2015-12-16 16:11:00

ብፁዕ ኣቡነ ቪጋኖ፦ ታማኝነት በኅዳሴ


የቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ኅየንተ የቫቲካን ቴለቪዥን ጣቢያ ዋና አስተዳዳሪ ብፁዕ አቡነ ዳሪዮ ኤድዋርዶ ቪጋኖ ታማኝነት በኅዳሴ፣ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የለውጥ ውሳኔ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት መጽሓፍ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 17 ቀን 2015 ዓ.ም. በቫቲካን ረዲዮ ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳርሽ ለንባብ እንደሚበቃ ሲገለጥ። የመጽሓፉ ደራሲ ብፁዕ አቡነ ቪጋኖ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ቤተ ክርስቲያንን በቀጣይነት ካቶሊካዊ ባህል ለማደስ ያላቸው እቅድ በጅምር ያለው ሂደት ለማንም የተሰወረ አይደለም በዚህ እሳቸው በደረሱት መጽሓፍ ዘንድ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ

ቤተ ክርስቲያን ተመስሎ የሂዳሴው ማእከል፣ ያላቸው የውይይት ጠባይ በእግዚአብሔር ምስጢር ላይ ያላቸው ጽናትና የቤተ ክርስትያን ቅዱስ ባህል መከተል ያለው ክብር ነው ብለው፣ ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ምኅረት ታምና የዚህ ምኅረት መገልገያ መሆንዋ የሚሰጡት ሥልጣናዊ ትምህርት የሚብራራ መጽሓፍ ነው ብለው፣ ከተመረጡበት ዕለት ጀምረው የሰጡት የመጀመሪያ ር.ሊ.ጳጳሳዊ ቃል ስለ ምርጫው የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን የሰጡት ትንታኔ በተለይ ደግሞ የአርጀንቲና የመገናኛ ብዙኃን መግለጫዎች ያካተተ ባጠቃላይ ውይይት ወዳጅ ነቢያዊ ራእያቸው የሚብራራ  ነው፣ ለሕዝብ ቅርብ የመሆን በተለይ ደግሞ ለተናቁት በከተሞቻችንናን በህልውና ጥጋ ጥግ ለሚኖሩት ያላቸው ቅርበት የሚያወሳ ከሳቸው ካህን የመሆን ጥሪ ጋር የተሳሰረ በቅዱስ ጴጥሮሳዊ ተከታይነት ጥሪ ሥር በመተርጎም የሚኖሩት ዕለታዊ ሕይወት የሚያብራራ መጽሓፍ መሆኑ ገልጠው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.