2015-10-16 15:44:00

የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም.


የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ እ.ኤ.አ. ከጥር 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በተለይ ደግሞ የሲኖዶስ ውይይት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. በይፋ ከጀምረበት ቀን ወዲህ በእያናንዷ ቀን ብፁዓን የሲኖዶስ አበው ስላካሄዱት ውይይት በማስደገፍ በቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ በአንዳንድ የሲኖዶስ አበው ወይንም በአንዳንድ በሲኖዶሱ በታዛቢነት ከተገኙት ውስጥ ተሸኝተው የሚሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እ.ኤ.አ ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ጧት በመቀጠል ስለ ተፋቱትና ዳግም ስለ ተጋቡት ጉዳይ ሰፊ ውይይት ተካሂደዋል፣ አንዳንዶቹ ስለ ጋብቻ የቤተ ክርስቲያን  ትምህርት ዳግም እንዲጠናቀር የሚሉ ይኽ ደግሞ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሥርወ እምነት ለመጠበቅ በሚል አስተያየት ላይ የጸና ሃሳብ አቅርበዋል። ይኽ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቃል ለመጨመርም ሆነ ለማጉደል ምንም ሥልጣን እንደሌላት ያበከረ ሃሳብ ነው። ሌላው ኢየሱስን በመከተሉ የእምነት ጉዳና ብዙ ሰዎች ቀጣይነት ባለው መንገድ ከቅዱሳት ምሥጢራት ተገለው እንዲኖሩ ማድረጉ አይገባም የሚል ከቅዱስ ቁርባን ተገሎ መኖር አደገኛ መሆኑ የሚያመለክት ሃሳብ ቀርበዋል።

ተፋተው ዳግም ተጋብተው የሚኖሩ ጠቅለል በማድረግ ሳይሆን ሳይሆን የእያንዳንዱ ተፋቶ ዳግም የተጋባው ሁኔት በተናጥል በማጤንና ቀርቦ በመወያየት ወደ ቅዱሳት ምስጢራት ማቅረብ ያስፈላጋል፣ ምክንያቱም በቅዱሳት ምሥጢራት ሱታፌ አድልዎ መኖር የለበትም። ነገር ግን በዚህ የእምነት ጉዞ የመረዳትና የመለየት ችሎታ እንዲበረታ ማድረግ ያስፈልጋል፣ በዚህ የመረዳቱ ሂደት በተመለከተም ብፅዕ ካርዲናል ካስፐር ባስደመጡት ንግግር እንዳሰመሩበትም የጸጸት ወይንም የንስሃ ጉዞ በሚል አገላለጥ ወደ ቅዱስ ቁርባን ሱታፌ ዳግም ድልው ለማለት የአንድ አመት ከግማሽ የዳግመ ሕንጸት እቅድ ማረጋገጥ ያስፈልጋል፣ ስለዚህ የተፋቱት ዳግም ተጋብተው የሚኖሩት በአንድ ላይ ሳይሆን እያንዳንዱ በግል ወደ ቅዱስ ቁርባን ሱታፌ ለማቅረ የሚደገፍ ሕንጸት ያለው አስፈላጊነት የሚያመለከት መሆኑ አባ ሎምባርዲ አስታውቀዋል።

የቤተሰብ ጉዳይ የሚመለከተው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ፣ የቀለም ትምህርት ከሚያስመስለው ቋንቋ ማራቅ ያስፈልጋል፣ የመስተንግዶ አገልግሎት በሚል ስያሜ የቤተሰብ የእርስ በእርስ መደጋገፍ በተለይ ደግሞ በተለያየ ምክንያት የቆሰለው ችግር ያለበት ቤተሰብ በሌሎች ቤተሰቦች የመደገፍ አገልግሎት ያለው አስፈላጊነት የሚያበክር ነው። ምክንያቱም ምሥጢረ ተክሊል በእምነት ተደግፎ ችግሮችን ሁሉ በእምነት ኃይል በመወጣት የሚኖር በችግር ላይ ላለው ቤተሰብ የመደገፍ የማበረታታት ጥሪም አለው፣ ስለዚህ ክርስቲያናዊ ቅዱሳት ምሥጢራት በጥልቀት የመኖር ተመክሮ ማካፈል።

የሥነ ጋብቻ ሕንጸት ሳይሆን በጋራ የእምነት ጉዞ ያለው አስፈላጊነት የሚያረጋግጥ የቤተሰብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ያለው አስፈላጊነት እርሱም የክርስቲያናዊ ጋብቻ ያለው ውበት የሚያጎላ ሕንጸት፣ ተፋተው ከመጡ ወይንም ለመፋታት ከደረሱ በኋላ እንዳይፋቱ ለማድረግ ከሚሰጠው ድጋፍ የቀደመ መሆን አለበት፣ ምክንያት ትዳር ጥሪ ነውና። ስለዚህ የቤተሰብ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ይኸንን ሁሉ ያጠቃለለ መሆን እንደሚገባው ተብራርተዋል።

ቅይጥ ጋብቻ

በኤውሮጳም በአነስተኛ ደረጃ በእስያና በአፍሪቃ በስፋት የሚየው ቅይጥ ጋብቻ፣  በተለይ ደግሞ በምስልምና ሃይማኖት ተከታይና በካቶሊክ ምእመን መካከል የሚኖረ ቃል ኪዳን ርእስ ዙሪያ የመከረው ውሎው፣ አንዱ በሌላው ላይ ተጽእኖ ሳይሆን፣ እምነቱት የመኖር ነጻነት ማረግገጥ አለበት፣ በተለይ ካቶሊካውያን ሴቶች የሌላው እምነት ተከታይ ከሆነው ዜጋ ጋር ተጋብተው ሲኖሩ እምነታቸውን እንዲክዱ ይገደዳሉ፣ ስለዚህ የእነዚህ ካቶሊክ ሴቶች መብት ለማስጠበቅ የተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የጋራ ውይይት ማበረታታት ያለው አስፈላጊነት ተሰምሮበታል።።

