2015-12-29 10:47:00

በዚህ የምህረት ዓመት “እርስ በእርሳችን ልንዋደድ ይገባል... መዋደድ ታላቅ መንፈሳዊ በረክትንም ያስገኛ"


ቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንችስኮስ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ቅዱስ የምህረት ዓመት ማወጃቸው የሚታወቅ ሲሆን ይህንን እወጃ ተከትሎ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በልዩ ልዩ ሰነ ስረዓቶች በዓሉን እያከበረች መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ይህንን በዓል አስመልክቶ የእንድብር ሀገረ ሰብከት ጳጳስ አቡነ ሙሴ እንዳሳሰቡት በዚህ የምህረት ዓመት “እርስ በእርሳችን ልንዋደድ ይገባል ምክንያቱም እርስ በርሳችን መዋደድ ታላቅ መንፈሳዊ በረክትን ከማስገኘቱም ባሻገር በምድራዊ ሕይወታችን እንድናድግም ጭምር ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርጋል” ብለዋል ስትል ማክዳ ዮሓንስ ዘግባለች።

 

ቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስክ ባወጁት የምህረት ዓመት የሰው ልጅ ከፍተኛ የሆነ መንፈሳዊ ለውጥ ያመጣል በሚል አስተሳሰብ ሲሆን በእግዚአብሔር የተፈጥረና በክብር መኖር ይገባው የነበረው የሰው ልጅ ከዚህ ታልቅ ክብር በሓጥያቱ ምክንያት ከእግዚአብሔር ርቆ የነበረ ሲሆን እግዚአብሔር ግን ሓጥያቱን ሳይቆጥር በልጁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ይቅር በማለቱ የእግዚአብሔርን የምህረት ፊት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አይተናል ማለት እንችላለን በለዋል ብፁዕ አቡነ ሙሴ ወልደግዮርጊስ።

ይህ የእግዚአንሔር ምህረትና ደግነት በፍፁም ልንረሳ አይገባም ያሉት ብፁዕ አባታችን አቡነ ሙሴ እኛ ክርስትያኖች ይህንን የእግዚአብሔርን ምሀረት በየዘመኑ ልናስታውስ ይገባናል ብለው በተለይም ደግሞ ለእኛ ኢትዮጵያውያን የምህረት ዓመትን በብዙ መልኩ ለምሳሌም በቀን አቆጣጠር “ዓመተ ምህረት” እያልን የምናስታውስ በመሆናችን ይህ የምህረት ዓመት ከባህላችን ጋር የተያያዘ በመሆኑ በታላቅ ደስታ በመቀበልና ር.ሊ.ጳጳስ የህንን የምህረት ዓመት ብለው ለመላው ዓለም በማወጃቸው እኛም የዚህ መንፈሳዊ ጉዞ ተካፋይ በመሆን በዓሉን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ለማክበር ተዘጋጅተናል ብለዋል።

እንደሚታወሰው ር.ል.ጳጳስ ፍራንችስኮስ እ.አ.አ በታህሳስ 13 የሮማ ካቴድራል የሆነውን የቅዱስ ዩሓንስ ላቴራኖን በር በመክፈት፣ በዓለም ሁሉ የሚገኙ ካቴድራሎች በራቸውን እንዲከፍቱ አደራ ባሉት መሰረት እኛም በሀገረ ስብከታችን በእንድብር የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን በማደረግ፣ በተልይም ደግሞ ቅዱስ አባታችን የምህረት አመትን በማስመልከት የስተላለፉትን መልዕክት በመተርጎም፣ ለህዝቡ በበራሪ ወረቀት መልክ እንዲደርስና በተጨማሪም የተለያዩ መልዕክቶችን የያዙ ትሸርቶችን በማሳተም፣ ለምዕመናን ቀድሞ እንዲደርሱ በማድረግ በእንድብር በሚገኘው የቅዱስ አንጦንዮስን ካቴድራል የምህረት በር ብታልቅ ድምቀት ከተለያዩ ቦታ በመጡ ምዕመናን በተገኙበት በድመቀት የምህረት ብሩ ተከፍቷል ብለዋል ብፁዕ አቡነ ሙሴ።

በዚህ ለአንድ ዓመት ተከፍቶ የሚቆየው የምህረት በር ምዕመናኖች በመግባት እና በመውጣት የእግዚአብሔርን ምህረት ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በተለይም የምሀረት እናት የሆነችውን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በመማፀን የእግዚአብሔርን ምህረት እንዲያገኙ ለምዕመናን እያስተማርን እና እያሳሰብን ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ይህንን ታላቅ እድል ለመጠቀም በተለያዩ ቦታ የሚገኙ ምህመናን ወደ ቤተ ክርስትያናችን ንግደትን በማድረግ የእግዚአብሔርን የምህረት እና ፀጋ እንዲያገኙ በማሳሰብ እግዚአብሔር ለኛ ምህረትን እደምያደርግልን ሁሉ እኛም ደግሞ እርስ በእርሳችን ይቅር መባባል ይኖርብናል በማለት ንግግራቸውን ደምድመዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.