2015-11-23 16:36:00

ብፁዕ አቡነ ፊዚከላ፦ ቤተ ክርስቲያን ወደ ሰው ልጅ ለመድረስ ምህረትን የዘነጋች ሆና ነበር


ዛሬ ከምን ጊዜም በበለጠ የምህረት በር ሙሉ በሙሉ ክፍት መሆን እንደሚገባው የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላ ቅዱስ የምህረት ዓመትና እንዲሁም በቅርቡ በፓሪስ የተከስተው ቀውስ ርእሰ ሥር ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ ቤተ ክርስቲያን ይላሉ ብፁዕነታቸው አለ ምንም ፍርሃት ሁሉም ለማስተናገድ ከወትሮው በበለጠ የተነቃቃች ብቻ ሳይሆን ወደ ሰው ልጅ ለመድረስ የሚበቃ መንገድ የምህረት መንገድ መሆኑም ትመሰክራለች፣ ስለዚህ ወደ ሰው ለመድረስ የሚቻለው በምህረት መንገድ ነው፣ ከዚህ ውጭ ሌላ መንገድ የለም፣ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን ገዛ እራስዋ እንድታድስ የሚጠይቅ ጉዞ ነው። ለዚህም ነው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የህዳሴ እቅዳቸው እያረጋገጡ ባሉበት በአሁኑ ወቅት የምህረት ዓመት ያወጁት፣ የቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ማእከልም ምህረት መሆን አለበት፣ ይኽ መሆን እንዳለበትም የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቃልና ሕይወት ይመሰክረዋል።

የምህረት ዓመት ለሽበራ ጥቃት አመች ሁነት ይፈጥራል የሚል ስጋት አለ፣ በፓሪስ የተጣለው የሽበራ ጥቃት የሁሉም ልብ በሃዘን የሞላ ጉዳይ ነው፣ የምህረት ዓመት ፍቅር ሰላም መቀራረብ ባለ ድል መሆኑ የሚመሰክር ቅዱስ ዓመት ነው። ቤተ ክርስቲያን ፍቅርና ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረገው ሂደት የተለየ ሚና አላት፣ ሃይማኖት የሞት መሳሪያ ሊሆን እንደማይችል አበክራ ትመሰክራለች፣ በሃይማኖት ምክንያት የሚፈጸም አመጽና ቅትለት ለገዛ እራሱ የሃይማኖት ባህርይ የሚጻረር ነው፣ ምህረት ድካምነት ሳይሆን ጽናት ነው፣ የድካምነት ምልክት ቢሆንማ እግዚአብሔር ይቅር ባላለን፣ ብርታት በገዳይነት የሚገለጥ ሳይሆን ባዳኝነት ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.