2015-11-02 15:41:00

ብፁዕ አቡነ አውዛ፦ የሕይወትና የሃይማኖት ነጻነት እንዲከበር


የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ማነቃቃትና ጥበቃ በሚል ርእስ ሥር በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በተካሄደው 70ኛው ክፍለ ጠቅላይ ጉባኤ የተሳተፉት በድርጅቱ ለቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ ኣቡነ በርናርዲቶ አውዛ፦ የሕይወት ነጻነት የሰብአዊ መብትና ክብር መሠረት ነው በሚል ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ ንግግር በማሰማት፣ የህሊና እንዲሁም የሃይማኖት ነጻነት ማነቃቃትና ጥበቃ እንደሚያስፈልግ ማብራራታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጋብሪኤላ ቸራዞ አስታወቁ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሕይወት ነጻነት የሰው ልጅ የህላዌ ባህርይ ነው በማለት የገለጡት የሕይወት ነጻነት የሁሉም ነጻነት መሠረት መሆኑ ብፁዕ አቡነ አውዛ በማብራራት፦ ይኽ የሁሉም ነጻነት መሠረት የሆነው በዓለም አሁንም ለአደጋ እየተጋለጠ ችላ እየተባለ ከዚህ ይባስም እንደ ማያስፈልግ ተደርጎ እንደሚታይና ድኾች የሚኖሩት ሕይወት በቀላሉ ላደጋ መጋለጡና የኅብረተሰብ ክፍል አባላት የሆኑት ሕጻናት አረጋውያን ስንኩላን የጦር ጉዳተኞች የሚያጋጥማቸው አደጋ ብሎም የሰው ልጅ ለክብር ሰራዥ አደጋ መጋለጥና ሰው ልጅ በተለያዩ የወንጀል ቡድኖች ለክብር ሰራዥ ተግባር ከቦታ ቦታ የማዘዋወሩ የአዲስ ባርነት ተግባር ስደትና መፈናቀል ለመሳሰሉት አደጋዎች የተጋለጠ መሆኑ የሚመሰክረው ነው እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ ገልጠው፣ ሕዝቦች ከማኅበራዊ ጥቅም ከተፈጥሮ ሃብት ጥቅም እንዳይገለሉ ማድረግና የሕይወት ነጻነት በማነቃቃት በማክበር፣ ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት በሕገ ፖለቲካ እንዲከበር ማድረግ ብቻ ሳይሆን ምኅዳር በመንከባከብና የሰው ልጅ መሠረታዊው ፍላጎት ማረጋገጥም እንደሚጠይቅ ነው እንዳሉ አስታውቀዋል።

አዳዲስ መብትና ክብር ተብለው የሚገለጡት አስተሳሰብ ለማረጋገጥ በሚል ዓላማ የሰው ልጅ መሠረታዊ የሆነው መብትና ክብር የሆነው የአስተሳሰብ የህሊና የሃይማኖት ነጻነት የመለወጥ ነጻነት የስግደትና የአምልኮ ነጻነት ችላ የማለቱ ምርጫ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው። ስለዚህ መሠረታዊው የሃይማኖት ነጻነት ለጥቂቱ የኅብረተሰብ ክፍል ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ሰው የሚመለከት ጉዳይ ነው ያሉት ብፁዕ አቡነ አውዛ አያይዘው፦ በአሁኑ ወቅት የአስተሳሰብ የህሊና የሃይማኖት ነጻነት ለከፋ አደጋ የተጋልጠ ሆኖ በሃይማኖት ስም በሰው ልጅ ላይ የሚፈጸም አመጽ እጅግ እየተስፋፋ፣ ብዙዎች በግድ እምነታቸው እንዲክዱና እንዲለውጡ ካልሆነም ንብረታቸውና ቤታቸውን እንደሚያጡ እየተደረገና አሊያም ገዛ አገራቸው ለቀው ለስደትና ለመፈናቀል ውሳኔ ተላልፈው እንደሚሰጡና ለሞትም እየተዳረጉ መሆናቸው ጠቅሰው የተለያዩ ሃይማኖቶች ባህሎችና ጎሳዎች ለከፋ አደጋ ተጋልጠው እያሉ የዓለም አቀፍ ፖለቲካና ብሔራዊ አቀፍ ፖለቲካ ይኸንን ጉዳይና በዚህ ወንጀል ተጠቂ የሆነውን የሕብረሰብ ክፍል ከመደገፍ ዝምታ የመረጠ ይመስላል እንዳሉ ቸራዞ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.