2015-11-12 18:23:00

ቤተሰብ በማእድ ተቀምጦ ሳለ ቤተሰብን ሳይሆን ተለቪዥንና ተለፎንን ዝም ማሰኘት አለበት


ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! ዛሬ ስለ ቤተሰብ በተመለከተ ሕይወት ከመዝራት ጀምሮ ስለሚከናወነው አንድ አስፈላጊ ነገር እናስተነትናለን፤ ይህም አብሮ መኖር ማለትም በሕይወት ዘመን የምታገኘውን ሁሉ የመከፋፈል እንዲሁም ልታደርገው በቻልክ መጠን ደስታ የሚሰጥ ልማድ ማለት ነው፣ ያለህንና ያገኘሀውን ከሌሎች ጋር ማካፈልን ማወቅ ክቡር መንፈሳዊ ኃይል ነው፣ የዚሁ ምልክትም በማእድ አብራ የምትመገብ ቤተሰብ ነው፣ ምሳን ተካፍሎ ወይንም አብሮ መብላት ከምግብ ባሻገር የቤተሰብ ፍቅሩ ውይይቱ እና ሌሎች በኅብረት የምንካፈላቸው ነገሮችን ያመለክታል፣ ይህም መሠረታዊ ተመኵሮ ነው፣ በቤተሰብ ውስጥ አንድ በዓል ካለ የትውልድ ዕለት ማስታወሻ ዝክረ ዓመት ወዘተ አባላቹን በአንድ ማእድ ዙርያ ይሰበስባል፣ ባንዳንድ ባህሎች በኃዘን የሚገኙ ቤተሰቦችን ለማጽናናት ተብሎ በኃዘን ግዜም እንደዛ ያደርጋሉ፣

በቤተሰብ ያሉ ግኑኝነቶችን ለማወቅ የምንጠቀምበት መሳርያ አብሮ መኖር ሲሆን በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ስውርም ይሁን የተገለጠ ችግር መኖሩን ወዲያውኑ በማእድ ያስታውቃል፣ አብራ የማትመገብ ቤተሰብ እንዲሁም ምግብ እየበሉ ተለቪዥን በመመልከትም ይሁን ሌላ የመገናኛ ብዙኃን እንደ እስማርት ፎን መጠቀም ካለ ቤተሰቡ ሙሉ ቤተሰብ አይደለም፣ በማድ ቤት ሕጻናት ከኮንፕዩተርና የእጅ ተለፎን ተጣብቀው አንዱ ከሌላው የማይነጋገሩ ከሆነ ይህ ቤተሰብ አይደለም፣ ጡርተኛ ቤተሰብ ነው ለማለት ይቻላል፣ ክርስትና አብሮ ለመኖር ልዩ ጥሪ እንዳለው ሁሉም ያውቁታል፣ ጌታ ኢየሱስ ባለበጎ ፈቃደኞችን በማእድ ያስተምር ነበር አንዳንዴም መንግሥተሰማይን እንደ የደስታ ግብዣ ይመስለው ነበር፣ የመጨረሻ ኑዛዜውን ለሓዋርያት ሲተውም በራት ማእድ የሥጋውና ደሙ ተዝካር መሥዋዕት አቅርበዋል፣ ይህ የሥጋውና ደሙ የደህንነታችን መግብና መጠጥ እንዲሆኑ የሰጠበትና የእውነተኛና ዘለዓለማዊ ፍቅሩ መግለጫ ነበር፣

ስለዚህ በማእድ ያለው ቤተሰብ በቅዳሴ እንዳለ ነው ለማለት እንችላለን! ምክንያቱም ቅዱስ ቍርባን እንዲህ ባለ ሁኔታ አብሮ የመኖር ተመኩሮን በመስጠት እግዚአብሔር ለዓለም ያለውን ፍቅርን በመግለጥ ለኩላዊ የዓለም አብሮ መኖር በር ይክፈግታል፣ በቅዱስ ቍባን በመሳተፍ ቤተሰብ በገዛራሷ ከመዘጋት ፈተና ትነጻለች፤ በፍቅርና መተማመን በርትታም እንደ ልበ ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ ለወንድማማችነት ድንበሮችዋን ትከፍታለች፣

በብዙ መዝጋቶችና ግድግዳዎች በተመለከተው ዘመናችን ከቤተሰብ የተወለደችና በቅዱስ ቁርባን የተካነች አብሮ መኖር እጅጉን ታስፈልጋለች፣ ለዚሁ አብሮ መኖር የቀለቡ ቅዱስ ቁርባንና ቤተሰባዊ ትስስር እፊታችን ለሚደቀኑ የመለያየትና በገዛ ራስ የመዘጋት ፈተናዎችን አሸንፋ የፍቅርና እንግዳ የመቀበል ድልድዮችን ለማነጽ ትችላለች፣ የአንዲት ቤተሰባዊ ቤተክርስትያን ቅዱስ ቍርባን የአብሮ መኖርና የመስተንግዶ እርሾ በመሆን ግጭቶችን ሳፈራ ሁሉን የሚቀበል የሰብ አውነት ትምህርት ቤት ለመሆን ትችላለች፣ በዚሁ ማኅበር ቅዱስ ቁርባናዊ የቤተሰብ አብሮ መኖር ሊመግባቸው ሊከላከልላቸውና ሊቀበላቸው የማይቻላቸው ትናንሾች ወይንም እጓለማውታዎች ወይንም ደካሞች ወይንም የቆሰሉና ተስፋ የቆረጡ እንዲሁም የተተው አይገኙም፣

የእነዚህ ቤተሰባዊ ዕሴቶች ተዝካር ሁኔታዎችን ለመረዳት ይረዳናል፣ አንዲት እናት በልጆችዋ ላይ ያላት አመለካከትና ልዩ ትኵረት ስንት ተአምር እንደሚያደርግ አይተናል እናውቃለንም፣ እስከ ትናንትና ድረስ በአንድ አከባቢ አንዲት እናት በቂ ነበረች፣ ባለነው ዘመን ግን ለዚሁ ቤተሰባዊ አብሮ መኖር ዕንቅፋት የሚሆኑ ብዙ ማኅበረሰባዊ ችግሮች እየታዩ ነው፣ ወደ ድሮው መመለስ አለብን፣ በማድ ቤት አብሮ እየበሉ ዝምታ ቦታ ሊኖረው አይችልም፣ ሲሉ ቤተሰብ ሲባል አብሮ መኖር አብሮ መብላት አብሮ ማውራት ሁሉንም መካፈል መሆኑን ገልጠዋል፣ 








All the contents on this site are copyrighted ©.