በሌላው ረገድም ቅይጥ ጋብቻ በተለያዩ ክልሎች ለተለያዩ ሃይማኖት ለጋራ ውይይት የሚያበረታታ መሆኑም ብፁዓን አበው እንደገለጡ አባ ሎምባርዲ አስታውቀዋል።

ምሥጢረ ተክሊል እንዲፈታላቸው የሚጠይቁ ጉዳያቸው ተመርምሮ በቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤት ይፈታ የሚል ውሳኔ ለመስጠት የሚፈጀው ረዥም ጊዜና የተንዛዛ ሂደት ለማስወገድ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ባላቸው ልዩ ሐዋርያዊ ሥልጣን አማካኝነት እንዲታደስ የሚል ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የወሰዱት ውሳኔ ውሎው በሚገባ የታመነበት ሲሆን፣ ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን ፍርድ ቤት የጋብቻ ጉዳይ የሚከታተለው ቢሮ በሕግና ፍትህ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን አገልግሎታቸው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ገጽታው የሚያጎላ ሕንጸት በሚገባ ማግኘት ይገባቸዋል የሚል ሃሳብ ተስተጋብተዋል።

ለጋብቻ ለሚዘጋጁት እጮኛሞች የሚሰጠው ትምህርተ ክርስቶስ ሕንጸት ከትዳር በኋላ ሊያጋጥም ስለ ሚችል ሁኔታ የሚመለከት ማድረግ፣ ምክንያቱም ከተጋቡ በኋላ ልጅ ለመውለድ ያለ መታደል ሁኔታ ሊያጋጥም ይችላል፣ ባህርያዊ ወይንም ሰብአዊ ጉዳይ የሚመለከት ሊሆን ይችላል፣  ለምሳሌ ለጋብቻ በሚሰጠው ሕንጸት ወላጃ አልባ የሆኑትን ማሳደግ የሚል ሃሳብ ጭምር ያካተተ መሆን እንደሚገባው ብፁዓን አበው አሳስበዋል።

በዚህ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተሳተፉት የፖዝናን ሊቀ ጳጳሳት የፖላንድ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ስታኒስላው ጋደችኪ፦ የተፋቱት በሚገባ የሚሸኝ ሐዋርይዊ ግብረ ኖልዎ ያለው አስፈላጊነት ገልጠው፣ ሲኖዶሱ ለውይይት እየተጠቀመበት ያለው ሰነድ እርሱም ለፍጻሜ ሰነድ የሚያገለግለው ነው፣ በመሆኑም ሰነዱ ዳግም እንዲጠናቀር የሚሉና አይ ሰነዱ የተጠቀመባቸው ቃላት ብቻ ይስተካከል የሚሉም አሉ፣ ሁለቱም ሃሳቦች መሰረታዊ ተምሳይነት እንዳላቸውም አብራርተዋል።

በመቀጠልም በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተሳተፉት በመክሲኮ የትላልነፓትላ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ካርሎስ አጒይር፦ ሲኖዱሱ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባወጁት የምኅረት አመት ሥር መጤን አለበት፣ ይኽ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ተግባር ምን መሆን እንዳለበት የሚገልጥ ቅዱስ ዓመት ነው። ምህረት ለሁሉም የሚለው የእግዚአብሔር ፍቅር ማበሰር፣ ይኽ የእግዚአብሔር እቅድ ነው። የእግዚአብሔር እቅድ በአንድ መንገድ የሚገለጥ ብቻ ሳይሆን በተለይ ደግሞ የሚታዩት ለውጦች ሁሉ ያካተተ ወቅታዊነት ያለው ነው። ስለዚህ ሲኖዶስ ተፋተው ዳግም የተጋቡትን ሳይጋቡ ልጅ የሚወልዱ እናቶች አለ ቃል ኪዳን የሚኖሩ እንዳሉ ግምት የሰጠ ነው፣ በወቅታዊው ሁነት የእግዚብሔር እቅድ ምን ተመስሎውና ትግባሬው ማስተንተን ያስፈልጋል።

የኅሊና ጋብቻ የሚል ሃሳብ ተነስተዋል፣ ይኽ ደግሞ የሕገ ወጥ ስደተኞች ተብለው የሚገለጡት በተለያየ ችግር ምክንያት አገራቸው ጥለው የሚሰደዱት አለ መኖሪያ ፈቃድ በስደት አገር የሚኖሩት ዜጎች የመኖሪያ ሕጋዊ ፈቃድ ስለ ሌላቸው ወይንም ገና በመጠባበቅ ላይ ያሉ፣ ለመጋባት የሚያስፈልገው የማስታወቂያ ወረቀቶች ስለ ሌላቸው ለመጋባትና ቃል ኪዳን ለማሰር የሚይቀርቡት ጥያቄ መልስ ለመስጠት እንዲቻል፣ ይኸንን ጉዳይ እንዴት ባለና በምን አይነት መልኩ ማስተናገድ አለበት ለሚለው ጥያቄ ውሎው የኅሊና ጋብቻ የሚል መፍትሔ እንደሰጠበት አባ ሎምባርዲ ገልጠው የእግዚአብሔር እቅድ እርሱም የፍቅርና የምኅረት እቅድ ነውና በተለያየ መልኩ የሚገለጥ ነው በማለት የተሰጠው ጋዜጣዊ መገልጫ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.