2015-12-04 16:06:00

የሰላም ነጋዲ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የኡጋንዳው ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን አጠናቀው ከኢንተበ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ከሩብ ተነስተው በማእከላዊት ረፓብሊክ አፍሪቃ ርእሰ ከተማ ባንጒይ በሚገኘው ዓለም አቀፍ ያየር ማረፊያ እ.ኤ.አ. ጥር 2014 ዓ.ም. በተመረጡት የአገሪቱ የሽግግር መንግሥት ርእሰ ብሔር ካተሪን ሳምባ ፓንዛ ባንጒይ በሚገኙት የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክና በማእከላዊት ረፓብሊክ አፍሪቃ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት በብዙ ሺሕ በሚገመቱት የአገሪቱ ዜጎች አቀባበል ተደርጎላቸው ለአገሪቱና ለርእሰ ብሐር ክብር ወደ የአገሪቱ ቤተ መንግሥት በማምራት ከርእሰ ብሔር ሳምባ ፓንዛ የግል ግኑኝነት ካካሄዱ በኋላ በቤተ መንግሥት የጉባኤ አዳራሽ የአገሪቱ መንግሥትና የፖለቲካ አበይት አካላት ባንጉይ የሚገኙት የተለያዩ መንግሥታት ልኡካን በተገኙበት ርእሰ ብሔር ካተሪነ ሳምባ ፓንዛ፦

በፍርሃት ላይ የእምነት ድል አድራጊነት

የቅዱስነታቸው በአገሪቱ መገኘት በእውነቱ ቀኑ ታሪካዊና ልዩ ዕለት ነው በማለት ገልጠው፣ በፍርሃት ላይ ድል አድራጊው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እምነት መተሳሰብና ትብብር የሚመሰክር ነው።

ከቅዱስ አባታችን የጽናት ምስክርነት

አጠያያቂውና አሳሳቢው ወቅታዊው የፖለቲካዊ ጉዳይና ተጨባጭም ይሁን የተጋነነው አስጊ አደጋ ቅዱስነታቸው በመካከለኛይቱ ረፓብሊክ አፍሪቃ ጉብኝት ከማካሄድ አልከለከላቸውም፣ ይኽ ደግሞ ለሁሉም የጽናት ምስክርነትና ትምህርትም ነው ብለው ቅዱስነታቸው በማእከላዊት ረፓብሊክ አፍሪቃ ባለው ቀውስ ለአደጋ የተጋለጡትና ሰለባ ስለ ሆኑት ሁሉ ያሳዩት አሳቢነት የሚገልጥ ነው በማለት አመስግነው፣ ለሁሉም የአገሪቱ ዜጎች ጥልቅና ተጨባጭ አብነት ነው ብለዋል።

ስለ ሁሉም እሰቃቂ ተግባር ሁሉ ምኅረትና ይቅር መባባል

ለሁሉም የአገሪቱ የፖለቲካ አካላትና እንዲሁም በአገሪቱ አመጽ እንዲቀጣጠል በተለያየ መልኩ በተለያየ ደረጃ እጅ ያለባቸውና ጠንሳሾች በጠቅላላ በሃይማኖት ስም አማኞች የፈፍጸሙት ቅትለት የስግደትና የአምልኮ ሥፍራዎችን ያረከሰ ተግባር ሁሉ ከቅዱስ አባታች ይቅርታን በመለመን ምኅረትና ይቅር መባባል እንዲረጋገጥ ለሁሉም አደራ ብለው፣ በፍቅር ላይ የጸና ተጨባጭ መንፈሳዊ መንገድ በጋራ ለመከተል ምኅረትና ይቅር መባባል የማያሻማ ክብር ነው ብለዋል።

የመለያየትና የመከፋፈል ሰይጣናዊ ተግባር ለመገሰጽ የጸሎት ጸጋ

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በመካከለኛይቱ አፍሪቃ ጉብኝት ያሰጠው አቢይ ጸጋ የጸሎት ጸጋ ነው። ሁሉም ለዚህ ጥልቅ ጸጋ አነቃተዋል። ያ የሚለያይና የሚከፋፍል የሰይጣን መንፈስ የሚገስጽ የጸሎት የምህለላ መንፈስ በተግባር ያነቃቃ ጸጋ እንዲሰፍን አድርገዋል፣ ይኽ ደግሞ በእውነቱ ለአገሪቱ ለሰላም ሂደት ወሳኝ ነው ብለዋል።

