2015-11-09 16:17:00

ሮማ፦ ፍጥረትና ተፈጥሮ ለመንከባከብ ስለ መሬት የእግር ጉዞ


እ.ኤ.አ. ህዳር 8 ቀን 2015 ዓ.ም. ከኰሎሰዩም አደባባይ ተነስቶ ቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ደርሶ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በሚያሳርጉት ጸሎተ መልአከ እግዚብሔርና እንዲሁም በሚለግሱት የጸሎተ መልእከ እግዚአብሔር አስተምህሮ ሱታፌ የተጠናቀቀ የሮማ ሰበካ ያዘጋጀው የሰበካው የተፈጥሮ እቃቤ ቀን ምክንያት ተፈጥሮ ለመንከባከብ ስለ መሬት የእግር ጉዞ መርሃ ግብር መከናወኑ የቫቲካን ረድዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድድሮ ጓራሺ አስታወቁ።

የተካሄደው ስለ መሬት የእግር ጉዞ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ይሴባሕ ዓዋዲ መልእክት መርህ ያደረገ ሲሆን፣ በዚሁ መርሃ ግብር የተለያዩ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የተለያዩ ማኅበራት ተሳትፈዋል፣ ዜጎች ሕጻናት አዛውን ወጣቶች ያሳተፈ ሁሉም ተፈጥሮ የመንከባከብ ያለው ያሳሰበና ይኸንን ኃላፊነት እንዲከበርም የሁሉም ኅሊና ለማነቃቃት ዓልሞ መከናወኑ ከሮማ ሰበካ ጋር በመተባበር ስለ መሬት የእግር ጉዞ ያዘጋጀ የኢጣሊያ የመሬት ቀን ለተሰየመው ማኅበር ሊቀ መንበር ፒየርልዊጂ ሳሲ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል።

የቅዱስ አባታችን ይሴባሕ ዓዋዲ መልእክት ኤኮኖሚና ምኅዳር የተጣመሩ ናቸው የሚል የሰጡት ማብራሪያ ያ ቅጥ የለሽ ትርፍ ብቻ የሚል ስግብግቡ ኤኮኖሚ የተደላደለ ኑሮ ለማረጋገጥ የሚደግፍ የእድ ጥበብ ግኝት የሁሉም ሰው ልጅ ጥራት ያለው ሕይወት የጎዳ ለተለያዩ በሽታዎች ከማጋለጥም አልፎ ድኽነት በማስፋፋቱ ሂደትና የተፈጥሮ የአየር ብከላና መቀያየር የመሳሰሉት አሉታዊ ውጤቶች በመከወን ሰውንና ተፈጥሮን ለከፋ አደጋ እያጋለጠ ነው። ከዚህ ሁሉ ችግር ለመላቀቅ የዕደ ጥበብ እድገት መቃወም ሳይሆን ሰብአዊና ማኅበራዊ ኤኮኖሚያዊ እደ ጥበባዊ ምኅዳር ያለው ይሁን ለማለት ዓለሞ ተፈጥሮና ፍጥረት ለመንከባከብ ጥሪ ያቀረበ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.