2015-11-04 16:30:00

የፈረሳይ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ምሉእ ጠቅላይ ጉባኤ


የፈረንሳይ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የማርሲሊያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ገርገስ ፖንቲየር ቤተ ክርስቲያን በእግዚአብሔር መኃሪነትና የዋህነት ተመርታ እንደ እናት ለልጆችዋ የዋህና መኃሪ በመሆን ትሸኛለች የሚል ሃሳብ ማእከል በማድረግ በቅርቡ በአገረ ቫቲካን የተካሄደው ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ የመከረው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን 14ኛው ልዩ ሲኖዶስ በተመለከተ ሰፊ ንግግር በማስደመጥ 118 ብፁዓን ጳጳሳት በአባልነት የሚያቅፈው የአገሪቱ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. እስከ ህዳር 8 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚዘልቀው ይፋዊ ጠቅላይ ጉባኤ ማስጀመራቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የሲኖዶሱ ፍጻሜ

ብፁዕ አቡነ ፖንቲየር ባስደመጡት ንግግር ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ የመከረው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት 14ኛው ይፋዊ ልዩ መደበኛው ሲኖዶስ ወቅታዊው ዓለም በዕለታዊ ሕይወቱ የሚያጋጥመው ችግር ቁስል የመከረ መሆኑ በማብራራት በእውነቱ ለተሰራው ምስጢረ ተክሊል በመላ ሕይወታቸው በታማኝነት የሚኖሩት ባለ ትዳሮች የተባረኩ ናቸው፣ የሚደነቁም ናቸው፣ ስለዚህ ይኽ ቤተሰብ ቀዳሚ የወንጌል አብሳሪ ነው። የሚመሰከረው ወንጌል ከኢየሱስ ክርስቶስ ቢሆንም ቅሉ አሳማኝነቱ እንዲጎላ የሚያደርገው በወንጌላዊ ታማኝነት የተካነ ሕይወት የሚኖር ክርስቲያን ነው። የሲኖዶሱ የፍጻሜ ሰነድም የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ውሳኔና ኃላፊነት ነው እሳችውን እንጠባበቃለን እንዳሉ የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ ቅዱስነታቸው የሚለግሱት የፍጻሜ ሰነድ በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በሕገ ቀኖና ተተርጉሞ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ገቢራዊ ይሆናል ብለው በሲኖዶሱ የተኖረው ገጠመኝም ጠለቅ በማድረግ በማብራራት፣ በጦርነት በአመጽ ለስቃይ የተዳረገው ቤተሰብ ለስደትና ለጥገኝነት ጥያቄ የተገደደው ቤተሰብ ጉዳይ ሲኖድሱ መክረዋል። ይኽች ቤተሰብ የጀግንነት ሙያ ፈጻሚ በማለትም የሲኖዶስ አበው ይገልጧታል እንዳሉ አስታወቀ።

የስደተኞችና የተፈናቃዮች ስቃይ

በኢጣሊያ የአግሪጀንቶ ክፍለ ሃገር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ሞንተነግሮ የስደተኞችና የተፈናቃዮች ርእስ ዙሪያ በጉባኤው ተገኝተው ንግግር እንደሚያስደምጡ ሲር የዜና አገልግሎት ጠቅሶ አያይዞም ብፁዕ አቡነ ዣገር በካላይስ የስደተኞች ጉዳይ በማስመልከት ንግግር እንደሚያስደምጡም ገልጦ፣ ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት ብፁዕ አቡነ ፖንቲየር ስደተኞች ኤውሮጳ የበለጸገ ዓለም እንዲሆን የተካሄደው ጥረትና የተረጋገጠው ታሪክ ተወናያን ጭምር ናቸው፣ ስለዚህ ለኤውሮጳ ግንባታ የስደተኞች ተሳትፎ የታሪክ ሐቅ ነው እንዳሉ አስታውቀዋል።

የመሬት ጠባቂዎችና ተንከባካቢዎች እንጂ ጌቶች አይደለንም

በአሁኑ ወቅት ፈረንሳይ በፓሪስ እ.ኤ.አ. ወርሃ ህዳር ማብቂያ ምኅዳር ማእከል በማድረግ የሚካሄደው ዓለም አቀፍ ዓውደ ጉባኤ ሂደቱና የሚያቀርበው አስተያየትና የሚሰጠው ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ እንደምትገኝና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ይሴባሕ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት ሊካሄድ ተወስኖ ላለው ዓውደ ጉባኤ ድጋፍ እንደሚሆንም ብፁዕ አቡነ ፖንቲየር ገልጠው፣ ዓዋዲ መልእክቱ ተቀባይነት ያለው ፍጥረት በሞላ የሚያከብር የልማት እቅድ የሚያነቃቃ በተፈጥሮ ፊት የሰው ልጅ ኃላፊነት ግልጥ አድርጎ የሚያብራራ ያንን የሰው ልጅ የተፈጥሮ ገዥ የሚያስመስለው ተግባሮቹ ሁሉ እንዲለውጥ የሚመራ ተፈጥሮ በሕይወት ላሉት ብቻ ሳይሆን ለመጪው ትውልድ ጭምር መሆኑ የሚያስገነዝብ ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልልጎት አስታወቀ።  








All the contents on this site are copyrighted ©.