2015-10-30 15:19:00

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፦ ስለ ሲኖዶስ፣ ቻይና በተመለከተና በቅርቡ ቅ.አባታችን ስለ ሚያከናውኑት ሐዋርያዊ ጉብኝቶች


የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፍ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን እ.ኤ.አ. ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ Nostra Aetate-ያለንበት ዘመን የተሰኘው ሁለኛው የቫቲካን ጉባኤ ውሳኔ ማእከል በማድረግ በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም. የተጠናቀቀው ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ የመከረው 14ኛው ይፋዊ መደበኛው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ልዩ ሲኖዶስ፣ ያጸደቀው የፍጻሜ ሰነድ መሠረት በማድረግ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ስለ ሚለግሱት ድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ያካተተ ንግግር ማሰማታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሚከለ ራቪያርቲ አስታወቁ።

ከዓውደ ጉባኤው ፍጻሜ በኋላ ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በቤተ ክርስቲያን ባህል መሠረትም በሁሉም በሚካሄዱት ሲኖዶሶች እንደሚደረገው ሁሉ በቅርቡ የተጠናቀቀው ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ የመከረው የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በዚሁ ርእስ ዙሪያ የደረሱት የተለያዩ አስተንትኖዎች ያቀፈው ሰነድ ለቅዱስ አባታችን በማቅረብ አንድ ድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን እንዲለግሱ ተመጽነዋል፣ ቅዱስ አባታችን ሐዋርያዊ ምዕዳን እንደ ሚለግሱም እምነቱ አለን፣ ሆኖም እስከ አሁን ድረስ ስለዚሁ ጉዳይ በይፋ የተሰጠ መግለጫ የለም ብለዋል። ውሳኔው የቅዱስ አባታችን ኃላፊነት ነው። የተካሄደው ሲኖዶስ ያጸደቀው የፍጻሜው ሰነድ በሁሉም እንዲታወቅና ለሁሉም እንዲደርስ በሚል ፍላጎትም ቅዱስነታቸው የሲኖዶሱ የፍጻሜው ሰነድ በይፋ ይታተም ብለው ውሳኔ ሰጥተዋል።

ቅዱስነታቸው የሚለግሱት ድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን መቼ እንደሚቀርብም ከወዲሁ ቁርጥ አድርጎ ለመናገር አይቻልም፣ መጠበቅ ነው። በቅርብ እንደሚሆንም ተስፋው አለኝ፣ ምክንያቱም ጊዜ ሲራዘም ሲኖዶሱ ያመለከተው ሃሳብና ውሳኔ የሚኖረው ኃይልና የሚኖረው አወንታዊ ተጽእኖ ሊጐድል ይችላል፣ ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ሐዋርያዊ ምዕዳን የሚያቀርቡ ከሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚሆን ነው ብለዋል።

