2015-10-05 15:11:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መልእክት ለአየር ላንድ ብሔራዊ የሕይወት ቀን


እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን በአየር ላንድ የሚከበረው ብሔራዊ የሕይወት ቀን ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ዕለቱ የሕይወት ሰብአዊ ክብር ለተሟላው ሰብአዊ እድገትና ለአንድ ስለ ጎረቤቱ ለሚያስተውል ሕብረተሰብ መሠረት መሆኑ የሚመሰከርበት ዕለት ነው የሚል ቅዉም ሃሳብ ማእከል በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት እንደ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘአሲዚ እያንዳንዷ ሕይወት የእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑ ተገንዝበን ሕይወትን የምንከላከል ስለ ሕይወት ክብር የምንቆም ሆነን እንገኝ አደራ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ሕይወትን በመንከባከብ ሞት እንደ የምድራዊ ሕይወት ፍጻሜ ማስተዋል

ቅዱስነታቸው ይኽ በአየርላንድ በስኮትላንድና በተባበሩት የእንግሊዝ ግዛት የሚከበረው የሕይወት ቀን ምክንያት የእነዚህ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት አቢያተ ምክር ዘንድሮ “ሕይወት መኮስኮስ ሞትን መቀበል” የሚለው የሚከተሉት መርህ ቃል ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት እንዲከበር የሚያሳስብ ያ በበሽታ እርሱም ገና መድሃኒት ባልተገኘለት በሽታ የተጠቃው ሕይወት ለመኖር ክብር የተገባ እንዳልሆነ የሚሰበከው በስመ አሳቢነት የሚሰበከው ሰው ዕለተ ሞቱ በገዛ እራሱ ኃይል እንዲወስን የሚያበረታታ ጽንሰ ሓሳብ እንዲወገድ የሚደገፍ ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት የተደረሰው የሥነ ሕክምና በሕይወት አድን ጎዳና የሚሰጠው አስተዋጽኦ ቅዱስ አባታችን እውቅና መስጠት ያለው አስፈላጊነት ባስተላለፉት መልእክት አበክረው፣ ይቅድመ ይቆይም ሁላችን ሟቾች ነን፣ ሆኖም ሟችነት፣ ባህርያዊ ሞት ለመሰረዝ ለሚያደርግ የሞት ባህል መሣሪያ ሆኖ እንዳይገኝ የህይወት ባህል በመመስከር ሁሉም እንዲቃወምው አደራ፣ ሕይወትን እናፈቅራለን፣ እያንዳንዷ ሕይወትም ጸጋ ነች ብለዋል።

ቤተሰብ ለእርስ በእርስ መደጋገፍና መረዳዳት የተገባ ብቁ ሥፍራ ነው

የሕይወት ባህል ለማረጋገጥ ያለው የላቀው ክብሩን ለማስተጋባትና ለማሳመን ቤተ ክርስቲያን ከሥነ ሕክምና ሊቃውንት ጋር ብቻ ሳይሆን መድሃኒት በማይገኝለት በሽታ የተጠቃ ቤተሰዎች ጋር ጭምር ቀርባ መወያየትና ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት መሠረትጋዊ አመክንዮ ማቅረብ ይገባታል እንዳሉ የቅድስት መንበር  መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.