2015-12-16 13:55:00

የዕለት ሮዕቡ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምሮ በቅዱስ አባታችን ፍራንሲስ


ቅዱስ አባታችን ፍራንሲስ በዛሬው ዕለት ማለትም እ.አ.አ በታህሳስ 16.2015 --- በቅዱስ ጴጥሮ አደባብይ ለተሰበሰቡት ምዕመናን እንደገለፁት፣ “ባለፈው ሳምንት በሮማ ቢቻ ስይሆን በመላው ዓለም የተከፈተዉ ቅዱሱ የምሕረት በር የምያመለክተው የካቶሊክ ቤተክርስትያን አለማቀፋዊነቷን እና ሕብረት ያላት ቤተክርስትያን መሆኗን የሚገልፅ ነው ብለዋል።

የዛሬ ሃምሣ ዓመት አሉ ቅዱስ አባታችን፣ በሁለተኛው የቫቲካን ጉባሄ እንደተጠቀሰው፣ ቤተክርስትያን በክርስቶስ የተጠራችው፣ በምድር የክርስቶስ ተወካይ በመሆን፣  የእግዚአብሔር ምህረታዊ ፍቅርን ለሰዎች ሁሉ ለማሳየት እና ለመግለፅ ሲባል ነው ብለዋል። ስለዚህም ሁላችንም በፍቅር፣ በርህራሄ እና ይቀር በመባባል፣ በእግዚአብሔርን ፍቅር ታግዘን ልባችንን በመለወጥ እርቅን እና ሰላምን ልናመጣ ይገባል በለዋል።

በተጨማሪም አሉ ቅዱስ አባታችን ለዚህ ቅዱስ የምሕረት ዓመት በተዘጋጀ ቅዱሱ በር በማለፍ፣ በክርስቶስ ምሕረታዊ ፍቅር ውስጥ ለምግባት ያለንን ጥልቅ ፍላጎት መግለፅ እየሱስ እኔ “የዘላልም ሕይወት በር ነኝ” እናዳለው ሁሉ፣ አሉ ቅዱስ አባታችን፣ እኛም በእውነተኛ መንፈስ ወደ እርሱ በመቅረብ፣ ለባችንን እውነተኛ ለሆነዉ ለእግዚአብሔር እና ለሰዎች ፍቅር መክፈት ይጠበቅብናል ብለዋል።

በተለይም ደግሞ አሉ ቅዱስ አባታች ንግግራቸውን ስያጠቃልሉ፣ በዚህ የምህረት ዓመት ኢዩቤልዩ የእግዚአብሔርን ፀጋ ለምግኘት፣ ሓጥያተኞች መሆናችንን እንድንገነዘብ፣ በምስጢረ ንስሓ በመሳተፍ እና የእግዚአብርን ምሕርት በመቀበል እግዚአብሔር በሚሰጠን ፀጋ ታግዘን ህይወታችንን ውጠታም በሆነ መልኩ እንድንመራ እና ለዓለም ሁል የእርቅ እና የፍቅርን ፀጋ ማምጣት ይጠበቅብናል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.