2015-11-11 14:59:00

ብፁዕ ካርዲናል ባሰቲ፦ የቅዱስ አባታችን ሥልጣናዊ ምዕዳን ለቤተ ክርስቲያን ዝክረ ነገር


እ.ኤ.አ. ህዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኢጣሊያ ቶስካና ክፍለ ሃገር ሐውጾተ ኖልዎ በማካሄድ በፊረንዘ በተካሄደው ኣምስተኛው ብሔራዊ ቤተ ክርስቲያናዊ ጉባኤ ተገኝተው ሥልጣናዊ ምዕዳን መለገሳቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስነታቸው ስለ ለገሱት ሥልጣናዊ ምዕዳን በማስመልከት የፐሩጃ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጓልቲየሮ ባሰቲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ቅዱስ አባታችን የለገሱት ሥልጣናዊ ምዕዳን በኢጣሊያ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ዓዋዲ መልእክት ነው፣ በተለያየ ወቅት ለዚህች ቤተ ክርስቲያን የለገሱት ሥልጣናዊ ምዕዳን በአንድ ላይ ያጠቃለለ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሓዋርያዊ ግብረ ኖልዎ፣ ሐዋርያዊ መስተዳድር ባጠቃላይ ለተልእኮዋና ላገልግሎቷ ዝክረ ነገር ነው። በመሆኑም ምንም አይነት ሰብብ ማቅረብ የማይቻላት ነው።

ዝክረ ነገሩ ግልጽ የሆነ ራእይ ያለው፣ አምስተኛው ቤተ ክርስቲያንዊ ጉባኤ ሰብአዊነት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን እርሱም በኢየሱስ ክርቶስ የተገለጠው ሰብአዊነት የሚያበክር ነው፣ ያ በዚያች እነሆኝ የእግዚአብሔር አገልጋይ እንዳልከው ይሁንልኝ ባለቸው በማርያም ማሕንጸት የተሰገወ፣ የተሰቀለ ሞትን አሸንፎ የተነሣ ሰብአዊነት ነው። ቅዱስ አባታችን ይኸንን ሰብአዊነት በጥልቀት አብራርተዉታል፣ እሳቸው በቃልና በሕይወት ተናግረዋል፣ ካሁን በኋላ ኃላፊነቱ የእረኞች ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን በለገሱት ሥልጣናዊ ምዕዳን ለብፁዓን ጳጳሳት ለማኅበረ ክርስቲያን ለካህናት ባጠቃላይ ለብሔርም ጭምር ተናግረዋል፣ ባብራሩትና ግልጥ ባለ ሁኔታ በገለጡት ሰብአዊነት እርሱም ማኅበረ ክርስቲያንም ይኸንን ሰብአዊነት የሚያጎሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ቅዱስነታቸው የገለጡት ሰብአዊነት ወንጌላዊ እንጂ ርእዮተ ዓለማዊ ሰብአዊነት አይደለም።

ቤተ ክርስቲያን እጅጌዋን ሰብስባ ጎንበስ ብላ ታገለግልም ዘንድ ጠርተዋል፣ ክርስቲያናዊ ሰብአዊነትና ክርስቲያናዊ ሥልጣኔ ግልጥ ባለ አነጋገር ጥልቅ ትርጉሙን ገልጠዋል፣ ለወጣቶች በማስመልከትም ባሉት ቃልም የቤተ ክርስትያንና የኅብረተሰብ መጻኢ አብራርተዋል፣ ብርቱ ወጣት ተዘግቶ የሚቀር ያንቀላፋ በተለያየ ምክንያት ደንግዞና ፈዞ እንዳይቀርም በእግሩ ቆም ብሎ ሁኔታዎች ለመግጠም የሚችል መሆን እንደሚገባው ገልጠው፣ ይኽ ዓይነቱ መሆን እንዲረጋገጥም መደረገ ወይንም መሰጠት የሚገባው ደገፍ አመልክተዋል፣ ቤተ ክርስቲያን በሕዝብ መካከል የምትገኝ የቆሰለች በአገልግሎት ምክንያት እጆችዋ የቆሸሸ እንጂ በገዛ እራሷ የምትዘጋ ታማሚ ቤተ ክርስቲያን መሆን አይገባትም ብለዋል። ስለዚህ ይኸ ሁሉ በእውነቱ የቤተ ክርስቲያን ዝክረ ነገር ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.