2015-10-12 15:58:00

ሲኖዶስ፦ እ.ኤ.አ. የጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ውሎው ጽማሬ


በዚያ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም. የሲኖዶስ አበው በተናንሽ ቡድኖች ተከፋፍለው ባካሄዱት ስድስተኛ የውሎው ጉባኤ በሲኖዶስ ውይይት ማካሄጃ ሰነድ ሁለተኛው ክፍል ላይ ባለው እርሱም “የቤተሰብ ጥሪ የመለየት (የመርዳት) ችሎታ” ርእስ ዙሪያ መወያየታቸው ተገልጠዋል።

ቤተ ክርስቲያን ለዚያ ለቆሰለው ቤተሰብ በእግዚአብሔር ምህረት በእግዚአብሔር ትምህርትና እውነት ፍቅር ቅርብ በመሆን በመደገፍ ለጋብቻ የሚሰናዱትን በአጭር የፈጣን ሕንጸት መርሃ ግብር አማካኝነት ሳይሆን በጥልቀት ተገቢ የምሥጢረ ተክሊል ሕንጸት በማቅረብ፣ ቤተ ክርስቲያን በምሥጢረ ተክሊል ዙሪያ ላለው ተልእኮዋ ታምኝ በመሆን ምህረት የድህነት እቅድ፣ የእግዚአብሔር ፍትሕ ለወደቀው ዳግም በመመለስ ለክርስቶስ የሚያቅፉት እጆች ተደገፎ ለመነሳት እሺ ለማለት እንዲችል የሚል ሲሆን፣ ይኽ ምህረት ለእግዚአብሔር እውነት የሚጻረር ወይንም ከእግዚአብሔር እውነት ጋር የሚጋጭ ሳይሆን የእግዚአብሔር እውነት በትክክል እግብር ላይ እንዲውል የሚያደረግ መሆኑ የተካሄደው ውይይት አስምሮበታል።

ብፁዓን የሲኖዶስ አበው በቡድን ተከፋፍለው ባካሄዱት ውይይት ደጋግመው በሚሥጢረ ተክሊል ዙሪያ የሚሰጠው ትምህርተ ክርስቶስ፣ ጋብቻ ጥሪ መሆኑ የሚያረጋግጥ ስለዚህ የጋብቻ ጥሪ ለሚቀበሉት የሚቀርብ መሆኑ ተስተውሎ ቤተሰብ ለመመሥረት በእግዚአብሔር መጠራትንና የተጠራውም እነሆኝ በማለት መልስ እንዲሰጥ የሚደገፍ ነው። ምሥጢረ ተክሊል ለመቀበል የሚሰናዱትም ቃል ኪዳን የማይፈታ መሆኑ እንዲያስተውሉና ይኽ ደግሞ ክፈሪሃ እግዚአብሔር ጋር የተቆራኘ በእግዚአብሔር ረድኤት የሚፈጸመም በዚህ ጥሪ የእግዚአብሔር ድጋፍ በመሻት ዕለት በዕለት የሚኖር ጥሪ መሆኑ ቤተ ክርስቲያን ማረጋገጥና በዚህ መንገድም ማነጽ ይገባታል። ስለዚህ ሕንጸት ቅድመ ምሥጢረ ተክሊልና ድኅረ ምስጢረ ተክሊል መኖር አለበት፣ ይኽ ደግሞ በሁሉም ሰበካዎች ቁምስናዎች የሚከናወን ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ መሆን እንደሚገባው ብፁዓን አበው ያሳስባሉ።

ብፁዓን አበው ስለ ልጆች ጉዳይ በማስመልከት፣ በአፍሪቃ ልጅ የማትወልድ ሴት የሚደርስባት ማኅበራዊ ሰብአዊ ባህላዊ ችግር እንዲሁም ልጆች በቤተሰብ ውስጥ ያላቸው ሚና ላይ በማተኮር ውይይት በማካሄድ፣ ልጆች የዚያ እጹብ ድንቅ ፍቅር የባልና ሚስት ፍሬ የእግዚአብሔር ጸጋ ለወላጆቻቸው በቃል ኪዳን እንዲጸኑ የሚያስገነዝቡ የተሟላ ሰብአዊ ሕንጸት የሚያስፈልጋቸው ናቸው። እግዚአብሔር ወንድና ሴት አድርጎ በመፍጠር በጾታዊ ስሜት ፍቅር ተሟይ እንዲሆን  በእግዚአብሔር ሰው በመፍጠር ፈቃድ ሱታፌ ያላቸው ናቸው። ለዚህም ትዳር በወንድና በሴት መካከል መሆኑ ቤተ ክርስቲያን ታስተምራለች፣ እንዲህ በመሆኑም ተመሳሳይ ጾታ ባላቸው ሰዎች መካከል ትዳር ብሎ ማሰብና እንዲሁም ከወንድና ሴት ጾታ ውጭ ሌላ ዓይነት ጾታዊ ስሜት አለ መኖሩ ብፁዓን አበው ያስገነዝባሉ።

የምንኖርበት ዓለም በስነ ስብእ ቀውስ የተጠቃ እንዲሁም እግዚአብሔርን ያጠፋ ባህል የሚስፋፋበት በመሆኑም ይኽ ደግሞ የሰው ልጅ ሰብአዊነት ለሚደልዝ ተግባር እንደሚያጋልጥ ብፁዓን አበው በማስተዋል፣ ይኸንን ችግር ለመቅረፍ የሰው ልጅ ውበት በእግዚአብሔር እቅድ የተፈጠረ መሆኑ የማበከር ብቃት ያለው የተሟላ ሰብአዊነት ምኅዳር እጅግ አንገብጋቢ መሆኑ ያመለክታሉ።

እንደ ኢየሱስ ፈቃድ ለመኖር እዲቻል መለኮታዊ ምንባቦች በቤተሰብ እንዲዘወተር ቃለ እግዚአብሒር ማዳመጥ ማንበብ ቤተሰብ ደስተኛ እንዲሆንና ዕለታዊ ለሚያጋጥመው ውጣ ውረድ ለመሻገር ኃይል እንደሚሰጠው ያሳሰቡት ብፁዓን አበው ቤተ ክርስቲያን በበኩልዋም የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ እምነት በማስተማሩ ተግባር ቤተሰብ ወደ ኢየሱስ ቅርብ እንዲሆን ትደግፋለች።

ወላጆች ጥበብ የተካኑ እንዲሆኑ፣ ልጆቻቸው በፍቅር ነገር ግን በጽናት ምክንያቱም የእግዚአብሔር ፍቅር ጽናትና መህረት ማለት በመሆኑ በዚሁ መልክ እንዲያፈቅሩዋቸው ተጠርተዋል፣ ስለዚህ ጥበብ የተካኑ መሆን ይጠበቅባቸዋል። የአብ ፍቅር ጠፍቶ የቀረውን ልጁ ዳግም አቅፎ ለመሳም በሩን ክፈቶ እጆቹን ዘርግቶ የሚጠባበቅ ነው በማለት የሲኖዶስ ውይይት ማካሄጃው ሰነድ ሦስተኛው ክፍል ወደ ሚያመለክተው እርሱም የቤተሰብ ተልእኮ ዛሬ ወደ ሚለው ርእስ በመሸጋገር ለተፋቱት ዳግም ቅዱስ ቁርባን መፍቀድ የሚለው ርእስ ዙሪያ የጦፍ ውይይት ጀምረዋል፣ ይኽ ውይይት ወደ ሰባተኛ ውሎ የሚያሸጋግር ይሆናል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.