ዳግም የዴሞክራሲ ሥርዓትና ጸጥታና ደህንነት በመካከለኛይቱ አፍሪቃ

የመካከለኛይቱ ረፓብሊክ አፍሪቃ ሕዝብ ለአገሪቱ መረጋጋትና ሰላም መሠረት የሆነው አገሪቱ አለ ምንም ቂም በቀልና መከፋፈል የጥላቻ መንፈስና የሃይማኖማኖትና የጎሳ አድልዎ ሁሉም ዜጋ በእኩልነት ለአገር ግንባታ የሚጠበቅበት አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የሚደግፈው የዴሞክራሲ ሥርዓትና ጸጥታና ደኅንነት ነጻ ሕዝባዊ ምርጫ እንዲረጋገጥ ተስፋ አድርገዋል፣ እውን እንደሚሆን በበኵላቸውም ያላቸው ተስፋ ገልጠው ደግመው ቅዱስ አባታችንን እንኳን ደህና መጡ በማለት ካስደመጡት ንግግር በመቀጠል ቅዱስ አባታችን አንድነት ሰብአዊ ክብርና ሥራ በተሰኙት ሦስት አበይት ቃላቶች ላይ በማተኰርም ባስደመጡት ንግግር፦

አንድነት በብዙኅነት ቀጣይና አቢይ ተግዳሮት ነው፣ ስለዚህ ይኸንን ተግዳሮት ገጥሞ ለማሸነፍ የፈጠራ ብቃት ቸርነትና መስዋዕትነት ሌላውን ማክበር ይጠይቃል፣ ከዚህ ጋር በማያያዝም ሰብአዊ ክብር የሚለውን ቃል ጠቅሰው፣ የገዛ እራሳቸው ሰብአዊ መብትና ክብር ብሎም ያለባቸው ግዴታ ጠንቅቀው የሚያወቁ በዚህ መሠረትም ለእርስ በእርስ መከባበር የሚያተኩሩ ዜጎች የሚለያቸው ግብረ ገባዊ ክብር ቅንነት ታማኝነት ሐቀኝነት ጸጋና ክብር የሚከተሉ ናቸው ብለው በመጨረሻም ሥራ በተሰኘው ቃል ላይ በማተኮር ለሁሉም ዜጎች ትምህርት የጤና ጥበቃ አገልግሎት መጠለያ ምግብ  የማግኘት መብት ማክበር ጋር የተያያዘ መሆኑ አብራርተው ይኽ ደግሞ ለተሟላ ሰብአዊ እድገት አቢይ ድጋፍ ከመሆኑም ባሻገር ለመደጋገፍና ለመተባበር የሚያነቃቃ ነው ብለዋል።

ማእከላዊት አፍሪቃ በተፈጥሮ ሃብት የታደለች አገር ነች፣ ይኸንን ሃብቷም በተገቢ አጠቃቀም ላይ በተመረኰዘ የተሟላ የአገር እድገት ማረጋገጥ ለሚል ዓላማ እንዲውልና የዚህ ሃብት ተጠቃሚም መላ ኅብረተሰብ መሆን አለበት፣ ከዚህ ጋር በማያያዝም ይሴባሕ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት በማስታወስ የተፈጥሮ ሃብት በመጠቀም የሚከወነው እድገት ሁሉም በብሔራዊ አቀፍም ይሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ ምኅዳር መከላከል በሚል እሳቤ የሚመራ መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያስደመጡት ንግግር፦ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በማእከላዊት ረፓብሊክ አፍሪቃ ሕዝባዊ እርቅ እንዲረጋገጥ ለሰላም መሠረት  መስፈርቶች ከሆኑት ውስጥ አንዱም ጥትቅ መፍታት የሚል ውሳኔ ሥር የተመራ ድጋፍ በማቅረ አገሪቱና ሕዝቧ ወደ ሰላም እንዲያቀና ትብብርና ደጋፍ ያስፈልገዋል፣ ለሰላም ሂደት ፍትህ መሠረት ያደረገ ማኅበራዊ ሰብአዊና ፖሊቲካዊ ሂደት አስፈላጊ ነው በማለት አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.