2015-10-12 16:02:00

የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ


የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ ኣባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በመካሄድ ላይ ያለው 14ኛው ጠቅላይ መደበኛ ጉባኤ ሲኖዶስ እ.ኤ.አ. ከጥር 4 ቀን 2015 ዓ.ም. በተለይ ደግሞ የሲኖዶስ ውይይት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ዕለት በዕለት የሚያካሂደው ውይይት በተመለከተ በእያንዳንዷ ቀን  በሲኖዶስ አበው ተሸኝተው የሚሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም. የሶሪያ ማላንካረሲ ስርዓት ለምትከትለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት የህንድ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ባሰሊዮስ ክሊሚስ ቶቱንካልና በቅዱስ የልበ ሲየሱስ ማኅበር ጠቅላይ አለቃ አባ ኻቪየር አልቫረስ ኦሮሪዮን እዛው ለተገኙት ልኡካን ጋዜጠኞች በማስተዋወቅ ቀጥለው፣ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 9ና 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ከምዕራብ ኤውሮጳ ከምስራቅ ኤውሮጳና ከኢጣሊያ የተወጣጡት የሲኖዶስ አበው በብዛት የሚግኙባቸው እንዲሁም ከአፍሪቃና ከመካከለኛው ምስራቅ ከላቲንና ከሰሜን አመሪካ የተወጣጡት የሲኖዶስ አበው ጭምር ያካተተ በጠቅላላ 75 ንግግሮች መደመጣቸው አባ ሎምባርዲ ገልጠው፣ በተካሄደው ውይይት ቤተሰብ በታሪክና በዕለታዊ ሕይወት የቤተ ክርስቲያን ኅላዌ መግለጫ፣ የሰብአዊነት የማኅበራዊነት የቤተ ክርስቲያናዊ ሕይወትና የቅድስና ትምህርት ቤት መሆኑ በስፋት መበከሩ አስታውቀዋል።

የቤተሰብ መንፈሳዊነት፣ እምነት በእለታዊ ሕይወት እንዴት መኖር፣ ይኽ ደግሞ ጸሎት ንባብ ቃል እግዚአብሔር መለኮታዊ ምንባቦች በቅዳሴ መሳተፍ በቅዱስ ቁርባን በሚስጢረ ኑዛዜ የቤተሰብ ሱታፌ የሚል ሲሆን፣ በምስጢረ ተክሊል ዙሪያ የተሟላ ሕንጸት ያለው አንገብጋቢነት ጋብቻ የእግዚአብሔር ጥሪ በመሆኑም ያቤተሰብ የሚመሠረትበት በእግዚአብሔር ፈጣሪነት ሱታፌ የሚኖርበት መሆኑም ብፁዓን አበው በተካሄደው ውይይት አንዳሰመሩበተ አባ ሎምባርዲ ገልጠዋል።

ስለ ቤተሰብ ተልእኮ በዓለምና በቤተ ክርስቲያን ሕይወት እንዲሁም ስለ ምሥጢረ ተክሊል በተመለከተ የሚሰጠው ሕንጸት፣ ጋብቻ ጥሪ መሆኑ በማስገንዘብም ብፁዓን አበው ለሚጋቡት ቅድመ ጋብቻና ከቃል ኪዳን በኋላም ድኅረ ጋብቻ ላይ ያነጣጠረ ቀጣይ የሚሥጢረ ተክሊል ሕንጸት ያለው አስፈላጊነት ቤተ ክርስቲያን በመገንዘብ ለዚህ ተልእኮ ብቃት ያላቸው ካህናት የማሰናዳት ኃላፊነት እንደሚጠበቅባት ገልጠው፣ ቤተ ክርስቲያን አለ ቤተሰሰብ አለ የቤተሰብ ተልእኮ እንዲሁም ካለ የቤተሰብ ሐዋርያዊ ግብረ ማሰብ እንደማይቻልም የሲኖዶስ አበው በአጽንኦት አሳስበዋል።

የእግዚአብሔር ምኅረት፦ በፍቅር በቅርበትና በየዋህነት ነገር ግን ከቤተ ክርስቲያን አንቀጸ እምነት ሳይለይ፣ ምኅረት በቤተሰብ መካከል በባልና ሚስት በወላጆችና ልጆች መካከል መኖር የሚገባው ጥሪ መሆኑ ብፁዓን አበው ገልጠው፣ ቤተ ክርስቲያን በችግር ላይ ያለው ቤተሰብ በተጋቡት ባልና ሚስት መካከል የሚፈጠረው አለ መግባባት በምኅረት ዓይን ቀርባ እንዲፈታ ትደግፋለች፣ ይኽ ደግሞ ምስጢረ ተክሊል የማይፈታ መሆኑ ታምና ይኽንን እውነት መሠረት በማድረግ የምታቀርበው ድጋፍ ነው። ቃል ኪዳን የማይፈታ መሆኑ የሚገልጠው የቤተ ክርስቲያን አንቀጸ ትምህርት የቤተ ክርስቲያን ነቢይነት ባህይር መግለጫ መሆኑም ተሰምሮበታል።

ወንጌልን ማበሰር ሰዎችን በእቅፍ ማስተናገድ እርሱም የእግዚአብሔር ፍቅር መኖር በተለይ ደግሞ በችግር የሚገኙትን መቀበልና ድጋፍ መስጠት የቤተ ክርስቲያን ጥሪ ነው። ይኽ ደግሞ የጌታ ፍቅር የሚኖርና እውነት የሚከተል ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መሆኑ ያሳሰቡት የሲኖዶስ አበው በወንድና በሴት መካከል የሚኖር ፍቅር በምስጢረ ተክሊል የሚመሰከር የማይሻርም መሆኑ ቤተ ክርስቲያን ይኽንን ከጌታ የተቀበለችው እውነት ተከታይ እንጂ የምትለውጠው እንዳልሆነ ብፁዓን ጳጳሳት ባካሄዱት ውይይት ለቡ እንዳሉም አባ ሎምባርዲ በሰጡት ጋዜጣዊ መገለጫ አስታውቀዋል።

ቤተሰብ እምነት በዕለታዊ ኑሮ በሚያገለግልበት ሙያው በተሰማራበት ዘርፍ ሁሉ የሚመሰክር በማኅበራዊ በፖለቲካዊ በኤኮኖሚያዊ ሕይወት ጭምር እምነቱን እንዲመስከር የተጠራ መሆኑ በማስተዋል፣ የሚወለዱ ሕንፃናት በቃልና በሕይወት በእምነት ጉዳይ ላይ የማነጽ ኃላፊነት እንዳለበትም ጭምር ብፁዓን አበው ማሳሰባቸው አባ ሎምባርዲ ገልጠው የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አጠቃለዋል።      








All the contents on this site are copyrighted ©.