2015-10-23 16:12:00

ሲኖዶስ፦ የፍጻሜ ሰነድ አጠናቃሪ ድርገት


የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ እ.ኤ.አ. ከጥር 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በተለይ ደግሞ የሲኖዶስ ውይይት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ከጀምረበት ቀን ወዲህ በእያናንዷ ቀን ብፁዓን የሲኖዶስ አበው ስላካሄዱት ውይይት በማስደገፍ በቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ በተለያዩ የሲኖዶስ አበው ወይንም በአንዳንድ በሲኖዶሱ በታዛቢነት ከተገኙት ውስጥ ተሸኝተው የሚሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እ.ኤ.አ ጥቅምት 22 ቀን 2015 ዓ.ም. በመቀጠል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፦ ብፁዓን አበው የሲኖዶስ በጋራ እንዲሁም በ13 ተናንሽ የውይይት ቡድን በመከፋፈል ባቀረቡት የፍጻሜ ሰነድ ላይ በማስደገፍ 10 አባላት ያሉት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የተመረጠው ድርገት የማጠቃለያ ሰነድ በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ከገለጡ በኋላ፣ ድርገቱ ያጠናቀረው ሰነድ ለሲኖዶስ አበው ጠቅላይ ጉባኤ ቀርቦ ውይይት ይካሄድበታል ቀጥሎም እ.ኤ.አ. ጥቅምት 24 ቀን ከቀትር በኋላ ድምጽ ይሰጥበታል እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ ገለጡ።

አባ ሎምባርዲ አብሯቸው የተገኙትን በህንድ የቦምባይ ሊቀ ጳጳሳት የሲኖዶስ የፍጻሜ ሰነድ አጠናቃሪ ድርገት አባል ብፁዕ ካርዲናል ኦስዋልድ ግራሲያስ፣ የኦቻይና አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የቶንጋ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ሶአነ ፓቲታ ማፊ የሎስ አንጀሎስ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኾሰ ሆራሲዮ ጎመዝን ለጋዜጠኞች አስተዋውቀው እንዳበቁ፣ የሲኖዶስ የፍጻሜ ሰነድ አጠናቃሪው ድርገት ሰነዱን ለማጠናቀቅ ሳይታክት ኃይለኛ ሥራ እያከናወነ መሆኑ አባ ሎምባርዲ ከገለጡ በኋላ በመቀጠል ብፁዕ ካዲናል ግራሲያስ ይላሉ፦

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፣ ድርገቱ የፍጻሜውን ሰነድ በማጠናቀሩ ሂደት ላይ እያለ ምንም’ኳ ድርገቱ ባካሄደው ውይይት ባይሳተፉም ነገር ግን ቤተሰብ ያለው አስፈላጊነት ርእስ ዙሪያ ምክር ለግሰዋ፣ በእውነቱ ድረገቱም ይኽ ጉብኝት ለመታደል ችለዋል፣ እኚህ የቦምበይ ሊቀ ጳጳሳት የፍጻሜው ሰነድ አጠንቃሪው ድርገት የተከተለው ሥልት ላይ በማተኮረ ድርገቱ ለፍጻሜው ሰነድ መሠረት የሚሆነው የብፁዓን አበው ሲኖዶስ ውይይትና እንዲሁም የሲኖዶስ አበው በ 13 ተናንሽ ቡድኖች በመከፋፈል ባካሄዱት ውይይት የቀረበው የፍጻሜ ሰንድ ማሰናጃ በጠቅላላ 700 የሃሳብ የማሻሻያና ማረሚያ ሃሳብ ያካተተ የተረከበው ሰነድ ላይ በመምከር ሰነዱ አንድ ወጥ እንዲኖረው በመወያየት የቀረበው ሃሳብ እንደ ቅዉም ነገሩ በማስቀመጥ ቅደም ተከተል በማስያዝ አጠናቅሮታል። ሰነዱ ለኪነ ቤተሰብ አካላት እንደሚሰጥም ገልጠዋል። ስለዚህ ሰነዱ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ለድምጸ ውሳኔ እንደሚቀርብ ማረጋገጣቸው ኢዛበላ ፒሮ ገለጡ።

