2015-12-23 14:59:00

የአርጀንቲና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት፦ አለ ኢየሱስ በዓለ ልደት ትርጉም አልባ ነው


የጌታችን ኢየሱስ ክርቶስ በዓለ ልደት አለ ኢየሱስ መኖርና ማክበር ትርጉም አልባ ነው፦ የሚል ቀዉም ሃሳብ ማእከል ያደረገ የአርጀንቲና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በበዓለ ልደት ምክንያት ለሁሉም የአርጀንቲና ማኅበር ክርስቲያንና መልካም ፍቃድ ላላቸው ሰዎች መልእክት ማስተላለፋቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በዓለ ልደት ዘእግዚእነ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ የሚጸግወንን ሐሴት ከሌሎች ጋር ተካፍሎ የመኖር በዓል ነው። የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ ለእኛ ለሰዎች ድህነት ነው ያሉት የአርጀንቲና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት፦

ኢየሱስ፦ ለበዓለ ልደት ምክንያት ከሌሎች ጋር የምንሰጣጠው ገጸ በረከት መሆን አለበት

የእግዚአብሔር ምኅረት ለሰው ልጅ ከመጠን በላይ ሰብአዊ በሆነ ለቅርበትና ለርህራሄም አንዲት ቤተሰብን በመምረጥ በታሪክ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ገባ። በመሆኑም የአርጀንቲና ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም ምእመናንና መልካም ፈቃድ ላላቸው ሰዎች ለበዓለ ልደት ምክንያት የምትሰጠው ገጸ በረከት ኢየሱስ ክርቶስን ነው። ኢየሱስ በመካከለችን የመጣው እኛ በተራችን የተቀበልነውን ኢየሱስ ለሌሎች እንድናካፍል ነው። በዚህ መንገድም በእግዚአብሔርና በሰው ልጅ መካከል የጸናው እርቅ እናከብራለን።

በዓለ ልደት የሰው ልጅ የእግዝአብሔር ልጅ የመሆን የላቀው ሰብአዊ ክብሩን ይመሰክራል

በዓለ ልደት የላቀው ሰብአዊ ክብራችን ብስራት ነው። እኛ የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆንና በዚህ መንፈስ ወንድማማቾች መሆናችንን ለመኖር እንድንችል እግዚአብሔር ሰው ሆነ። በተለይ ደግሞ በምኅረትና ይቅር በመባባል መንፈስ ወንድማማቾች መሆናችንን ለመኖር ተጠርተናል፣ ሰው የሚኖረው የለገሰው  መሆን አለበት ማለትም እግዚአብሔር መሆን አለበት፣ የሚኖረን የሰጠነው፣ እግዚአብሔር ያለው ለእኛ የለገሰው ነው። በዚህ ቸልተኝነት ግለኝነት ስግብግብነት በሰፈነበት ዓለም የምኅረት ደሴት እንሆኑ እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎ ይጠቁማል።

ህማምንና በስቃይ ላይ የሚገኙትን አጽናኑ

የአርጀንቲና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ለበዓለ ልደት ምክንያት ያስትላለፉት መልእክት ሲያጠቃልሉ፦ ሁሉም የዚያ በግርግም የተወልደው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተሰብአዊ ጸጋ በእያንዳንዱ ቤተሰብ ይገባ ዘንድ እንዲጸለይ ምዕዳን በማቅረብ፣ ለታመሙት በስቃይ ላይ ለሚገኙት ለቆሰሉት ልባቸው በኃዘን ለተሞላው ለድኾች ለእስረኞች ሁሉ ፍቅር ሐሴትና መጽናናት እናቅርብ እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።   








All the contents on this site are copyrighted ©.