2015-10-28 15:42:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ በሥነ ባህል የሊቅነት ክቡር ማዕርግ ለብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ ወደ ተሟላ ውህደት ለመድረስ በሚደረገው ጥረት ለሚሰጡት አስተዋጽኦ እውቅና የሚሰጥ ነው


በኢጣሊያ ቶስካና ክፍለ ሃገር በምትገኘው የአፍቅሮተ ዘቤት ካቶሊካዊ እንቅስቃሴ ማእከል ተብላ በምትጠራው በሎፒያኖ ከተማ በሚገኘው የዚህ ካቶሊካዊ እንቅስቃሴ፦ ሶፊያ መንበረ ጥበብ ለቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ለብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ  በሥነ ባህል የሊቅነት የክብር ማዕርግ እውቅና መሰጠቱ  የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጋብሪኤላ ቸራዞ አስታወቁ።

በዚያ የክብር ሊቅነት ማዕርግ እውቅና ለመሰጠት በተካሄደው ሥነ ሥርዓት በምስራቅ ኤውሮጳ የኦርቶዶስ ቤተ ክርስቲያንና የምስራቅ አቢያተ ክርስቲኢያን የበላይ መንፈሳዊ መሪዎች መሳተፋቸው የገለጡት ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ አክለው፣ የአፍቅሮተ ዘቤተ ካቶሊካዊ እንቅስቃሴ ሊቀ መንበር ማሪያ ቮቸ፦ በሁሉም ደረጃ ወደ ውህደት በሚመራው መንገድ አብሮ መጓዝ በሚል ቅዉም ሃሳብ ዙሪያ ንግግር ማስደመጣቸው አስታውቀዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ የተሰጠው የሊቅነት የክብር ማዕርግ ምክንያት በጋራ ወደ ምሉእና ወደ ተጨባጭ ውህደት ታልሞ በውፉይ መንፈስና በጽናት በሚደረገው ጥረት የሚሰጡት አቢይ አስተዋጽኦ እውቅና የሰጠ ነው የሚል ቅዉም ሃሳብ የተሰመረበት ያስተላለፉት መልእክት በተካሄደው ሥነ ሥርዓት መነበቡ ቸራዞ ገለጡ።

ለዚህ የሊቅነት ክቡር ማዕርግ ብቁ ያስባለው ምክንያት አንዱ በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን መካከል ወህደት እንዲረጋግጥ ታልሞ በሚደረገው የጋራው ውይይትና ጥረት ቀዳሚ ሚና ከመጫወትም አልፎ ሰላምና ፍትህ በዓለም ዙሪያ ለማነቃቃት የሚሰጡት የላቀ አስተዋጽዖ የሚል ሲሆን፣ እየሰጡት ላለው አስተዋጽኦ አድናቆትና ክብር የሚገልጥ ማዕርግ መሆኑ ተመልኮቶ ይገኛል ያሉት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ አያይዘው፣ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ የተሰጣቸው የሊቅነት የክብር ማእርግ ለዚያች ለቁስጥንጥንያ የሰማዕታት ቤተ ክርስቲያን መላ ክብር የሚሰጥ መሆኑ የክብር ማዕርጉ ሲቀበሉ ባስደመጡት አስተምህሮ ገልጠው፣ የምዕራብና የምስራቅ አቢያተ ክርስትያን የጋራ ግኑኝነት ታሪክ ተንተርሰው፣ የነበረው ግኑኝነት ቀርቶ መካፋፈል ላይ ተደርሶ እርሱ በእርስ እውቅና ባለ መሰጣጠት ዋሳኔ ሲወጋገዙ መቆየታቸውንም አስታውሰው፣ በዮሓንስ  23ኛ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ አተናጎራ በጋራ ባካሄዱት ለውህደት ባነጣጠረው ግኑኝነት አዲስ ወደ ውህደት የሚመራ ባህል መነቃቃቱንም አስታውሰው፣ ይኽ ደግሞ በጋራ ወደ አንድነት በማቅናት የሚደረገው ጉዞ ያስጀመረ የሁለቱም አቢያተ ክርስቲያን መልካም ፍቃድ ያረጋገጠ ታሪካዊ ሂደት ትውስት ብቻ ሳይሆን ቀጣይነቱም እየተረጋገጠ ነው እንዳሉ አስታውቀዋል።

ብፁዕ ውቅዱስ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ አክለውም አንድነት ውህደትና አንዳዊነት በተሰኙት ቃላት መካከል ያለውን ልዩነት በጥልቀት ተንትነው፣ የውህደት ባህል በብዙኅነት፣ ኅብረ ባህል የሚያከብር የውህደት ባህል መሆኑ ገልጠው፣ ይኸንን ሃሳብም እ.ኤ.አ. መጋቢት 14 ቀን 2008 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የአፍቅሮተ ዘቤት መሥራች ኪያራ ሉቢክ ቅድስት ሥላሴአዊ ቲዮሎጊያ መሠረት በማድረግ የሚከወን ነው ባሉት መሠረተ ሃሳብ እንዳብራሩትም ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ አመለከቱ።








All the contents on this site are copyrighted ©.