2015-11-06 16:48:00

ብፁዕ ካርዲናል በቶሪ፦ የፊረንዘ ሕዝብ ቅዱስ አባታችንን በጉጉት እየተጠባበቀ ነው


እ.ኤ.አ. እፊታችን ማክሰኞች ህዳር 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኢጣሊያ ቶስካና ክፍለ ሃገር ሐውጾተ ኖልዎ እንደሚያካሂዱ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስነታቸው በፊረንዘ የቶስካና ክፍለ ሃገር ርእሰ ከተማ በሚካሄዳው ብሔራዊ ቤተ ክርስቲያናዊ ጉባኤ ተገኝተው መሪ ቃል እንደሚለግሱና ከቶስካና ክፍለ ሃገር ማሕበረ ክርስቲያንና ከክፍለ ሃገሪቱ የመንግሥት ተወካዮችና የመስተዳድር አባላት ከማኅበረ ፍትኃ ጋር እንደሚገናኙም ስለ ሐውጾተ ኖልዎ በማስመልከት ከቫቲክን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የፊረንዘ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጁዘፐ በቶሪ ገልጠው፣ በጠቅላላ የቶስካና ክፍለ ሃገር ሕዝብ ከቅዱስነታቸው ጋር ለመገናኘት በጉጉት እየተጠባበቀ ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን በፊረንዘ ለሚካሄደው ብሔራዊ ቤተ ክርስቲያናዊ ጉባኤ አቢይ ትርጉም የሚያሰጡና በሚያካሂዱት ሐውጾተ ኖልዎ የሚለግሱት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የዓቢይ የሐሴት ምክንያት እንደሚሆንም ነው ያሉት ብፁዕ ካርዲናል በቶሪ አያይዘው ኵላዊ ሐዋርያ ሊጎበኙን በመምጣታቸውም ጸጋ ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚህ በሚያካሂዱት የአንድ ቀን ሐውጾተ ኖልዎ ከኅሙማን ተነጥለው በድኽነት ከሚኖሩት በጠቅላላ በከተሞቻችንና በህልውና ጥጋ ጥግ ከሚኖሩት ከእስረኞች ጋር ይገናኛሉ፣ ፊረንዘ በሚገኘው አቢይ የእግር ኳስ ሜዳም መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳርጋሉ፣ ከኅሙማን ጋር በመሆን በቅዱስ ምስል ቅድስተ ማርያም ዘብሥራት ፊት ተገኝተው ማርያማዊ ጸሎት ያሳርጋሉ።  የአንድ ቀን ጉብኝት ቢሆንም ቅሉ የሚኖሩት ሐዋርያዊ መርሃ ግብር ጥልቅና ሰፊ መሆኑ ብፁዕ ካርዲናል በቶሪ ገልጠዋል።

ሁላችን እንደምናውቀው ሁሉም ሕዝብ ቅዱስ አባታችንን እንደ አባት ነው የሚመለከታቸው የሚያከብራቸው ቃላቸውም የሚያዳምጠው፣ የሳቸው የአባትነት መንፈስ በሁሉም የሚኖር ገጠመኝም ነው። ሁሉም ከሳቸው ጋር ለመገናኘት ለመነጋገር ይፈልጋል፣ ምክንያቱም የሚረዱ ትሁት የዋህና ቀጥተኛ አመለካከት ያላቸው አባት ናቸውና። የሕዝበ እግዚአብሔር ስቃይ ተራውን ሕዝብ የሚረዱ በመሆናቸውም በእውነቱ በሁሉም ዘንድ ተወዳጅነት አላቸው።

የሚካሄደው ብሔራዊ ቤተ ክርስቲያናዊ ጉባኤ ዋናው ርእሰ ሰብአዊነት የሚል ነው። ስለዚህ የውይይቱ ርእስ አዲስ ሰብአዊነት ላይ ያተኮረ እንደሚሆን ገልጠው፣ በአሁኑ ወቅት ያንን እውነትኛውን ሰበአዊነት በእያንዳንዳችን ዘንድ በኑባሬ ያለው ባህይር የሚቀናቀን የሚጻረረ ሁነት እየተፈጠረ ሰብአዊነት ለአደጋ ተጋልጦ ይገኛል፣ ስለዚህ ይኸንን ሰብአዊነት ዳግም ለመገንባት ወደ አናሥር መመለስ ያስፈልጋል፣ ያንን የእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ መሆን መለስ ብሎ በማስተዋል እንዲኖር የሚያሳስብ ዓውደ ጉባኤ ነው። ሰብአዊነታችን የእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ የሚል ነው፣ ይኽ ደግሞ የፍጹም ልጁ አርአያና አምሳያ ነው። የወደመው ሰብአዊነታቸው መልሶ ዳግም ያለበሰንም እርሱ ነው። ሰብአዊነታችን ባጭሩ ቲዮሎጊያዊ ትርጉም ይኽንን ይመስላል፣ ዓውደ ጉባኤው ይኸንን ሃሳብ በስፋት እንደሚያብራራውም ገልጠው የዚህ ሰብአዊነት ማእከልም እሴቶች ናቸው፣ እርሱም ፍጹምና የሚሰዋ ፍቅር የሚል ነው። ፍቅር ለድኾች ፍቅር ለተጠማው ፍቅር ለተናቀው የሚል ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.