2015-12-07 16:15:00

የምኅረት ዓመት ቅዱስ በር የመክፈት ሊጡርጊያዊ ሥነ ሥርዓት


እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. የምህረት ዓመት ምክንያት በሚፈጸመው የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቅዱስ በር በመክፈቱ የሊጡርጊያዊ ሥነ ሥርዓት ቅዱስነታችው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንደሚሳተፉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ስለ ምህረት ዓመት በማስደገፍ አስተምህሮ ምዕዳንና ስብከት ሲሰጡ በምህረትና በእውነት መካከል ስላለው ግኑኝነት በተመለከተ ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ዋቢ በማድረግ ሲያብራሩ ተደምጠዋል። በተለይ ደግሞ ህዳር ወር 2015 ዓ.ም. ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ የመከረው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ባስጀመሩበትና በመጀመሪያው የሲኖዶሱ ቀናት ወቀት ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛን በስፋት ጠቅሰው እንደነበር ያስታወሰው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፦ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እውነት በሐቅ የተሰኘውን ዓዋዲ መልእክት ጠቅሰው እውነት ሰውን ልጅ ይከላከላል ሰብአዊ ፍጡር ከተለያዩ ርእሰ ዋቢነት ከማድረግና ፍርያማው ፍቅር ወደ ስግብግነት ከሚለውጥ፣ ቃል ኪዳን ወደ ጊዚያዊ አብሮ መርኖ ከሚለወጡ ፈተናዎች ይጠብቃል በማለት። አለ ሓቀ ፍቅር ወደ ራሮትና ኢተኣማኒ ስሜት ይቀየራል፣ ስለዚህ እንዲህ ሲሆን ፍቅር በተለያዩ አስፈላጊነት በሌላቸው ነገሮች የተሞላ ባዶ ጨዋታ ሆኖ ይቀራል፣ ባንድ አልቦ እምነት በሆነ ባህል ውስጥ ፍቅር ለዚህ ዓይነቱ ዕጣ ይጋለጣል ያሉትን ጠቅሰው ማብራራታቸው ይገልጣል።

በሲኖዶሱ ፍጻሜ ባስደመጡት ምዕዳን ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛን ጠቅሰው፦ ምኅረት እርሱም እግዚአብሔር የወንጌል መልእክት ማእከል ነው በማለት ሁሉም ቤተ ክርስቲያን የምትለውና የምታከናውነው ያንን እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያለው ምህረት የሚገልጥ ነው። ቤተ ክርስቲያን የምትለውና የታሳውቀው እውነት በዚያ ከእግዚአብሔር መሃሪው ፍቅር ተገፋፍታ ነው ምክንያቱም ሰዎች ሕይወት እዲሆናቸውና እንዲበዛላቸው ነውና” (ዮሐ. 10,10)።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. የምኅረት ቅዱስ ዓመት ሲያውጁ ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ ብዙውን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ምሕረት መስካሪ የመሆን ጥሪዋ እንዴት በማረግ ነው በሚገባ የሚበከረው በማለት ያስቡ እንደነበር ገልጠው፣ ይኽ ደግሞ በአንድ መንፈሳዊ መለወጥ የሚጀምር ነው። ስለዚህ ይኸንን በሚገባ ለማበሰርና ለመኖር አንድ ልዩ የምህረት ዓመት እርሱም የእግዚአብሔር ምህረት ማእከል ያደረገ ቅዱስ ዓመት አውጂያለሁ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.