2015-11-09 16:14:00

የቅድስት መንበር የዜና ኅትመት ክፍል መግለጫ


እ.ኤ.አ. ህዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በፊረንዛ በሚያካሂዱት ሓውጾተ ኖልዎ ከፖለቲካ አካላት ከመንግሥት ባለ ሥልጣናት ከኢጣሊያ መራሄ መንግሥት በጠቅላላ ከኢጣሊያ የፖለቲካ አካላት ጋር ለመገናኘት ፈቃደኛ አለ መሆናቸው ቅዱነታቸው ከወዲሁ አስታውቀዋል የሚባለው በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን እየተሰራጨ ያለው ዜና በማስመልከት የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈረሪኮ ሎምባርዲ እ.ኤ.አ. ህዳር 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ሕንፃ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስተባብለው፣ የኢጣሊያው መራሔ መንግሥት ቀደም በማድረግ እ.ኤ.አ. ሕዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም. በፊረንዘ ሊገኙ እንደማይችሉ መልእክት በማስተላለፈ ያሳወቁ እሳቸው ናቸው፣ ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ከመራኄ መንግሥት ጋር ላለ መገናኘት ይሻሉ የሚለው አሉታዊ ዜና ከእውነት የራቀ ከመሆኑም ባሻገር የኢጣሊያ መራሔ መንግሥት በፊረንዘ እንደማይገኙ እርሱም ቀደም ብሎ የተያዘ የሥራ እቅድ ስላላቸው አሳውቀው እንደነበር ገልጠው፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በፍሬንዘ የእግር ኳስ ሜዳ በሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ የመራሔ መንግሥት ቤተሰቦች እንደሚሳተፉ አባ ሎምባርዲ ገልጠው የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.