በመቀጠልም በቅርቡ አንድ የቫቲካን ልኡካን ወደ ፐኪንግ ለጉብኝት መሄዱ ይነገራል፣ ስለ ጉዳይ  ምን ይላሉ የሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ ብፁዕነታቸው ሲመልሱ፦ የተካሄደው ጉብኝትን የተደረገው ውይይት በቅድስት መንበርና በቻይና መካከል ያለው ግኑኝነት ጥንቃሬ እንዲኖረው የሚያደረግ የአንድ ቀጣይ ክወና ክፍል ነው። ስለዚህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተከናወነ ጉብኝትና ውይይት አይደለም ብለው፣ ያስገኘው ውጤት አለ ወይ ከሚለው ጥያቄ ጋር  በማያያዝ ሲመልሱም ተገናኝቶ ለመወያየት መቻሉ ይኽ ለገዛ እራሱ አንድ ውጤት ነው በማለት መልስ ሰጥተው አክለውም በቅድስት መንበርና በቻይና እንዲሁም በፐኪንግ መካከል ያለው ግኑኝነት ቅድስት መንበር ከተለያዩ አገሮች ጋር እንዳላት ጥንቁር ግኑኝነት እንዲኖርም የሚደግፍ እንደሚሆን የሁሉም ፍላጎት ነው። የምንኖርበት ዘመን የተሰኘው የቫቲካን ሁለተኛው ጉባኤ ውሳኔ ዝክረ 50ኛው ዓመት ምክንያት በማድረግ በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ ተሳትፈዋል፣ የተለያዩ ሃይማኖቶች እሴቶች የማስተላለፉ ኃላፊነት አላቸው ወይ ለሚለው ጥይቄ ብፁዕ ካርዲናል ፓርሊን ሲመልሱም ሁሉም ሃይማኖትች በሰላም ግንባታና ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት አቢይ ኃላፊነት አለባቸው፣ ሰላም ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም ከገዛ እራስ ጋር ሰላም ከባለንጀራ ጋር ሲኖር ባካባቢ ሰላም ይኖራል። ስለዚህ የሃይማኖቶች አስታዋጽኦ መሠረታዊ ነው። በተለይ ደግሞ በአሁኑ ወቅት በእግዝአብሔር ስም አመጽ ሲከወንና በእግዚአብሔር ስም የሚፈጸመው ዓመጽ ምክንያታዊ የማድረግ ተግባር የሚታይ በመሆኑም የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች መሪዎች በእግዚብሔር ስም ሰላም እንጂ አመጽ ምክንያታዊ ሊሆን እንደማይችልና በእግዚአብሔር ስም የሚከወነው ዓመጽ ጸረ እግዚአብሔር መሆኑ የማሳወቅ ኃላፊነትና ግዴታ አለባቸው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በቅርቡ አፍሪቃን ይጎበኛሉ በመካከለኛይቱ አፍሪቃ የአል ሻባብ የሌሎች አክራሪያ ሃይሎች መኖር ስለዚሁ ያለው ሁነታ አያስፈራም ወይ ከሚለው ጥያቄ ጋር በማያያዝ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ ሐዋርያዊ ጉብኝት ይፈጸማል ሲባል መፈጸም እንደሚቻል የሚያስተማምን ሁኔታ ስላለ ነው። የምትፈራ ከሆንክ የትም አትሄድም ባለህበት ትቀራለህ። ቅዱስ አባታች ወደ ሁሉም ለመድረስ ፍላጎት እንጂ ፍርሃት የላቸውም ይኽ ኃይል የሚያገኙትም ከእምነት ነው። በዚህ በመካከለኛይቱ ረፓብሊክ አፍሪቃ አገር በሚያከናውኑት ሐዋርያዊ ጉብኝት አማካኝነት በአፍሪቃ ሰላም ያነቃቃሉ፣ ጉብኝቱ በክፍለ ዓለሟ ሰላም ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት አቢይ ድጋፍ ነው በማለት መልስ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ስለ ሚከፈተው የምህረት ቅዱስ ዓመት ምክንያት የተለያዩ ሃይማኖቶች የሚያሳትፍና ተመሳሳይ ጅምሮች በእቅድ ተይዘዋል ወይ? ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱ፣ በርግጥ የሚያውቁት ጉዳይ እንደሌለ ገልጠው፣ ሆኖም በሚቀጥሉት ቀናት የሚታይ ጉዳይ ይሆናል ካሉ በኋላ፣ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በመክሲኮ ስለ ሚያካሂዱት በእቅድ ተይዞ ስላለው ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ርእስ ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፦ ያንን አገር በቅርብ የሚያቁት መሆኑም አስታውሰው ያ ሐዋርያዊ ጉብኝት የዚያች አገር ሕዝብ እምነትና ካቶሊካዊ ባህል የሚያበረታታ እምነት የሚያጸናና የታደሰ ክርስትና እንዲኖር የሁሉም ጥረት የሚያነቃቃ እንደሚሆንም ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.