2015-11-04 19:56:00

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ!


 

ውድ ወንድሞችና እኅቶች! እንደምን አደራችሁ! ከጥቂት ቀናት በፊት የተገማደደው የሲኖዶስ አበው ጳጳሳት ጉባኤ ቤተሰብ በቤተክርስትያን ሕይወትና ባለነው ዘመን ያለውን ጥሪና ተልእኮ በሚመለከት በጥልቀት አስተንትነዋል፣ የጸጋ ግዜ ነበር፣ በጉባኤው ፍጻሜ ላይ የሲኖዶስ አበው የተወያዩበትና የተስማሙበት ማጠቃለይ ሰንድ አስረከቡኝ፣ ሰነዱ ታትሞ ለሁላችን እንዲዳረስ እፈልጋለሁ ምክንያቱም ለሁለት ዓመታት ያህል ስንሠራ የተከታተሉን ሁላቸው በዚሁ ሥራ እንዲሳተፉ በሚል ሃሳብ ነው፣ ግዜው በእነዚህ መደምደምያ አንቀጾች የማስተንተንበትና የምመረመርበት ጊዜ ሆኖ አይታየኝም፣

በዚሁ የአስተንትኖና ምርመራ ጊዜ ሕይወት አትቆምም! በተለይ ደግሞ የቤተሰብ ሕይወት ቆሞ አይቀርም፣ እናንተ ውድ ቤተሰቦች ሁሌ በጉዞ ናችሁና፣ በየዕለቱም የቤተሰብ ወንጌል ጣዕምን የሚገልጽ በተግባር በሕይወት ኑሮአችሁ በተከታታይ ትጽፋላችሁ፣ በዚሁ አንዳንዴ የሕይወት አንዳንዴም የፍቅር ደርቅ በሚታይበት ዓለማችን እናንተ ስለታላላቅ ስጦታዎች ማለትም ስለ ትዳርና ስለቤተሰብ በየዕለቱ ትናገራላችሁ፣

ዛሬ ይህንን ጉዳይ ላስምርበት እወዳለሁ! ማለትም ቤተሰብ አንዱ ለሌላው ስጦታና ምሕረት የማቅረብ ልምምድ የሚካሄድበት ታላቅ ሜዳ መሆኑን እገልጣለሁ፣ አለቤተሰብ ምንም ፍቅር ለረዥም ጊዜ ሊቆይ አይችልም፣ ገዛራስን ካለመስጠትና ምሕረትን ካለመለገስ ፍቅር ሊኖር አይችልም፣ ጌታ በቃሉ ባስተማረን የአቡነ ዘበሰማያት ጸሎት ኢየሱስ አባታችንን “የበደሉንን ይቅር እንዳልን ሁሉ በደላችንን ይቅር በልልን” ብለን እንድንለምነው ይነገረናል፣በወንጌለ ማቴዎስም “ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤  ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም።”(6፤14-15) በማለትም የጸሎቱን ትርጉም ያብራርልናል፣ ይቅር ሳይሉ መኖር አይቻልም በተለይ በቤተሰብ ውስጥ አይጥምም፣ በየዕለቱ አንዱ ሌላውን ስንበድል እንኖራለን፣ በድካማችንና በእኔነታችን ለሚከሰቱ ለእነኚህ ጉድለቶች በየዕለቱ ኅልናችን መመርመር ያስፈልገናል፣ ማድረግ ያለብንም ስህተት ከተፈጸመ ወዲያውኑ እርማት ማድረግ በተለይ በቤተሰብ ውስጥ በጥፋታችን ለተበጣጠሱ የቤተሰብ ግኑኝነቶችን ወዲያውኑ በምሕረት መፈወስ አለብን፣ ለረዥም ግዜ ይዘነው የጠበቅን እንደሆነ እጅግ ይከብዳል፣ የዚህ ዓይነት ቁስሎችና ችግሮችን የመፈወስ ፍቱንና ቀላል መድኃኒት አለ፣ ይህም በየዕለቱ ይቅርታ ሳይጠይቁ ባልና ሚስት ሰላም ሳይፈጥሩ እንዲሁም በወላጆችና በልጆች መካከል በወንድማሞች መካከል ወዘተ ዕለቱን አለማሳለፍ ነው፣ ለነገ የሚባል አይደለም፣ ወዲያውኑ ይቅሬታ መጠየቅን ከተማርንና አንዱ ሌላውን ምሕረት መስጠት ከቻልን ቁስሎቹ ይድናሉ የቤተሰቡ መተሳሰርም ይጠነክራል፣ ቤተሰቡም ጽኑ ሆኖ በምንፈጽማቸው ትናንሾችና ትላልቅ ጥፋቶች የሚያስከትለውን መናወጥ ይቋቋማል፣ ስለዚህም በቤተሰብ ውስጥ ለዕርቅና ሰላም ተብሎ ረዥም ውይይትና ንግግር ሳይሆን በፍቅር ሰላምታና ይቅርታ መለዋወጥ በቂ ነው ከዛ በኋላ ሁሉ ተረስቶ አዲስ ህይወት ይጀምራል፣ እባካችሁ ቀኑን በሁከት አትፈጽሙት! ተረዳችሁት ወይ!

