2015-11-18 16:11:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሮማ የሚገኘው ሙክራብ ይጎበኛሉ


እ.ኤ.አ. ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሮማ የሚገኘው የአይሁድ እምነት ተከታዮች ሙክራብ እንደሚጎበኙት የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በመቀጠልም ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ይኸንን ሮማ የሚገኘው ሙክራብ ጎብኝተው ከአይሁድ ሃይማኖት አቢይ መምህርና የአይሁድ ሃይማኖት ተከታዮች ጋር ተገናኝተው እንደነበር ያስታወሰው የቅድስት መንበር መግለጫ በማያያዝ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይኸንን የሮማው ሙክራብ የጎበኙ ሦስተኛ ር.ሊ.ጳ. እንደሚሆኑም ያመለክታል።

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሮማ የሚገኘው የአይሁድ እምነት ሙክራብ ጉብኝት በማስመልከት የሮማ የአይሁድ ሃይማኖት ተከታይ ማኅበረሰብ ቃል አቀባይ ፋቢዮ ፐሩጃ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የሮማ የአይሁድ ሃይማኖት ተከታዮች ይኸንን የር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሮማው ሙክራብ ጉብኝት በደስታ እየተጠባበቁ መሆናቸው ገልጠው አንድ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ር.ሊ.ጳ. የሮማው ሙክራብ ሲጎበኙ የር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሦስተኛ መሆኑ አስታውሰው የሚደጋገም ጉብኝት ሳይሆን እያንዳንዱ ጉብኝት ለየት የሚያደርገው የራሱ መለያ ያለው ነው፣ የር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጉብኝትም ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በሙክራብ ያካሄዱት ጉብኝት ዝክረ 30ኛው ዓመት በሚታሰብበት ወቅት የሚከናወን በመሆኑም ቀጣይነት ያለውና ኅዳሴ ያለው ጉብኝት እንደሚሆን ነው ካሉ በኋላ፣ በእነዚህ ሁለቱ የመጽሓፍ ቅዱስ ታሪክ ወንድሞች የሆኑት የአይሁድ ሃይማኖት ተከታዮችና የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን መካከል የሚደረገው የጋራው ውይይትና ግኑኝነት የሚያጠናክር ነው ብለዋል።

አንድ የሚያደርገው የሚያገኛው የጋራው አካፋይ የሆነው ክብር ማጉላት የተገባ ነው። በዚህ በአሁኑ ወቅት ውጥረትና ፍርሃት በነገሰበት ዓለም ይኸንን ክብር አጉልቶ መኖር ለሰላም ሂደት ወሳኝ ነው። ስለዚህ የር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጉብኝት ይላሉ ለሰብአዊ አንድ አዲስ ወደ ሰላም የሚመራ ግፊት እንደሚሆን አያጠራጥርም በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.