2015-12-24 09:17:00

እግዚአብሔር ይህንን የምህረት በር ስልከፈተልን እንድሉን ልንጠቀም ይገባ


እ.አ.አ. በታህሳስ 8. 2015 ቅ.ር.ሊ. ጳጳስ ፍራንቸስኮ የምህረት ዓመት ማወጃቸው የሚታወቅ ሲሆን ይህንን መሰርት በማድረግ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በልዮ ልዩ ሰነ ስረአቶች ይህንን የምረት ዓመት እያከበርች ትገኛለች።

ይህንን መሰርት በማድረግ ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ኮምንኬሽን ቢሮ ማክዳ ዩሓንስ  የባህር ዳር እና የደሴ ሀገረስብከት ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ልሳነ ክርስቶስን አነጋግራ እንደዘገበችው፣ በዚህ የምህረት ዓመት  አሉ ብፁዕ አባታችን አቡነ ልሳነ ክርስቶስ፣ “እግዚአብሔር ትልቅ እና መሓሪ አምላክ በመሆኑ ከጥንት ጀምሮ አካሉ እና ሙሽራው በሆነችው በቤተ ክርስትያን አምካይነት ለሰው ልጅ ያለውን የምህረት፣ የእርቅ እና የፍቅር ሓሳብ ለማንፀባረቅ እና ለማስታወስ እንድችል ነው ቅዱስ አባታችን ፍራንችስኮስ ይህንን የምህረት ኢዩበልዩ ዓመት ብለው በማወጃቸው ትልቅ ደስታ ይሰማናል ካሉ ቡኋላ ለኛ ክርስትያኖች እግዚአብሔር አድስ ሕይወት እንድንጀምርና በዓለም ውስጥ እንዳለን ተሳትፎ፣ እንደ እግዚአብሔር አገልጋይ ወይም እንደ ምዕመን የወደቅንባቸው እና የተሳሳትንባቸው ጊዜያት በመኖራቸው ሓዋርያው ጳውሎስ “የሁኋለኛውን ትቼ የፊቴን ለመያዝ ሮጣለው” እንዳለው፣ እኛም የሁኋለኛውን ጥለን ወደ ፊት እድንጓዝ እግዚአብሔር ይህንን የምህረት በር ስልከፈተልን እንድሉን ልንጠቀም ይገባ ብለዋል።

በመቀጠልም አሉ ብፁዕ አባታችን መፃፍ ቅዱሳችን እንድሚያስረዳው አዳም እና ሔዋን ሀጥያት ከሠሩ ቡኋላ ኪሩበል ሰይፍ ይዞ የገነትን በር እደዘጋና ይህም የገንት በር ለብዙ ጊዜ ተዘግቶ እንደቆየ እና በመጨረሻም በጌታችን እየሱስ ክርስቶስ፣ በዩሓንስ ራዕይ ላይ እንደተጠቀስው ይህንን የምህረት በር ለዘላለም ከፍቶታል ብለዋል።

በማከልም እግዚአብሔር በባህሪው የምሕረት አባት መሆኑን በማስረዳት “የሰማይ አባታችሁ መሓሪ እንደ ሆነ እናንተም መሓሪ ሁኑ” እንዳለው ሁሉ የኛ ቅድስና የሚረጋገጠው ደግሞ መሓሪ እና ይቅር ባይ ስንሆን ቢቻ ነው ካሉ ቡኋል ብፁዕ አባታችን አቡነ ለሳነ፣ የህንን ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ የከፈቱልንን የምህረት በር አጋጣሚውን በመተቀም፣ መንፈስ ቅዱስ አሁንም በቤተ ክርስትያን ውስጥ ሥለሚሠራ እያንዳንዳችን እድሉን በመጠቀም ንስሓ መግባት እና በመለወጥ ለሌሎችም በተሰማራንበት የሥራ መስክ ሁሉ ይህንን የምህረት የምስራች ልናውጅ ይገባል ብለዋል።

በመጨረሻም ብፁዕ አባታችን በባህርዳር እና በደሴ ሀገረ ስብከት እ.አ.አ. በታህሳስ 30.2015 እና በማስከተልም በጥር 1.2016 በኢትዮጲያ የቀን አቆጣጠር በታህሳስ 21 እና 22. 2008 የምህረት በር በባህር ዳር ቅ. ኪዳነ ምሀርት ፀሎት ቤት በሀገረ ስብከቱ የምገኙት ካህናት፣ መነኩሳን፣ ደናግል፣ ምዕመናን እና የዩኒቬርሲቲ ተማሪዎች በተገኙበት በሀገረ ስብከት ደረጃ በይፋ የምከፈት ሲሆን ይህ የምከፈተው የምህረት በር ምንም እንኳን በውጫዊ ገፅታው የእግዚአብሔርን የምህረት በር ሙሉ በሙሉ ይሚገልፅ ባይሆንም እኛ ግን እደ ክርስትያን የድህንነት በር የሆነውን ልባችንን በመክፈት ይቅር እንድንባባል የሚጋብዘን በመሆኑ እድሉን በመጠቀም ለራሳችን ምህረትን አግኝተን ለሌሎችም ያንን የምህርት በርከት በማምጣት ለሀገራችን ሰላምን እና ፍቅርን ማስገኘት ይጠበቅብናል ሲሉ ንግግራቸውን ደምድመዋል ስትል ማክዳ ዩሓንስ ዘግባለች።  








All the contents on this site are copyrighted ©.