2015-10-30 15:28:00

ብፁዕ አቡነ አረላኖ፦ ይሴባሕ የቅ. አ. ር.ሊ.ጳ. ዓዋዲ መልእክት ለሁሉም ድንቅ ሃብት ነው


ቅድስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ “ይሴባሕ” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት፦ እርሃብ ለመዋጋትና ጨርሶ ለማጥፋት ብሎም ስነ ምኅዳራዊ ለውጥ የሚያነቃቃ ተቀባይነት ላለው ለልማት እቀድ ለእርሻ ልማት እቀድ መሠረት ነው” በሚል ርእስ ሥር ሮማ የሚገኘው የቅዱስ መስቀል መንበረ ጥበብ፣ ከዓለም አቀፍ የምግብ ድርጅት ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ማኅበር እንዲሁም በዓለም አቀፍ የምግብና የእርሻ ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ሐዋርያዊ ልኡክ በመተባበር ያዘጋጁት ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በጳጳሳዊ የቅዱስ መስቀል መንበረ ጥበብ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ መካሄዱ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመድዮ ሎ ሞናኮ ገለጡ።

ስለ ተካሄደው ዓውደ ጥናት በማስመልከት በዓለም አቀፍ የምግብና እርሻ ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ሐዋርያዊ ልኡክ ብፁዕ አቡነ ፈርናንዶ ኪካ አረያኖ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ዓዋዲ መልእክቱን የሚያነብ አካል ተፈጥሮና ፍጥረትን ለመደገፍ ለመንከባከብ ምን ዓይነት መንገድ መከተል እንደሚገባና ምን ማድረግም እንደሚያስፈልግ ያስተውላል፣ ተፈጥሮንና ፍጥረትን ለመከላከል ከግል ኃላፊነት በመንደርደር ወደ ብሔራዊ ኃላፊነትና ዓለም አቀፋዊ ኃላፊነት የሚሸኝ ምን እናድርግ ለሚለው ጥያቄ መልስ የሚሰጥ እርሃብ ለመዋጋትና ተከስቶ ያለው የተፈጥሮ አየር ንብረት ብከላ እንዲጎድልና እንዳይበክል ምን መደረግ እንዳለበትም የሚመራ ሃሳብ ያስፈረ ዓዋዲ መልእክት ነው። ግለኝነት ስግብግብነት ሌላው እንደጥራጊ ላለ መመልከት የሚደገፈው ስበአዊ ሥነ ምኅዳራዊ ለውጥ የሚያነቃቃ ዓዋዲ መልእክት ነው። የተካሄደው ዓውደ ጥናትም ይኸንን ሓሳብ በተለያየ መልኩ አስምሮበታል ብለዋል።

በመቀጠልም በጳጳሳዊ ቅዱስ መስቀል መንበረ ጥበብ የቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ ትምህርት ሊቅ የዚሁ ትምህርት ዘርፍ አስተማሪ ፕሮፈሰር አርቱሮ በሎክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ይሴባሕ ዓዋዲ መልእክት ተፈጥሮናና ፍጥረትን ለመንከባከብ የሚመራ በዚህ ሂደት ለሰው ልጅ እርምጃም መርህ ነው። ሁላችንን ተለወጡ የሚል ነው። አስተሳሰብ አካሄድ አጠቃቀም ሁሉ ለውጡ የሚል ብቻ ሳይሆን ለመለወጥ የሚደግፍ መንገድ የሚያመለክት ዓዋዲ መልእክት ነው። ስለዚህ እስካሁን ድረስ እርሃብ ለማስወገድ ያላስቸለው ዓለም አቀፋዊ እቅድ እርሃብ እንዳይጠፋ የሚያደርግ ኤኮኖሚያዊ ሂደት፣ ሰው በተፈጥሮ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ያለው አሳሳቢነት የመሳሰሉት ስጋቶች ለማስወገድና የምንከተለው የተሳሳተው የልማት እቀድ ይለወጥ የሚል ብቻ ሳይሆን እንዴት መለወጥ እንዳለበትም የሚመራ ዓዋዲ መልእክት ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.