2015-12-12 11:21:00

ኖስትራ አሄታቴ (ያለንበት ዘመን)፣ ከአይሁዳዊያን ጋር ያለንን ግንኙነት እና ልዩነት የሚገልጽ የሁለተኛ የቫቲካን ጉባሄ ሰነድ


በብጹዕ ካርዲናል ኩርት ኮክ በጂህዳ አኩሊኖ እንደተዘጋጀ

የዚህ ጹሁፍ ሃሳብ ባለፉት ሃምሳ ዓመታት ከሁለተኛ የቫቲካን ጉባሄ ቡሃላ በአይሁድ እና በካቶሊክ ማህበረሰብ መካከል ስለተደርጉት ዉይይቶች እና ስለተገኘዉ ፍሬያማ ለዉጥ ለማንሳት በማሰብ ነዉ። በተለይም ደግሞ በዚህ ሰነድ በአራተኛ አንቀጽ የተጠቀሰው ፍሬ ሓሳብ ስለካቶሊክ እና አይሁዳዊያን ግንኙነት የሚገልጽ ቢቻ ሳይሆን ከተለያዩ እመነቶች ጋር ያለንን ግንኙነትንም በጣም እንዲጠናከር ያገዘም ጭምር ነው። መሪ ሃሳቡም ከአይሁድ ማህበረሰብ ጋር ልኖረን ስለሚገባ አድስ መንፈሳዊ አካሄድ የምያስረዳ ነዉ።

በዚህ አንጻር የካቶሊክ ቤተክርስትያን ከአይሁዳዊያን ጋር የምታደርገዉ ግንኙነት ከሌሎች እምነቶች ጋር ለምታደርገዉ ዉይይት እንደ መስፈንጠሪያ ሆኖ ሊይገልግል ስለምችል በጥንቃቄና በትኩረት ልታይ ይገባዋል።

በምደረገዉ መንፍሳዊ የመግባባት ዉይይት ላይ ትኩረት ወይም ልሰመርባቸዉ ይሚገባቸዉ ጉዳዮች፣ ለምሳሌም የራዕይን አስፈላጊነት፤ በብሉይ እና በአዲስ ኪዳን መካከል ያለዉ በፍጹም ልለያይ የማይችል ግንኙት፤ የእየሱስ የዓለም ሁሉ አዳኝ መሆኑን የሚገልጽ እምነት፤ እግዝሓብሄር ለእስራኤል ሕዝብ የገባዉ ቃል ኪዳን የማይሻር መሆኑንና ዓለማቀፋዊ የቤተክርስትያን የወንጌለ ስብክት አገልግሎት ትኩረት ሊሰጥባቸዉ የሚገባቸዉ ጉዳዮች ናቸዉ።

ኖስትራ አሄታቴ (ያለንበት ዘመን)፣ በካቶሊክ እና በአይሁዳዊያን መካከል የጠበቀ ግንኙነት እንዲኖር እና እንዲፈጠር ያስቻለ ሰነድ ቢቻ ሳይሆን እንደ ጠላት የሚፈራረጁ ሁለቱ ማሕበረሰቦች በመቀራረብ እንድሰሩ እና ግጭቶችን በመነጋገርና አግባብ ባለዉ መልኩ መፍታት እንዲችሉ ያስቻለም ጭምር በመሆኑ አስፈላግነቱ በጣመ የጎላ ነዉ። ይህንን መነሻ በማድረግ እ.አ.አ 1974 ዕርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፓዉሎስ ስድስተኛ ከአይሁድ ማህበረሰብ ጋር የምደረዉን ዉይይት በተጠናከረ መልኩ ለማስኬድ በማሰብ ኮሚቴ በማቋቋም ዉይይቱ በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀጥል በማድረጋቸዉ እንደ አብነት ስቆጠሩ፣የሳቸዉን አራዐያ በመከተል ቀጣዮቹ ጳጳሳትም አሁን እሳካሉት ቅዱስ አባታችን ፍራንሲስም የተልዕኮዋቸው አንዱ ሥራ አድርገዉ በተጠናከር መልኩ ሥራዉን አስቀጥለዉ ሰንብተዉአል።

