2015-11-02 15:56:00

ዜና ዕረፍት


ለሠላሳ ዓመት በቫቲካን ረዲዮ በጋዜጠኝነት ሞያ ያገለገሉ በጥዑም ልሳናቸው ታዋቂነት ያላቸው የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ጥንቁቅ አዋቂ በዚሁ ጉዳይ በሳል አስተያየት አቅራቢና ተንታኝ በሚያቀርቡት የዓለም አቀፍ ፖለቲካ ትንተና እጅግ ተደናቂነት ያላቸው፣ ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በአንጎላ ከዛም በኵባ ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ባካሄዱበት ወቅት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቅድስት መሬት ባካሄዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ጭምር ከሸኙዋችው የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኞች አንዱ የበልጂም ተወላጅ በቫቲካን ረዲዮ የፈረንሳይኛ ቋንቋ ጋዜጠኛ በርናርድ ደኮቲኘ በ 56 ዓመት ዕድሚያቸው እ.ኤ.አ. ህዳር 1 ቀን 2015 ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

በዚህ አጋጣሚም የቫቲካን ረዲዮ ሠራተኞችና ጋዜጠኞች የተሰማቸው ጥቅል ሃዘን በመግለጥ  ለእኚህ የዋህ ለሁሉም ቅርብ በተለይ ደግሞ በሰብአዊ አደጋ ለተጠቁት እግጅ ቅርብና አሳቢ የተለያዩ የሰብአዊ ድጋፍና ትብብር መርሃ ግብሮች በማረጋገጥ አቢይ አስተዋጽኦ የሰጡ ለእንስሳትና ለተፈጥሮ ለስነ ቅብና ለስነ ግጥም አቢይ ፍቅር የነበራቸው ባጋጣሚ ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት ባልደረባችን በጸሎታችን እናስባቸው፣ በልባችን ህያው ለሆኑት ወንድም በርናርድ ደኮቲኘ እግዚአብሔር በመንግሥቱ እንዲቀበላቸው እንማጠናለን።








All the contents on this site are copyrighted ©.