ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንጻ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ሁሌ ማለዳ መሥዋዕተ ቅዳሴ በማሳረግ የዕለቱ ምንባቦች ተንተርሰው የሚለግሱት ስብከት አንድ ወጥ በማስያዝ ካቶሊካዊ ስልጣኔ ለተሰየመው አንዴ በሁለት ሳምንት ለሚታተመው የኢየሱሳውያን መጽሔት ዋና አዘጋጅ የማኅበሩ አባል አባ አንቶንዮ ስፓዳሮ የቅዱስነታቸው ከመጋቢት 13 ቀን 2013 ዓ.ም. 266ኛው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው የተመረጡበት አንደኛው የቅዱስ ጴጥሮስ ሓዋርያዊ ሥልጣን ዓመት ቅድስት ማርታ ሕንጻ በሚገኘው ቤተ ጸሎት ባሳረጉዋቸው መስዋዕተ ቅዳሴ ያስደመጡዋቸው የአንድ ዓመት ስብከቶች ያካተተ እውነት አንድ ግኑኝነት ነው በሚል ርእስ ስር አንድ ወጥ በማስያዝ ከደረሱት መጽሐፈ ስብከት በመቀጠልም፣ እ.ኤ.አ. ከመጋቢት ወር 2014 እስከ ሰኔ 2015 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው በቤተ ጸሎቱ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ የለገሱት ስብከት ያካተተ ሁለተኛው ተከታታይ መጽሐፈ ስብከት አንድ ወጥ በማስያዝ ያዘጋጁት መጽሐፍ በሪዞሊ ማትሚያ ቤት ታትሞ እ.ኤ.አ. ከ ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ለንባብ መብቃቱ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።
የመጽሐፉ ደራሲ አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሌ ማለዳ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንጻ በሚገኘው ቤተ ጸሎት አንድ በማለት መሥዋዕተ ቅዳሴ በማሳረግ ጀምረው የሚለግሱት አጭር ስብከት በቫቲካን ረዲዮ አማካኝነት በተለላዩ የመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት ጭምር የሚከታተሉ እጅግ ብዙ መሆናቸው አስታውሰው፣ ይኸንን የማለዳው የቅዱስነታቸው ስብከትም “በአፍ የሚነገር የቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርት (በቃል የሚተላለፍ)” በማለት ሰይመው የሚያስደምጡት ወንጌላዊ ስብከት ውነኛ በመሆኑ የሁሉም ልብ በተጨባጩ ሁነት የሚነካ ነው። የተደመጠው የዕለቱ ወንጌል ማእከል በማድረግ የሚቀርብ ረቂቅ ኅልዮ፣ የሥነ ቅዱስ ወንጌል ትምህርት ብቻ ሳይሆን ይኸንን ትምህርት በተጨባጩ ዓለም ተጨባጭ መልእክቱን በስፋት የሚያስረዳ በመሆኑ የሁሉም ልብ የሚማርክ ነው።
የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅድስት ማርታ ስብከቶች ቋንቋ ግጥማዊነትና ሁላቀፍ በመሆኑም ማንም የማይነጥል ሁሉም በቀላሉ ሊረዳው የሚችል ነው። ስለዚህ ወንጌላዊነት ስልት የሚከተል መሆኑ አባ ስፓዳሮ አብራርተው፣ ስብከቶቹን የሚያነብ ሰው በቀላሉ የሚረዳው ቢሆንም ቅሉ ለምሳሌ ኢጣሊያዊ የፍልስፍና ሊቅ ጆቫኒ ረያለ መጽሐፉ እንደ አንድ የላቀ የፍልስፍና መጽሐፍ አድርገው እንዳነበቡት ይናገራሉ፣ ስለዚህ መጽሐፉ ለቲዮሊያዊ ሊቅ፣ ለስነ ማኅበራዊ ሊቅ ለፍልስፍና ሊቀ ወዘተ ለተለያየ የጥናት ዘርፍ የሚቀርብ በተለያየ መልኩ የሚለው ያለው ነው። ባጠቃላይ ቃለ ወንጌል ወቅታዊ የሚያደርግ ስብከት ነው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ያላቸው የቤተ ክርስቲያን ዕይታ (ራእይ) ጭምር የሚገልጥ ነው። በመሆኑም በቃል የሚተላለፈ የቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርት ነው ብለዋል።
ምኅረት የሚል ወንጌላዊ ቃል የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሥልጣናቸው አስረጅ ቁልፍ ነው። ምህረት ሕጋዊ ተግባር አይደለም፣ ይቅር የሚል ነጻ የሚል ሁለትነታንን ይማለውጥ ሕጋዊ ተግባር አይደለም፣ ምኅረት ግኑኝነት ነው። በአንድ ሰው ሕይወት የእግዚአብሔር መኖርና ኅላዌ ነው። ቅዱስ አባታችንም ይኸንን ዓይነቱ ምኅረት ነው በቃልና በሕይወት የሚገልጡት በማለት አባ ስፓዳሮ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።
All the contents on this site are copyrighted ©. |