2015-12-24 09:02:00

ቤተ ክርስትያን እንከን እና ግድፈት ያለባት ብትሆንም እናት ሆና ግን ትቀጥላለች


እ.አ.አ በ20.12.2015 ቅዱስ አባታችን ቅዱስ በጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምእመናን እንደገለፁት “ቤተ ክርስትያን እንከን እና ግድፈት” ያለባት ብትሆንም እናት ሆና ግን ትቀጥላለች ብለዋል።

በበዓለ ገና እግዚአብሔር ሁለንተናውን በልጁ በክርስቶስ አማካይነት ለኛ ሰቶናል ያሉት ቅዱስ አባታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ምሳሌን በመከትል ንፁዕ ልብ ሲኖረን ቢቻ ነው ይህንን  ታልቅ የመዳን ስጦታ ልንረዳው የምንችለው ብለዋል ስትል ሮበርታ ባርቢ ዘግባለች።

የገናን በዓል በሚገባ ለማከበር እንድንችል አሉ ቅዱስነታቸው ድንቅ በሚባሉ የሕይወታችን  የቀን ተቀን እንቅስቃሴ የሚያርፍበት ቦታ ላይ በማተኮርና በማሰብ ሊሆን ይገባል ካሉ ቡኋላ፣ ለሕይወታችን መሳካት እና ለመኖራችን አስተዋፆ እያደርጉ ያሉትን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን በማሰብ፣ የእየሱስ መወለድ እያንዳንዳችንን የእግዚአብሔርን አምሳል እንድንላበስ በማድረጉ ሲሆን በተለይ ደግሞ እየሱስ የባርያን እና የድሀን መልክ ይዞ በመወለዱ እግዚአብሔር ለድኾች ቅርብ እና የነርሱን መልክ ይዞ ወደ ዓለም በመምጣቱ  ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን በማገልገል በተለይም ደግሞ ለድኾችን ትኩረትን በመጠት እግዚአብሔርን ልናገኘው እንችላለን ብለዋል።

በሁለተኛነትም አሉ ቅዱስ አባትችን ታሪክ በሕይወታችን ድንቅ ነገር የሚፈጠርበት የጊዜ መለክያ በመሆኑ ታሪክን በእምነት ዓይን ልንመለከተው ይገባል ካሉ ቡኋላም በታሪክ ውስጥ እየተንፀባረቀ ያለውን በታላላቅ መንግስታት ተፅኖ እየተፈፀመ ያለውን የልተስተካከለ የእኮኖሚ እና የግብይት ሥራዓት በጣም ሊያስፈራን አይገባም ብለው “በገና የሚወለደው ጌታ ታሪክን የሚለውጥ ጌታ ነው ካሉ ቡኋላ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንደ ዘመረችዉ “ገዢዎችን ከዙፋናቸው አዎርዶዎቸዋል ትሑታንን ግን ከፍ ከፍ አድርጎዋቸዋል፣ የተራቡት በበጎ ነገር አጥግቦአቸዋል ሀብታሞችን ግን ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል” በማለት ከሉቃስ ወንጌል በመጥቀስ ምዕመናንን በማበረታታት ይህ የሚንፀባረቀው ኢፍታዊ ድርጊት ተስፋ እናዳያስቆርጣቸው መክረዋል።

በማስከተልም ቤተ ክርስትያን እንደ አንድ የአይማኖት ተቋም ቢቻ መታየት የለባትም ያሉት ቅዱስ አባትችን ምንም እንኳን ግድፈት እና ድክመት ቢታይባትም፣ ልክ እንደ አንድ ግድፈት እና ድክመት እናዳላት እናት ልትታይ ይገባል ካሉ ቡኋላ፣ ቤተ ክርስትያን ተወዳጅ የጌታ ሙሽራ እና  ክርስቶስ በቀጣይነት የሚያነፃት በመሆኗ፣ ቤተ ክርስትያን ቀጣይነት ያለው የእግዚአብሔር ፍቀር መገለጫ መሆኗን መረዳት ያስፈልጋል ብለዋል ቅዱስነታቸው።

በማከልም ቤተ ክርስትያን እንደ እናት ሁልግዜ በሮቿን እና እጆቿን በመክፈት ሁሉንም በእኩልነት ልታስተናግድ እና በታልቅ ፈገግታ ልክ እንደ እናት ሁሉንም ወደ እግዚአብሔር ምህረት ልትጋብዝ ይገባል ብለው የበዓለ ልደት ስጦታ ሊሆን የሚገባዉም ይህ የግዚአብሔር ምህረት ነው በለዋል።

በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን በላቲን ስርዓተ ሊጡርጊያ መሰረት የዕለቱን ማለትም እ.አ.አ የ20.12.2015 በሉቃስ ወንጌል በምዕራፍ 1 ከ ቁጥር 39-45 ያለዉን ማርያም ኤልሳቤጥን የጎበኘችበትን የወንጌል ቃል ስያስተነትኑ “የሁለቱ ሴቶች ግንኙነት አሉ ቅዱስ አባታችን እንዷ ወጣት ሌላዋ ደግሞ የእድሜ ባለፀጋ በተገናኙበት ወቅት የነበረውን ታልቅ ደስታ በማውሳት ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ “ለመሆኑ የጌታየ እናት ወደኔ ትመጣ ዘንድ እኔ ማነኘ?” ብላ እንደመሰከርች ሁሉ ዛሬም እናታችንን ቅድስት ማርያም ወደየበታችን በምንጋብዝበት ወቅት የገና ስጦታ የሆነዉን ክርስቶስን ወደ ቤታችን በማምጣት በታችንን በደታ እና በፍቅር እንድትሞላው ለንጋብዛት ይገባል በለዋል።

ከመላዕከ እግዚአብሔር ፀሎት ቡኋላ ቅዱስ አባታችን በቅዱስ ጴጦሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡት ልጆቻቸው በተለያየ ዓይነት በሽታዎች ለሚሰቃዩ ቤተሰቦችን በደስታ እና በሀዘናችው ጊዜ ሁሉ ከናንተ ጋር አብረን በመሆናችን ተስፋ ባለምቁረጥ የእመነት መንገዳችሁን በታልቅ ትዕግስት እንድትቀጥልሉ አደራ እላለው በማለት ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.