የተጠናቀረው ሰነድ ጠቅለል ባለ መልኩ አንድ መቶ ገጽ አዘል ሆኖ በመግቢያው ብፁዓን አበው በቡድን ተከፋፍለው ባካሄዱት ውይይት በፍጻሜው ሰነድ እንዲታከል በማለት ያቀረቡዋቸው ነጥቦች ይካተታሉ፣ ሰነዱን በማስደገፍም የመላ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ( እ.ኤ.አ. ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. ውይይት አካሂዶበታል፣ ስለዚህ መታከል አለበት ተብለው የሚቀርቡት ሃሳቦች በጽሑፍ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም. በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በፊት እርሱም እስከ 2 ሰዓት በፊት ቀደም ብሎ መቅረብ ይኖርበታል) ይኸንን ሁሉ በማካተትም የሲኖዶስ የፍጻሜ ሰነድ አጠናቃሪው ድርገት ከዚህ በመንደርደር መሻሻል የሚገባውን በማሻሻል መታከል የሚገባውን በማከል እ.ኤ.አ. ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ጧት የሲኖዶስ ብፁዓን አበው የቀረበው የፍጻሜ ሰነድ በማስድገፍ ውይይት ካካሄዱበት በኋላ ከቀትር በኋላ ለእያንዳንዱ አንቀጽ ድምጽ ይሰጡበታል፣ ድምጽ የተሰጠበት ሰነድ ይፋ ማድረግና አለ ማድረግም የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ ይሆናሉ እንዳሉ ፒሮ አስታወቁ።

ብፁዕ ካርዲናል ማፊ፦ ሲኖዶስ ቀጣይ ጉዞ ነው

ብፁዕ ካርዲናል ግራሲያስ የሰጡት መግለጫ እንዳጠቃለሉም ብፁዕ ካርዲናል ማፊ፦ ዓለማዊ ትሥሥር የተረጋገጠበት ዓለም የእርስ በእርስ ጥገኝነት ያለው ተጨባጭ ገጽታ ያጤነ ጥንቃቄ የተሞላው ግምገማ ያሻዋል፣ ሲኖዶስ ይኸንን ያስተዋለ ነው። በመሆኑን ለቤተሰብ የቤተ ክርስቲያን ቅርበትና ድጋፍ ለማረጋገጥ ክፍት በሆነ ልብ የሚወያይ ነው። ያም ሆኖ ይኽ ሲኖዶሱ ጉዞ የሚቀጥል ነው። ዓለማዊ ትሥሥር ቡራኬ ብቻ ሳይሆን ተግዳሮትም ጭምር ነው ቤተ ክርስቲያን ይኸንን ጉዳይ ጠንቅቃ የምታውቅ ስትሆን ከዚህ ጋር የተስተትካከለ በሥርወ እምነት ላይ የጸና ሐውርያዊ ግብረ ኖልዎ ለማቅረብ በተለያየ ወቅት በተለያየ ርእስ ሥር ሲኖዶስ ታካሂዳለች እንዳሉ ፒሮ ገለጡ።

ብፁዕ አቡነ ጎመዝ፦ አለ የጾታ ልዩነት የሰው ዘር የመብትና ክብር እኩልነት ለበስ ነው

ብፁዕነታቸው ይላሉ ሲኖዶሱ ስለ ስደተኛ ርእሰ ጉዳይ ትኩረት በመስጠትም ተወያይተዋል፣ ለምሳሌ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ውስጥ 11 የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸ ስደተኞች አሉ፣ ስለዚህ ይኸንን የስደተኛውን ቤተሰብ ቀርቦ መደገፍና ከሚኖርበት ኅብረሰብ ጋር ተቀላቅሎ ለመኖር እዲችል መደገፍ ይኖርበታል። የአንድ አገር መጻኢ በቤተሰብ ላይ የጸና ነው። ስለዚህ ለቤተሰብ ተገቢ ክብርና ትኵረት መስጠት ያስፈላጋል። ሲኖዶሱ የሴቶችና የወንዶች መብትና ክብር እኩልነት በጥልቀት በማብራራት አስምሮበታል፣ ይኽ ደግሞ ሁሉም በእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ ተፈጠረ በሚለው ቃልና ተግባር ላይ የጸና ነው። ከዚህ በመንደርደርም ሲኖዶስ ማኅበረ ክርስቲያን እምነቱን በጥልቀት በመኖር እንዲመሰክረውም ያስገነዝባል ካሉ በኋላ አባ ሎምባርዲ የዕለቱ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዲህ ባለ መልኩ እንዳጠቃለሉ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.