2015-12-10 16:42:00

“ቤተክርስትያንን የምንቀበለዉ ለክርስቶስ ስንል ነው”።


(ከአባ ራኔሪዮ ካንታላሜሳ አድሪያና ሜሶቲ እንደተጠናከረችዉ)

የሁለተኛ የቫቲካን ጉባሄ ሰነድ ሉሜን ጀንሲዉም ዎይም ባማረኛ በግርድፉ ስትርጎም የሕዝብ ብራሃን እንደ ሚያስረዳዉ “ቤቴክሪስቲያን የክርስቶስ አካል እና ሙሽራ ናት ይላል”። በሓጥያተኞች የተሞላች ቤተክርስቲያንን መቀበል ማለት ክርስቶስ እራሱን መቀበል ማለት ነዉ። ምክንያቱም ክርስቶስ የህዝብ ሁሉ ብርሃን ነው የሚለዉ የሉሜን ጀንሲዉም ሰነድ በሚገባ እንደ ሚያስረዳዉ ክርስቶስ የቤቴክርስቲያን ማዐዘን በመሆኑ ምንም እንኳዋን ቤቴክርስቲያን በብዙ ህጥያተኛ መሪዎች የተሞላች ብትሆንም ቤቴክርስቲያንን የምንቀበለዉ ክርስቶስ ቤቴክርስቲያንን ስለዎደዳ ቢቻ ሳይሆን እኛ ክርስቶስን ስለምንወደዉም ጭምር ሊሆን ይገባል ሲሉ አክለዋል።

ዋናው ጥያቄ ሊሆን የሚገባዉ ”ቤቴክርስቲያን ምንድናት”? የሚለዉ ሳይሆን ”ቤቴክርስቲያን ማናት” ? ­የሚለዉ ነዉ መሆን ያለበት ካሉ ቡሃላ አባ ካንታላሜሳ መጸሓፍ ቅዱሳችን እንደሚያሳየዉ፣ ”ቤቴክርስቲያን እንከን የለለባት የክርስቶስ ሙሽራ ናት…እርሱም በጣም ስለዎደዳት እራሱን አሳልፎ በመስጠት አነጻት” ይለናል ስለዚህ ቤቴክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት ማለት ነዉ ብለዋል።

አባ ካንታላሜሳ የካርዲናል ራዚንገርን ህሳብ በመጥቀስ ሓሳባቸዉን ስያጠናክሩ ቤቴክርስቲያን የክርስቶስ ሙሽራ በመሆኗ የክርስቶስ አካል ተደርጋ ትቆተራለችኦ ስለዚህም ሙሽራ የሚለዉ ቃል ሊፈጥጸም የሚችለዉ ሁለት ስጋ እና ነፍስ ባላቸዉ ዎንድ እና ሴት መካከል በመሆኑ እነሱም አንድ አካለ ሆነዉ በጋቢቻ እንደሚዋአዱ ሁሉ እንዲሁም የክርስቶስን ስጋ የሚመገቡ ሁሉ ከእርሱ ጋር አንድ አካል ይሆናሉ።

 ስለዚህ ያለቤቴክሪስቲያን እና ያለቅዱስ ቁርባን ክርስቶስ በዓለም ዉስጥ ”አካል ” ሊኖረዉ አይችልም። መማከልም ስጠቅሱ አንድ የዎንጌል ሰባኪ “ቤቴክርስቲያን የክርስቶስ አካል እና ሙሽራ መሆኗ፣ ለአንድ ክርስቲያን መንፈውሳዊ ሕይዎት ምን ዓይንት ትርጉም ሊኖረዉ ይችላል”? ብሎ ያስብ ነበር። ሲመልስም “ቤቴክርስቲያን የክርስቶስ የቅርብ አካሉ መሆኗን ካመንኩኝ፣ እኔ እንደምረዳዉ ቤተክርስቲያን እንደ ቤቴክርስቲያኒነቷ በሓሳብ ደርጃ ቢቻ ሳይሆን በተግባር እኔም የክርስቶስ አካል እንድሆን ታደርገኛለች ማለት ነዉ” ሲል ያስረዳል። ስለዚህ እኔ ቢቻየን ሳይሆን የምኖረዉ ክርስቶስም በኔ ይኖራል ማለት ነው። ይህም እውነታ በተቅበለነዉ ጥምቀት እና በየጊዜዉ በምንቀበልዉ ቅዱስ ቁርባን እዉን ይሆናል ማለት ነዉ።

ቅዱስ ቁርባን እያንዳንዳችንን የክርስቶስ አካል ማለትም ቤቴክርስቲያን እንዲኒሆን ያደርገና። ይህም እኛ ሁለት ባህሪ አንደኛዉ የራሳችን የተፈጥሮ ባህሪ ሁለተኛዉ ገግሞ የክርስቶስን ባህሪ በመላበስ አንድ አካል ቢቻ እንድንሆን ያደርገናል። ከሁለት ባሕሪ ወደ አንድ ባሕሪ እንቀየራለን ማለት ነዉ።

ስለዚህም ታላቁን ሚስጢር የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋዉንና ደሙን ስንቀበል የኛ ተፈጥሮአዊ ባሕሪ በክርስቶስ ይሞላል ሓዋሪያዉ ጳዉሎስ እንድሚለዉ “እኔ ሳልሆን የምኖረዉ ክርስቶስ በኔ ይኖራል” ማለት ነዉ።

እኛ የክርስቶስን ሥጋ እና ደም እንደምንቀበል፣ ክርስቶስም ደግሞ የኛን ሥጋ እና ደም ይረከብና የራሱ ያደርጋል። ስለዚህ ሁለንተናችን የራሳችን መሆኑ ይቀርና የክርስቶስ ይሆናል። ክርስቶስ የኛ እኛ ደግሞ የክርስቶስ እንሆናለን። ስለዚ ሁለንተናችን የክርስቶስ ይሆናል ማለት ነዉ።

በጥምቀት የክርስቶስ የሆንን ሁላችን በተለይም ደግሞ ለሱ አገልግሎት የተቀደሱ ሰዎች በሙሉ ከፍተኛ የሆነ አላፊነት አለብን። ይህ የክርስቶስ አካል ያደረገን ታላቅ አላፊነት ደግሞ የክርስቶስ አካል የሆነችዉን ቤቴክርስቲያን እንዳናዋርድ እና እንዳናቆሽሽ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል።

በመጨረሻም ይህንን የተሰጠንን ታላቅ ሓላፊነት በአግባቡ መዎጣት እንድንችል የክርስቶስ እገዛ ስለምያስፈልገን እርእሰ ሊቃነ ፓፓስ አቡነ ፍራንሲስ እንዳሉት “ከክርስቶስ ጋር እለታዊ የሆነ ግንኙነት” ማድረግ አስፈላጊነቱ አያጠራጥርም።

ባጠቃላይ በቤቴክርስቲያን ሚስጢር መሳተፍ ቢቻ የጎላ መንፈሳዊ በረከትን እና ለዉጥ ለኛ ሊያመጣ  አይችልም። ይልቁንም ክርስትናችንን ክርስቶስ በሚፈልገዉ መልኩ መኖር አስፈላጊ እና ለህይዎታችንም ጠቃሚ እና በረከትን የምያስገኘ ነዉ ሲሉ ሓሳባቸዉን ቋጭተዋል አባ ካንታላሜሳ አድሪያና ሜሶቲ እንደተጠናከረችዉ።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.