና እምነቱ የሌለው ነው። የእግዚአብሔር ምሕረት ለሰው፣ የሰው ልጅ የእግዚአብሔር ልጅ የመሆን ክብር የሚያረጋግጥ ነው።

ሰላም ፍጥረትንና ተፈጥሮን መንከባከብ ተያይዘው የሚሄዱ እሴቶች ናቸው” የወደመ ቤት የሰላም ማደሪያ ሊሆን አይችልም፣ በመሆኑም ተፈጥሮን ለመንከባከብ የምናደርገው ጥረት ሰላም የሚገነባ ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ይኸንን በተለያየ መልኩ በማስተማር በቤተ ክርስቲያን አምካኝነት ለፖለቲካው ዓለም ለዓለም አቀፍ ፖለቲካ ያሳስባሉ በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።  








All the contents on this site are copyrighted ©.