2015-11-02 15:59:00

ካሜሩን፦ ወጣት ትውልድ ከጦር መሣሪያ ለማግለል የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ እቅድ


በካሜሩን እሩቅ ሰሜናዊ ክልል በሚገኙት የተለያዩ ታጣቂ ኃይሎች የገሪቱ ወጣት ትውልድ ጦር መሣሪያ እዲያነግብ በሚያረማምዱት የምልመላ ዘመቻ እንዳይሳብና ለዚህ ለሞት ለሚዳርግ ምርጫ መሣሪያ እንዳይሆን በአገሪቱ የማሩዋ ኮኮሎ ሰበካ ከካመሩን የሁሉም ሃይማኖቶች የጋራ ውይይት የሚያነቃቃው ማኅበር ጋር በመተባበር ወጣቱ በልማት ጎዳና ተሳታፊ የሚያደርገው የሕንጸት እቅድ መወጠኑ ሲገለጥ፣ የምስልምና እምነትና የክርስትና እምነት ተከታይ ያገሪቱ ወጣት ዜጋ በሥነ እርሻ በሥነ እንስሳት ርቢ ሕንጸት ለማሰልጠን እቅድ መወጠኑ ከካሜሩን የሚሰራጩ ዜናዎች ይጠቁማሉ።

ሃይማኖቶችና መንግሥት በጋራ ድኽነት በመዋጋት ተግባር

ይኽ የተለያዩ በካሜሩን የሚገኙት ሃይማኖቶች በጋራ የወጠኑት ወጣት አድን የተሰኘው የሕንጸት እቅድ በማስመልከትም የካሜሩን የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ማኅበር ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ኣብዱራህማን ሳይዱ የተወጠነው የሕንጸት እቅድ ድኽነት ለመዋጋት ጭምር የሚያግዝ መሆኑ በማብራራት በዚህ እቅድ መንግሥት እንዲተባበር ጥሪ ማቅረባቸው የገለጡት የአገሪቱ የዜና አውታሮች አክለው ወጣቱ በቀላሉ በተለያዩ የወንጀል ቡድኖችና ታጣቂ ኃይሎች እንዳይማረክ ብሎም በሥራ ዓለም እንዲሳተፍ የሚያበቃው ሕንጸት በማቅረብ የገዛ እራሱ መጻኢ በመገንባት የአገር ብሩህ መጻኢነቱ እንዲመሰክር የሚደግፍ እቅድ ነው እንዳሉም ያመለክታሉ።

በግል ሥራ ፍቅርና ተዋህዶ በመኖር ባህል ማነጽ

ያለው የሥራ አጥነት ችግር እግምት ውስጥ በማስገባትም፣ ወጣቱ ትውልድ በግል ሥራ እርሱም በግብርናው መሥክ እንዲሰማራ የሚያበቃው ስልጠና በማቅረብ ተፈጥሮን በማፍቅር ባህል ገዛ እራሱ ከመደገፍ አልፎ በማኅበራዊ ሕይወት ተዋህዶ እንዲኖር የሚያበቃው በኤኮኖሚው ፖለቲካ ተሳታፊነቱ የሚያነቃቃ ሕንጸት በማቅረብ ከሞት ባህል ማዳን የሚል እቅድ መሆኑም ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.