በሌላም በኩል ስታይ አይሁዳዊያን እና ክርስቲያኖች አንዱ አንዱን ልያበለጽግ የሚችል ሀብት ስላላቸው፣ ከሌላዉ እምነት በተሻለ አይሁዳዊያን እና ክርስቲያኖች የምያስተሳስራቸዉ ነገር ስለሚበዛ በተለይም ደግሞ ክርስትና ከአይሁዳዊያን የሚመዘዝ የዘር ግንድ ሰላለው ግንኙነቱ ከለላዉ እምነት በተሻለ የተቆራኘ እና የተሳሰረ ነው። ያለ አይሁዳዊያን ቤተክርስቲያን የደህንነት ታሪኳን የሚገልጸዉን እና ከአይሁድ የሚመዘዘዉን ማንንነቷን ታጣለች ማለት ነዉ።

በአብዛኛዉ ከአይሁድ ጋር የሚደረገዉ ዉይይት ፍሬያማ የሚሆንበት ምክንያት የሁለቱን ሃይማኖቶች ማንነት የሚያገናኝ እና በጥብቅ የምያስተሳስራቸዉ ታሪክ በመኖሩ ምክንያት ጭምር ነው። ሁለቱንም በይበልጥ የምያስተሳስራቸዉ ጉዳይ ቢኖር እየሱስ አይሁዳዊ መሆኑና በአይሁደ ጊዜ መኖሩ ስሆን የሚያለያያቸዉ ደግሞ በእየሱስ አዳኝነት ላይ የሚያነሱት ጥያቄዎች ናቸው።

እየሱስ የዓለም ሁሉ አዳኝና አማላጅ መሆኑን፣ ሓዋርያዉ ጳዉሎስ እንዳስቀመጠዉ የማይለወጥ እና የማይሻር ሀቅ ነዉ። በአንጻሩ ደግሞ አይሁዳዊያን መንፈሳዊ ጸጋን እና በረከትን የምያገኙት በቀጥታ ከእግዝሓብሔር ዘንድ ቢቻ ነዉ። ትልቁ ትኩረት ልሰጠዉ የሚገባዉ ጉዳይ ታድያ አይሁዳዊያን ጌታችን እየሱስ ክርስቶስን ሳያምኑ እንደት ልድኑ ይችላሉ የሚለዉ ስሆን፣ የኖስትራ አሄታቴ (ያለንበት ዘመን)፣  ዶክመንት ስመልስም “ለማብራራት የምያዳግት መለኮታዊ ሚስጢር ነዉ” ብሎ ይደመድማል። 

ቤተክርስትያን ወደ አይሁዳዊያን የምታደርገዉ መንፈሳዊ ተዕልኮ በይዘቱ ቀላል ቢመስልም እዉነታዉ የምያሳየዉ ግን በጣም ጥንቃቄ ልቸረዉ የሚገባው አስቸጋሪ ተልዕኮ እና እሾህ የበዛበት አስቸጋሪ መንገድ መሆኑን ያሳያል ምክንያቱም ከመኖር ህልዉናቸው ጋር የተያያዘ በመሆኑ።

ስለዚህም ቤተክርስትያን ልትረዳዉ የሚገባዉ ነገር ቢኖር በአንድ አምላክ በምያምኑ ወደ አይሁዳዊያን የምደረገዉ መንፈሳዊ ተልዕኮ ከለሎች ክርስትያን ካልሆኑና የራሳቸዉ ፍልስፍና ካላቸዉ እምነቶች ለየት ያለ መሆኑን በመረዳት መረዳት ይጠበቅባታል።

የካቶሊክ ቤተክርስትያን ማንኛውንም አይነት መንፈሳዊ ተልዕኮ ወደ አይሁድ ምድር ለማድረግ አትነሳሳም፣ ነገር ግን ክርስትያኖች ክርስቶስን በሕይዎታቸዉ በአይሁድ ማህበረሰብ ፊት በትህትና እና በጥንቃቄ፣ በተጨማሪም አይሁዳዊያን የእግዚሓብሄርን ቃል እንደምያዉቁ ከግምት ዉስጥ በማስገባት በተግባር እንድመሰክሩ ግን ታበረታታለች።

በመጨረሻም የኖስትራ አሄታቴ ሰነድ የምያጠቃልለዉ ሁለቱም አይማኖቶች በጋራ ያላቸዉን መልካም የሆኑና ለዓለማችን አስፍላጊ የሆኑ እንደ ፍትህ፣ ሰላም እና አንድነትን በማረጋገጥ በዓለም ላይ እርቅንና ሰላምን ላማስፈን መጣር ይኖርባቸዋል፣ መክንያቱም የዓለም ሰላም ልጠናከርና ልረጋገጥ የምችለዉ በሀይማኖቶች መካከል ጥብቅ የሆነ ዉይይት ስደረግ ቢቻ መሆኑም ያስረዳል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.