2015-12-24 10:15:00

የሰማይ አባታችው መሀሪ እንደ ሆነ እናንተም መሀሪ ሁኑ::


እ.አ.አ. በታህሳስ 8. 2015 ቅ.ር.ሊ. ጳጳስ ፍራንቸስኮ የምህረት ዓመት ማወጃቸው የሚታወቅ ሲሆን ይህንን መሰርት በማድረግ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በልዮ ልዩ ሰነ ስረአቶች ይህንን የምረት ዓመት እያከበርች ትገኛለች።

ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ኮምንኬሽን ቢሮ ማክዳ ዩሓንስ እንደዘገበችው ይህ የምህረት ዓመት በተለያዩ የኢትዮጵያ የካቶሊክ አብያተ ክርስትያናት  እየተከበረ ሲሆን የጅማ ቦንጋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ገብረመድህን እንደ ገለፁት ይህ የምሕረት ዓምት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ  በጣም ወቅታዊ በሆነ ጊዜ የተሰየም ነው ካሉ ቡኋላ ይህ የምሕረት ዓምት በሀገረ ስብከታቸው በተለዩ ዝግጅቶች እንደሚከበርና በእሁድ ታህሳስ 17.2008 በልደታ ማርያም ቤተ ክርስትያን በይፋ እንደሚከፈት ገልፀዋል።

በዋነኝነትም የሚከበረው ርዕሰ ሊቃን ጳጳስ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ መርህ ቃል አድርገው የሰጡንን “የሰማይ አባታችው መሀሪ እንደ ሆነ እናንተም መሀሪ ሁኑ” የሚለዉን የወንጌል ቃል በመተግበር ስሆን በተለይም ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች ከቤተ ክርስትያን የራቁትን ምዕመንናንን መሀክል ያደረገ እንቅስቃሴዎች እንድሚደርጉ እና ቅዱስ ወደ ሆኑ ቦታዎች በተለይም ደግሞ በሀግረ ሰብከታቸው ወደሚገኝው ለእምነታቸው ብለው ህይወታቸውን አሳልፈው ወደሰጡት የቀድሞ የሰማዕታት የቀብር ቅዱስ ስፍራ በሚደርግ የምዕመናን ንግደት እንደ ሚከበር ገልፀዋል።

በማስከተለም ይህንን የምህረት በር በይፋ በሀገረ ሰብከታቸው በሚቀጠለው እሁድ ሲከፈት ሁላችንም ሓጥያተኞች መሆናችንን እያስታወስን እና ለንስሓ ልባችንን በማዘጋጀት ሓዋሪያው ጳውሎስ “ሁሉም ሓጥያት ሰርተዋል የእግዢአብሔር ከብርም ጎድሎዋቸዋል” እንዳለው ሁሉም ሥጋ ለባሽ ደካማ መሆኑን በገንዘብ በምህረት ከተሞላው አምላክ ጋር በሚስጢረ ንስሓ በመታርቅ እና በስራዓተ አምልኮም በመሳተፍ እምነቱን በማጠንከር እንድያከብረው ለሀገረ ስብከታችን ምዕመናን ጥሪ እናቀርባለን እናስተምራለንም ብለዋል.።

በተለይም አሉ ብፁዕ አብታችን በዚህ የምህረት አመት በዋነኝነት ለሦስት ጉዳዮች ትኩረት እንሰጣለን ካሉ ቡኋላ በመጀመሪያ ቅድምያ የምንሰጠው ጉዳይ የክርስቶስን በሉቃስ ወንጌል በምዕራፍ 15፣ 11-32 የተጠቀሰውን የጠፋን ልጅ ታሪክ እያስታወስን ከቤተ ክርስትያን በተለያዩ ምክንያቶች የራቁትን ወጣቶች ለመሰብሰብ ከፍተኛ ሓዋሪያዊ ሥራ የምናከናውንበት ጊዜ ነው ካሉ ቡኋል በሀገረ ሰብከታችን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወጣት ስላልን ወጣቱን በሚስጢረ ንስሓ እንዲካፈል እና እምነቱንም በማዳበር ሌሎችንም በፍቅር ወደ ቤት ክርስትያን መሳብ እንድችል ለማስተማር ሓዋሪያዊ ሥራዎች ታቅደዋል።

በማስከተልም የቅዱስ ቪንሰንትንና የእማሆይ ትሬዛን አራያ በመከተል ለአቅመ ደካሞችና ለድኾች ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ድኾችን በመርዳት ክርስቶስን ማግኘት እንደሚቻል ስላስተማሩን ማንኛውንም የተቸገር ሰው በምንችለው መልኩ እንድንረዳና እንድናግዝ መንፈሳዊ ጥሪ የሚቀርብበት ወቅት ነው።

በመጨረሻም በዚህ የምህረት ዓመት ሁሉም ክርስትያኖች በመቻቻል እና ልዩነታቸውን በሰለጠነ መልኩ አክራሪነትን ባስወገድ በውይይት እንዲፈቱ የምናሳስብበት ወቅት ነው ካሉ ቡኋል ምዕመናን መንፈሳዊ ንግደትን በተለይም በጅማ ቦንጋ ሀገር ስብከት ወደ ሚገኘውን ከሦስት መቶ በላይ ለእምነታቸው ሲሉ የተሰው ሰማዕት የቀብር ቦታ ንግደትን በማድረግ እምነታቸውን እንድያጠነክሩ የምናስተምርበት ቅዱስ የምህረት ዓመት ነው ሲሉ ንግግራቸውን ደምድመዋል ስትል ማክዳ ዩሓንስ ዘግባለች።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.