እ.ኤ.አ. ጥቅምት 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ በ14ኛው ይፋዊ መደበኛው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ተሳታፊያን ውስጥ በስድስት ብፁዓን ካርዲናሎችና በአምስት ብፁዓን ጳጳሳት ተጅበው በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ለአራት ብፁዓን የቤተ ክርስቲያን ልጆች ቅድስና ማወጃቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አድሪያና ማሶቲ ገለጡ።
አዲሶቹ ቅዱሳን የመንፈሳዊ ጉባኤ ልጆች ደናግል ማኅበር መሥራች አባ ቪቸንዞ ግሮሲ፣ የመስቀል ተከታዮች ደናግል ማኅበር መሥራች የማኅበሩ ጠቅላይ አለቃ የነበሩት ማርያ ዘንጽሕት ድንግል ማርያም፣ እንዲሁም የቅድስት ተረዛ ዘሕፃነ ኢየሱስ ወላጆች ሊዶቪኮ ማርቲና ማሪያ አዘሊያ ጒየሪን መሆናቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሶቲ አያይዘው በብዙ ሺሕ የሚገመተው ከውስጥና ከውጭ በተለይ ደግሞ በብዛት ከስፐይንና ከፈረንሳይ በመጡት ምእመናን ባጥለቀለው አጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው “እራስ ለማስቀደም መራወጥና የኢየሱስ ተከታይነት አይጣጣምም” የሚል ቀዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ ስብከት መለገሳቸው አስታውቀዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አገልግሎት ትህትና እና በኢየሱስ የተገለጠውና የተኖረው መስቀል ላይ ያተኮረው የዕለቱ ምንባባት ላይ ተንተርሰው፣ በአንደኛው ምንባብ ነቢይ ኢሳያስ የእግዚአብሔር አገልጋይ ተክለ ሰብነት እርሱም የተናቀ በሁሉም የተራቀ ለስቃይ የተጋለጠ፣ ተልእኮው የሚሰቃዩትን በጥልቀት ለመረዳት በስቃይ ጎዳና የሚያልፍ የሌሎችን ሸክምና ግድፈት ለማንጻትም የራሱ በማድረግ የሚሸከም ነው በማለት ለይቶ ይገልጥልናል። ኢየሱስ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሕይወቱ ሞቱ በጠቅላላ በአገልጋይነት በሚያልፍ ተልእኮው ለእኛ ድህነት ለመላ ሰው ዘር ከእግዚአብሔር ጋር እርቅ ሆኖልናል።
የሰው ልጅና የደቀ መዛሙርቱ አስተሳሰብ ጭምር ኢሳያስ ከሚገልጠው ተክለ ሰብነት የተለየ ነው። ያዕቆብና ዮሐንስ በመንግሥቱ ለዛውም በቀኙና በግራው ለመቀመጥ ይጠይቃሉ፣ ኢየሱስ የዚህ ዓይነቱ የደቀ መዛሙርት አስተሳሰብና ጥያቄ የሚያናጋ ሌላ እሳቤ ያቀርብላቸዋል። የከበረው ሥፍራ የመቀዳጀቱ ዋስትና ሳያቀርብላቸው እስከ መጨረሻ ድረስ ጸንተው እርሱም በሚጠጣው መራራ ጽዋና በስቃዩና በመስቀል ኅብረት እንዲኖራቸው ይጠይቃቸዋል፣ የእርሱ ጥሪ ያንን ቀዳሚ ለመሆን ሌላውን ለማዘዝ የሚቃጣው ዓለማዊው ፍላጎት የሚያገል በዚያ በፍቅርና በአገልግሎት ጎዳና እንዲከተሉት ነው።
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን በሌሎች እንዲታይ እንዲከበር ሥራው እንዲታይለት ስልጣንና የተሳካ ከፍተኛ ውጤት ለመጨበጥ መራወጥ ከሚለው ምርጫ የተለየ የዚህ ምርጫ ተቃራኒ በሆነ መንገድ እንዲከተሉት ይጠራቸዋል።
