2015-11-09 18:01:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በጣልያን አገር በፍሎረንስና ፕራቶ የአንድ ቀን ሓዋርያዊ ጉብኝት


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በጣልያን አገር በፍሎረንስና ፕራቶ የአንድ ቀን ሓዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ ነገ ጥዋት ወደ ፍሎረንዝ እንደሚጓዙ ተመልክተዋል፣

በመርሓ ግብሩ መሠረት ነገ ጥዋት በሮም ሰዓት አቆጣጠር በጥዋት ሰባት ሰዓት ከቫቲካን በሄሊኮፕተር ተነሥተው ከአንድ ሰዓት የበረራ ግዜ በኋላ በፕራቶ የሚገኘው የስፖርት ሜዳ ይደርሳሉ፣ ቀጥታ የፕራቶ ካተድራልን ጎብኝተው በካተድራሉ አደባባይ ከሠራተኞች ጋር ተገናኝተው ከተናገሩ በኋላ እንደገና በሄሊኮፕተር ወደ ፍሎረንስ ይጓዛሉ፣ በፍሎረንስ የሚገኘው የልዊጂ ሪዶልፊ የአትለቲክስ ሜዳ ከሩብ ሰዓት በረራ ይደርሳሉና የፍሎረንስ መጥመቅያ ቦታ ይጐበኛሉ፣ የቅዱስነታቸው ሓዋርያዊ ጉብኝት አካል የሆነው የመላዋ ኢጣላያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን አምስተኛ ሃገራዊ ጉባኤ ለመሳተፍም ስለሆነ ይህ ጉባኤ እ.አ.አ ከዛሬ ጥቅምት ዘጠኝ እስከ እፊታችን ጥቅምት አሥራ ሶስት ቀን “አዲሱ ሰብአውነት በኢየሱስ ክርስቶስ” በሚል መሪ ሓሳብ በቅድስት ማርያም ዘፍዮረ ካተድራል አደራሽ እየተካሄደ ካለው የጣልያን አገር ቤተክርስትያን ሃገራዊ ጉባኤ ተወካዮች ስብሰባም ይሳተፋሉ፣ እኩለ ቀን ላይ በብሥራተ ማርያም ባዚሊካ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ በማቅረብና አብረው ከጸለዩ በኋላ በቦታው ለሚገኙ ሕመምተኞችን ይጐበኛሉ፣ እኩለ ቀን ተኩል ላይ ደግሞ በባሲሊካው አደባባይ በሚገኘው የድኃው ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ምግብ ቤት በማለት በሚታወቀው ከሚመገቡ ድሆች ጋር አብረው ምሳ ይበላሉ፣

በጣልያን አገር ሰዓት አቆጣጠር አሥራ አምስት ሰዓት ከሩብ በከተማው በሚገኘው አርተምዮ ፍራንክ ሜዳ ላይ መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ፣ ከመሥዋዕተ ቅዳሴው በኋላ ከአስተዳደርና መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር በመገናኘት ይሰናበታሉ፣ ማምሻውን በሄሊኮፕተር እንደሚመለሱ ተመልክተዋል፣

ሓዋርያዊ ጉብኝቱን በተመለከተ እርካታቸውና ደስታቸውን የገለጡ የፍሎረንስ ልሂቅ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ሲልቫኖ ፕዮቫነሊ ሃገራዊ ጉባኤውንና የር.ሊ.ጳ ጉብኝት አስመልከተው ለቫቲካን ረድዮ በሰጡት መግለጫ ፍሎረንስ የክርስትናና የባህል ማእከል ለመሆን ያበቃት የሰብ አውነት ሙላት በክርስትና ብቻ እንደሚገኝ በማወቅዋና ይህንን ለማራመድ ብዙ ጥናትና ሥነጥበባዊ ሥራዎች በማበርከት መሆንዋን እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣

“በእርግጥ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በፍሎረንስ ለሚያደጉት ጉብኝት በታላቅ ጉጕት እንጠባበቀዋለን፣ ትምህርታቸውን ለመስማትም ዝግጁ ነን፣ ቅዱስነታቸው በሕዝብ ላይ ብዙ መልካም ስሜት ፈጥረዋል እንዲሁም ከማንኛው ጋር ተገናኝተው ለመናገርና እንደወንድምና እኅት መቀበል ስለማያዳግታቸውም ጉብኝቱ አመርቂ ፍሬ እንደሚኖረው ባለሙሉ ተስፋ ነኝ” ሲሉ ከገለጡ በኋላ የፍሎረንስ የክርስትና ሁኔታ እንደቀድሞው አለ ወይስ ተለወጠ የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ሲመልሱ “ሁኔታው እንኳን ልትናገረው ልታስበውም ደስ አይልም! ፍሎረንስ በብዙ ነገሮች ተለውጣለች በተለይ የክርስትናን መንገድ ትታ በዓለማዊ ሰኩላር አስተሳሰብና አክሄድ መመራት ከጀመረች ዓመታት አልፈዋል፣ በዚህም ይሁን በሌላ ምክንያት የክርስትያኖች ቁጥር ቀንሰዋል፣ ነገር ግን ዋና ቍምነገሩ ብዛት አይደለም፣ የመጀመርያዎቹ ክርስትያኖች ያስታወስን እንደሆነ እጅግ ጥቂትና በየከተማው ትናንሽ ብድኖች ነው የነበሩት ሆኖም ግን ለሁሉም እስከሚያበሩ ድረስ ብርሃናቸው ይፈነጥቅ ነበር፣ በፍሎረንስም እንደዛ ሊሆን ተስፋ አለኝ፣ የቍጥር ጉዳይ ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ የመሞላትና የመመስከር ጉዳይ ነው፣ እንደድሮው የፍሎረንስ ከተማ የሥነሰብአውነት ማእከል በመሆን መለኮታዊውንና ምድራዊውን በክርስትና መንፈስ የምትገልጥ ባንልም ገና ሰብ አውነት ሙላትና ትርጉም የሚያገኘው በክርስትና መሆኑን በተቻለ አቅሟ ለመመስከር እየታገለች ነው፣ ፍጹም ሰውና ፍጹም አምላክ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስን ዓላማችን በማድረግና ትኵረታችን በእርሱ ላይ በማድረግ የፍቅርና የእውነት ጉዞ መራመድና ይህንን ጸጋ ለሌሎችም ተስፋ እንዲሆነ ማካፈል ነው፣ ምንም እንኳ ፍሎረንስ በምታደርገው ጥናትና ሁሉን ነገር ፍጹም ለማድረግ በምታካሄደው ጥረት እንደድሮም ባይሆን ክርስትያናዊ ምስክርነት እንደምትሰጥ ተስፋ አለኝ፣ ፍሎረንስ እኮ ኢየሩሳሌም ነች፤” ባሉበት ጊዜ በሮማ መገኘታቸውን ሊያስታውሳቸው ጋዜጠኛው “ሮማስ” ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ “ አረ ሁሉም ከተሞች ኢየሩሳሌም ናቸው፤ እያንዳንድዋ ከተማ እንደኢየሩሳሌም ክርስትናን ተቀብላ በዕለታዊ ሕይወትዋ ብትመሰክር እንዴት ጥሩ ነበር” በማለት ምኞታቸው ከገለጡ በኋላ ጋዜጠኛው አያይዞ ከሳምንታት በኋላ ሊታወጅ ቀርቦ ስላለው የምሕረት ኢዮቤልዩ አስመልክቶ “ፍሎረንስ በዚሁ ቅዱስ ዓመት የምሕረት ከተማ ልትሆን ትችላለች ወይ?” ብሎ ጠየቃቸው፣ ብፁ ዕነታቸውም ሲመልሱ “ነች እንጂ! ይህ የምሕረት ቅዱስ ዓመት የሚል አዋጅ እኮ ለመጀመርያ ግዜ በ1244 ዓም በዚች ከተማ ነው የተወለደው፤ እንደ አንድ የክርስትያን ማኅበር ነው የጀመረው፤ ማኅበሩም ለሌሎች ለማገልግል ሙታንን ለመቅበር ሕመምተኞችን ሆስፒታል ለማድረስ በቤቶች እየተዘዋወሩም ይረዱ ነበር፣ ስለዚህ በፍሎረንስ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ከተሞች እንዲሁ ዓይነት የምሕረት ማኅበር ተቋቍሞ ሌሎችን ለመርዳት የሚንበረከኩ ያስፈልጋሉ፣” ሲሉ ስለፍሎረስና ስለ ር.ሊ.ጳ ጉብኝት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፣ 








All the contents on this site are copyrighted ©.