2015-11-09 16:08:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ለቱኒዛውያን የሰላም ኖበል ተሸላምዊች፦ የሰላም ገንቢዎች


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የ 2015 ዓ.ም. የሰላም ኖበል ተሸላምዎች አርባእቱ የቱኒዚያ ዜጎች ሞሃመድ ፋድሀል ማህፉድ፣ አበደሳታር በን ሙሳ፣ ዊደድ ቡቻማኡይና ሁቺነ አባሲን እ.ኤ.አ. ህዳር 7 ቀን 2015 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ተቀብለው ማነጋገራቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሚከለ ራቪያርት ገለጡ።

ቅዱስነታቸው ከእነዚህ አርባዕቱ የሰላም ኖበል ተሸላሚዎች የአገረ ቱኒዚያ ዜጎች ጋር ባካሄዱት የ15 ደቂቃ ውይይት፦ እናንተ የሰላም ገንቢዎች ሥራችሁ እጅንና ልብን ያዋሃደ ተግባር ነው ላሉት ቅዱስ አባታችን አርባዕቱ የሰላም ኖበል ተሸላሚዎች በበኩላቸውም ቅዱስነታቸውን እውነተኛ የሰላም ሰው በማለት ገልጠው፣ በእሳቸው አቀባበል ተደርጎላቸው መልእክትም ስለ ተለገሰላቸው ያመሰገኑም ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ለእነዚህ የሰላም ኖበል ተሸላሚዎች ይሴባሕ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት እንደ ሥጦታ ሲለግሱ የሰላም ኖበል ተሸላሚዎችም በዓለም የሰላም ሰው ተብሎ የሚገለጠው በሁሉም የሚደንቀው የማህተማ ጋንዲ የምስል ቅብ ገጸ በረከት እንዳቀረቡላቸውም  ራቪያርት አስታወቁ።

እነዚህ የ2015 ዓ.ም. የሰላም ኖበል ተሸላሚዎች በረፓብሊካዊት ኢጣሊያ ርእሰ ብሔር አነሻሽነት በተዘጋጀው ዓውደ ጉባኤ በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙም ሲገለጥ፣ ለእነዚህ የቱኒዝ ዜጎች የተሰጠው የሰላም ኖበል ሽልማት ሰላምን የሚያበረታታ መሆኑ የቱኒዚያ የሕግ ጠበቃዎች ምክር ቤት አባል አብደላዚዝ ኤሲድ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው ቱኒዚያ እየተከተለችው ላለው ዴሞክራሲያዊ የሽግግር ጎዳና እውቅና የሚሰጥና በጀ የሚል ትእምርት ነው፣ ስለዚህ ማንኛውም ዓይነት ችግር ተገናኝቶ በመወያየት መፍትሄ ማፈላለግ እንጂ ችግሩን ሌላ ችግር በመፍጠር ለመፍታት ጥረት ማድረግ ወደ ቀጣይና ወደ ተወሳሰበ ችግር ማዝገም ማለት ይሆናል ብለዋል።

ሞሃመድ ፋድሀል ማህፉድ በበኩላቸውም ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ቱኒዚያ ዴሞክራሲያዊ የሽግግር ወቅት ለመኖር በቅታለች፣ ይኽ ደግሞ በፖለቲካ ደረጃ ነው። ነጻና ከማንኛውም ዓይነት ተጽእኖ ነጻ የሆነ ምርጫ ተካሂዷዋል፣ ፍትኅ ማኅበረሰብ ያሳየው ብስለት የሚደነቅም ነው ሲሉ የቱኒዚያ የሰውብአዊ መብት ተሟጋች ማኅበር ሊቀ መንበር አብደሳታር በን ሙሳም ይላሉ፣ የዓለም አቀፍ ሕጎች የሚያከብር የሕዝብ ባህልና አመለካከት የሚያንጸባርቅ ዴሞክራሲያዊ ሕገና ሥርዓት ለሰላም ወሳኝ ነው። ሕገ መንግሥት ነጻና ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ከሕግ በታች እንጂ ከሕገ በላይ የማይሆንበት ሥርዓት ማለት ነው። መንግሥት ቀዳሜ የሕገ መንግሥት አክባሪና አስካባሪ ሆኖ መገኘት ይጠበቅበታል፣ ይኽ ደግሞ ለአገራዊ ሰላምና እርቅ መሠረት ነው ብለዋል።

በመጨረሻም የቱኒዚያ የኢንዳስትሪ ማኅበር ሊቀ መንበር  ሞሃመድ በን ቸይክህ በበኩላቸውም ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በአሁኑ ወቅት ቱኒዝያ በተረጋጋ ሁኔታ ትገኛለች ብለው፣ ሆኖም መረጋጋቱ እንዳይበከል የሁሉም ንቁ ተሳትፎ ወሳኝ ነው፣ ወቅታዊው የአገሪቱ ችግር ይላሉ፣ ኤኮኖሚያዊ ጉዳይ ነው፣ ስለዚህ ሁሉም በመተባበር የአገርና የዜጎች ጥቅም በማስቀደም ከተጋ ኤኮኖሚያዊ ችግር ሳይቀር የሚፈታ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.