በቤተሰብ ውስጥ እንዲህ መኖር የተማርን እንደሆነ ከቤተሰብ ውጭ በምንገኝበት ቦታ ሁሉ እንዲሁ እናደርጋለን ማለት ነው፣ ስለዚህ ጉዳይ መጠራጠር ቀላል ነው፣ ብዙ ሰዎች ክርስትያኖችም ጭምር የማጋንን ይመስላቸዋል፣ እንዲህ ለማለት ይቻላል ሆኖም ግን ጥሩ ቃላት ብቻ እንጂ እተግባር ላይ ለመዋል የማይቻል ነው ይላሉ፣ ነገር ግን ምስጋና ለእግዚአብሔር ሁኔታው እንዲህ አይደልም፣ እንደእውነቱ ከሆነ ከእግዚአብሔር ምሕረት በመቀበል እኛም በበኩላችን ለሌሎች ምሕረት መለገስ እንችላለን፣ ለዚህም ነው ጌታ ኢየሱስ በሰማይ የምትኖር አባታችንን ስንጸልይ እላይ የጠቀስናቸውን ቃላት በየዕለቱ እንድንደግማቸው የሚጠይቀን፣ እንዲሁ በተበታተነው ማኅበረሰባችን እንደቤተሰብ ያለ አንዱ ሌላውን ይቅር ለማለት የምንማርበት ቦታ እንዲኖር የግድ ነው፣

የአበው ጳጳሳት ሲኖዶስም በዚህ ጉዳይ ተስፋችንን እንደገና እንዲበራ አደረገው ምክንያቱም ይህ ይቅር የማለትና ምሕረት የመቀበል ጉዳይ ከቤተሰብ ጥሪና ተልእኮ አንዱ ነውና፣ ይቅር ማለት ቤተሰብን ብቻ አይደለም ከመከፋፈል የሚያድነው ነገር ግን ማኅበረሰባችን ከክፋትና ከጭካኔ ይገተዋል፣ እያንዳንዱ የምሕረት ሥራ የቤቱ መፈራከስን አስተካከሎ ግድግዳው እንዲጸና ያደርጋል፣ ውድ ቤተሰቦች ቤተ ክርስትያን እጐናችሁ በመሆን ጌታ በተናገረው አለት ላይ ቤታችሁን ለመገንባት እንድትችለ ትረዳችኋለች፣ በወንጌለ ማቴዎስ ይህንን ምሳሌ የሚከተለውን አንዘንጋ “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። (7፡21-23) ይላል፣ ኃያል ቃላት ናቸው! ኅልናችን ቀስቅሶ ለንስሓና ለለውጥ እንዲጠራን የተናገረው መሆኑም አያጠራጥርም፣

ውድ ቤተሰቦች በወንጌል የብፅዕና ጐዳና ለመራመድ ቈርጣችሁ የተነሳችሁ እንደሆነና አንዲ ሌላው ይቅር ለማለት በማስተማርና በመማር ለመጓዝ የቻላችሁ እንደሆነ በታላቅዋ ቤተሰብ የሆነችው ቤተክርስትያን የአሳዳሹ የእግዚአብሔር የምሕረት ኃይል የመመስከር ችሎታችን እንደሚያድግ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፣ አለበለዚያ ግን ምንም እንኳ ልብ የሚቀሰቅስና ነፍስን የሚያረካ ቆንጆ ስብከት ብንሰብክ አጋንንትም ብናባርር በመጨረሻው ግን ጌታ በወንጌል እንደተመለከትነው እንደተከታዮቹ አላውቃችሁም ሊለን ይችላል፣

እውነት እላችህዋለሁ የክርስትያን ቤተሰቦች ባለነው ዘመን ለማኅበርሰብና ለቤተክርስትያን ብዙ ነገሮች ሊያበረክቱ ይችላሉ፣ ስለዚህ በዚህ የምሕረት ኢዮቤልዩ ቤተሰቦች አንዱ ሌላውን ይቅር በማለት የሚገኘውን ሃብት እንዲያውቁት ይሁን፣ ማንም ሰው ባለዕዳ ሆኖ የማይሰማበት ኑሮ እንዲገኝ ቤተሰቦች ተጨባጭ የዕርቅ መንገዶች እንዲገነቡና በተግባር እንዲኖርዋቸው ይችሉ ዘንድ እንጸልይ፣

በዚህ አሳብም ሁላችን በኅብረት “በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ የበደሉንን ይቅር እንድምንል በደላችንን ይቅር በልልን” እንበል፣ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፣ 








All the contents on this site are copyrighted ©.