2015-10-21 15:51:00

ብፁዕ ካርዲናል ታግለ፦ ቤተሰብ በደጉ ሳምራዊው ዓይኖች መመልከት


የሲኖዶስ አበው ከሁኑት ውስጥ አንዱ የተለያዩ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበራት የሚያቅፈው የቅድስት መንበር በካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ለሚጠራው ማኅበር ሊቀ መንበር የሲኖዶስ አበው ወኪል ሊቀ መንበር የማኒላ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ታግለ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ግሪክንና መቀዶኒያ በሚያዋስነው ክልል የሚገኘው የስደተኞችና ተፈናቃዮች መጠለያ ሠፈር ጉብኝት መልስ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ እየመከራ ስላለው ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚጠናቀቀው እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ስለ ሚከፈተው የምህረት ቅዱስ ዓመትና በተለያየ ችግር ምክንያት ተገፋፍቶ የበለጠ መጻኢ በመሻት ወደ ኤውሮጳ የሚጎርፈው ስደተኛ ጉዳይ ማእከል በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በቅድሚያ ግሪክንና መቄዶኒያን በሚያዋስነው ክልል ያለው የስደተኞች መጠለያ ሠፈር ለመጎብኘት በመቻላቸው ካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስንና የግብሪ ሄላስ የተሰየመው የተራድኦ ማኅበር አመስግነው ያንን የስደተኞች የመጠለያ ሰፈር የጎበኘኹት እንደ የሲኖዶስ አበው ሳይሆን በካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ባላቸው ኃላፊነት መሆኑ አስታውቀው፣ በዚያ መጠለያ ሠፈር የሚገኙት ስደተኞች ሕፃናት ቤተሰቦች ምንም ነገር የሌላቸው ቢሆኑም በመካከላቸው የሚኖሩት ፍቅር የሚለውጥ ነው ካሉ በኋላ ከዚህ የመግቢያ መልስ ወደ የሲኖዶሱ ሂደት ላይ በማተኮር፦ የቤተሰብ ቁስሎች የምንላቸው ፍች መለያየት የመሳሰሉት ገጠመኞች እንደ ልማድ መመልከት አይገባንም፣ ይኸ የቤተሰብ ቁስል ለገዛ እራሱ አቢይ ሰብአዊ ውጥረትና ግጭት ነው። ቤተሰብ የዓለም ማኅበረሰብ እርሱም የማኅበራዊ የባህላዊና የኤኮኖሚያዊ ጉዳይ መስተዋት ነው። ሲኖዶሱ ስለ ቤተሰብ ሲመክር ይኸንን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ብፁዓን ጳጳሳትና እረኞች ከሕዝብ ጋር ጥምረት እንዲኖራቸው የሕዝቡን ስሜት ኑሮና ሁነት ተካፋይ እንዲሆኑ ይመክራሉ፣ ይኽ ማለት ደግሞ አካላዊ ቅርበት ብቻ ሳይሆን በእምነት አይን በደጉ ሳምራዊው ዓይኖች ሕዝብን መመልከት ማለት ነው። በእረኛው ኢየስሱ ዓይኖች መመልከት። ይኽ ዓይን የወንድም ስቃይ ችግር ምኞች በጠቅላላ ሁነቱን መካፈል የሚል ነው፣ ቅዱስ ጳውሎስ ከሁሉም ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ ሆንሁ ሲል በቃልና በሕይወት እንዳስተማረው መኖር ማለት ነው። ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ይኸንን ነው በቃልና በሕይወት ከብፁዓን ጳጳሳትና እረኞች የሚጠይቁት ብለዋል።

ምኅረት ፍትህ መቆርቆር (የሌላው ስቃይ ተካፋይ መሆን) በእግዚአብሔር ዘንድ ኅብረተ አላቸው፣ አይነጣጠሉም፣ እኛ ሟቾች ስጋ ለበስ ፍጡራን እነዚህ ባህርያት አጠቃሎ ለመኖር ያቅተናል፣ ለማስተዋል ስንል እንለያያቸዋለን፣ ሆኖም በእግዚአብሔር ዘንድ በእምነት ዓይን አንድ መሆናቸው ማስተዋል ይኖርብናል፣ ጌታ ሆይ ማረኝ የሚለው ጸሎት ጌታ ሆይ ፍትሕ አድርግልኝ ራራልኝ የሚል ወደ ጌታ የሚያርግ እረሮ ነው። ስለዚህ እረኛ ይኸንን ጸሎት የሚኖር ነው።

ብፁዕ ካርዲናል ታግለ በተለያዩ ሰባት ሲኖዶች መሳተፋቸው ገልጠው እያንዳንዱ ሲኖዶስ የገዛ እርሱ መልክ አለው፣ በተለያዩ አገሮች የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የምትገኝበት ክልል ባህል ቋንቋ የምትኖር ነች፣ ይኽ ሁሉ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በሚካሄደው ሲኖዶስ ትልቅ ሃብት ሆኖ ይቀርባል፣ ስለዚህ የኢየሱስ ቃል በተጨባጩ ሰብአዊ ሁነት የሚያነበብበት ጉባኤ ነው ብለው፣ በተለያዩ አገሮች የሚገኝ ቤተሰብ የተለያየ ተጋርጦ ያለው ነው። ድኽነት የሥራ እጦት የመሳሰሉት ችግሮችን ጠቅሰው ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ያንን ሕዝብ የሚኖረውን ሕይወት በመኖር ከድኻው ተስፋ መኖርን እምነትን ትማራለች፣ የሰው ልጅ ችግር ለማቃለል የሕዝቡን ሕይወት የገዛ እራስ ማድረግ ግድ ነው። ይኽ ደግሞ የተስፋ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልው ሥር የሚጠቃለል ነው ብለው ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.