ኢየሱስ ያንን ቅቡል የሆነው አመለካከት በክርስቲያን ማኅበረሰብ ሥልጣን አገልግሎት ማለት መሆኑ በሚገልጠው ትምህርት ይለውጠዋል።
ኢየሱስ አስተሳሰባችን እንድንለውጥ ከሥልጣን ጥማት ወደ እራስ ዝቅ ማድረግና ማገልገል ወደ ሚለው ሐሴት እናተኵሩ ዘንድ ይጋብዘናል።
ገዛ እራሱን በቃልና በሕይወት ዋቢ በማድረግ በተምሳሌት ልንኖረው እንደሚገባንም ገዛ እራሱ መሥዋዕት በማድረግ ገልጦልናል። በቅዱስ መጽሐፍ ባህል የሰው ልጅ ማለት ያ ከእግዚአብሔር ሥልጣን ክብርና መንግሥት የሚቀበል ማለት ነው። ኢየሱስ ይኸንን ባህል በሙላት ትርጉሙ በቃልና በሕይወት ምን መሆኑ ገልጦልናል።
“….ኢየሱስ ያለው ሥልጣን አገልጋይ በመሆኑ፣ ክብርና መጎስ ገዛ እርስ ዝቅ በማድረግ መሆኑ፣ የንግሥናው ሥልጣን ሕይወት እስከ መስጠት ባለው ቅሩብነት የሚገለጥ መሆኑ አረጋግጦልናል” በስቃዩና በሞቱ ያንን የመጨረሻውን ሥፍራ በመያዝ ልዕልናው በማገልገል መሆኑም በተግባር በመግለጥ ይከንን የማገልገል ጸጋ ለቤተ ክርስቲያኑ ለግሰዋል።
ስለዚህ በዓለም መመዘኛ በኩል የሚገለጠው ሥልጣንና በትሁት አገልግሎት የሚል በኢየሱስ አብነት የተገለጠው ሥልጣን የማይጣጣሙ ናቸው፣ ጉጉት እራስ ለማስቀደምና የኢየሱስ ተከታይነትነት የማይዛመዱ ናቸው፣ ክብር ቀዳሜ ሥፍራ ገናናነት ምድራዊ ድሎችና የስቁል ኢየሱስ አመክንዮ የማይዛመዱ ናቸው። ነገር ግን የሌላውን ስቃይ የገዛ እራስ በማድረግ መሰቃየትና የእኛ ስቃይ ይሚጣጣሙ ናቸው።
ወደ እብራውያን የተጻፈው መልእክት ኢየሱስ በመኖር የሚገልጠው ክህነት የምህረትና ያዛኝነት የስቃይ ተካፋይነት መሆን ያስታውሰናል፣ የስቃያችን ተክፋይ ብቻ ሳይሆን በቀጥታ የገዛ እራሱ ተመክሮ አድርጎታል፣ ሰው የመሆናችንን ሁነት በጥልቀት ያውቀዋል፣ አለ ኃጢአት በሥተቀረ የሚለው መለያው ኃጢአት በጥልቀት ከማስተዋል አያገለውም፣ የእርሱ ክብርና መጎስ የዚያ የጉጉት የሥልጣን ጥማት ማለት ሳይሆን አለ ሐጢአት በስተቀረ የሰው ልጅ በማፍቀር የሰው ልጅ ሁነት በመካፈል ዳግም የሚፈውሰው ጸጋ የሚሰጥ ነው።
እያንዳንዳችን ምሥጢረ ጥምቀት የተቀበልን፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ክህነት ሱታፌ ያለው በመሆኑ ድልድይ ያደርገናል፣ የፍቅሩ የስቃይ ተካፋይነቱ በተለይ ደግሞ እጅግ በስቃይ በኃዘን በቀቢጸ ተስፋና በብቸኝነት ለሚገኙት ሁሉ ፍቅሩን የሚያገናኙ ድልድይ መሆን ማለት ነው። ለዚህ ተግባርም አዲሶቹ ቅዱሳን ድንቅ አብነት ናቸው፣ ቅዱስ ቪንቸንዞ ግሮሲ ለሁሉም በተለይ ደግሞ በችግር ለሚገኙት ቅርብ በመሆኑ ለእግዚአብሔር ፍቅር ቀናተኛ በመሆን የኖረ ቆሞስ፣ ቅድስት ማሪያ ዘንጽሕት ድንግል ማርያም ድኾችን የታመሙትን በማገልገል የኖረች፣ የቅድስት ተረዛ ዘሕፃነ ኢየስሱ ወላጆች ዕለት በዕለት ቤተሰብ የእምነት የፍቅር ሥፍራ አድርገው በመኖር ገልጠውልናል…በሐሴተኛው ወንድሞችን በማገልገሉ ጥሪ የእግዚአብሔር ድጋፍና የማርያም እናታዊ ጥበቃ ለመታመን ያጽኑን በማለት ያስደመጡት ስብከት እንዳጠቃለሉ ማሶቲ ገለጡ።
All the contents on this site are copyrighted ©. |