2015-10-02 15:42:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ በልባችን ውስጥ በኑባሬ ያለው እግዚአብሔርን የመናፈቅ ባህርይ አናጥፋ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሌ ማለዳ እንደተለመደው በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 1 ቀን 2015 ዓ.ም. በመቀጠል፦ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርቲያን ቅድስት ተረዛ ዘሊሰ የምታከብርበት ቀን መሆኑ በማስታወስ፣ የዕለቱ ከመጽሓፈ ነህምያ ምዕ. 8 ከቁጥ 1-12 እንዲሁም ከሉቃስ ወንጌል ምዕ. 10 ከቁ. 1-12 የተወሰደውን ምንባብ ተንተርሰው፣ የእስራኤል ሕዝብ በባቢሎን ከረዥሙ የስደት ዓመታት ተላቆ ወደ እየሩሳሌም ተመለሰ። ያ ሕዝብ በስደት አገር እያለ እግዚአብሔርን አልራሳም። ከረዥም ዓመታት በኋላም ወደ እስራኤል ዳግም ይመለሳል። እየሩሳሌምንና ቤተ መቅድስንም መገንባት ይጀምራል፣ ነሕሚያ ጸሐፍቱ እዝራ ለሕዝበ እስራኤል የሕግ መጽሓፍ ያነብ ዘንድ ይጠይቀዋል። ህዝቡም ቃለ እግዚአብሔር በሰማ ጊዜ የእግዚአብሔር ሕግ ሲነበብለት እጅግ በኃሴት በመሞላቱ ያነባ ነበር።

የእግዚአብሔር ሐሴት ኃይላችን ነው

ያ በስደት ይኖር የነበረው ሕዝብ ወደ አገሩ ተመልሶ ከተማውን የተወለደባት ከተማና የእግዚአብሔር ከተማ ብቻ አይደለም ያገኘው፣ ያ ህዝብ የእግዚአብሔር ቃል ሲነበብለት ሳለ ከመለያው ጋር ነው የተገናኘው፣ ለዚህም ነው ቃሉን ሲሰማ ያነባ የነበረው። ከማንነት መለያው ጋር ነው የተገናኘው።

በሐሴት ያነባ ነበር፣ ምክንያቱም ከእውነተኛው መለያው ጋር ተገናኝተዋልና። በስደት አገረ እያለ አጥቶት ከነበረው እየጠፋ ይሄድ ከነበረው ከእውነተኛው መለያው ጋር በመገናኙት ምክንያት በደስታ ያነባል። እትተክዙ የእግዚአብሔር ሐሴት ኃይላችሁ ነውና ይላል ነሕሚያ፣ እውነተኛው መለያችን ጋር ስንገናኝ የምንኖረው ሐሴት እግዚአብሔር የሚሰጠው ኃይል ነው። እኛ በጉዞ ያለን ሕዝቦች ያንን መለያችን እናጣለን፣ ደስታችን በጌታ ቤት ሳይሆን በተለያየ ሁነት እንሻለን፣ ነገር ግን ውዶቼ መለያችን ጌታችን ነው ብለዋል።

በእግዚአብሔር ብቻ ነው መለያችን የሚገኘው

እንዴት ባለ ሁነትና መንገድ ነው መለያችን ጋር የምንገናኘው? መለያህን ቤትህን ያ ያንተ የነበረው ሁሉ ስታጣ በውስጥህ ያጣኸውን ሁሉ በማስታወስ በናፍቆት ትሰቃያለህ። አዎ ይኽ የመናፈቅ ባሃርይ ወደ ቤትህ ትመልስ ዘንድ ይገፋፋሃል። የእስራኤል ሕዝብ ያ በውስጡ የነበረው ናፍቆት ነው እንዲያነባ ያደረገው። በደስታ ያነባ ዘንድ አደረገው፣ ስለዚህ የዚህ ዓይነቱ ናፍቆትም የእግዚእብሔር ጸጋ ነው። የተትረፈረፈ ምግብ ሲኖረን፣ መራብን አናውቅም፣ እርሃብ በእኛ ውስጥ አይኖርም፣ ሁሉ የተደላደለልን የተመቻቸልን ስንሆን ባለንበት የተረጋጋን ስንሆን ወደ ሌላ ስፍራ ለመሄድ አይቃጣንም፣ ሁላችን ገዛ እራሳችንን “የተመቻቸልኝ የተደላደለልኝ ነኝ ለምንም ነገር ፍላጋ አልወጣም” እንላለን ወይ በማለት እራሳችንን እንጠይቅ፣ በመንፈሳዊነት አነጋገር ይኸንን የምለው፣ በልቤ ውስጥ የምፈልገው ምንም ነገር የለምን? በውስጤ በኑባሬ ያለው የመናፈቁ ባህርይ ጠፍቷል ወይ? የእስራኤል ሕዝብን ተመልከቱ በደስታ ያነባ ነበር። ናፍቆት ያጠፋ ልብ ያ እውነተኛ ኃይላችን የሆነውን የእግዚአብሔር ሐሴትን አያውቅም፣ የመናፈቅ ባህርይ ያጠፋ ልብ በዓል የማያደርግ ይሆናል።

ያ በልባችን ውስጥ በኑባሬ ያለው እግዚአብሔርን የመናፈቅ ባህርይ አናጥፋ

ያ ሕዝብ ተገልጦነት የነበርው ቃል ዳግም በሰማ ጊዜ በደስታ ያነባ ነበር፣ ያ በውስጡ የነበረው ወደ ፊት እንዲል ይገፋፋው ከነበረው እግዚአብሔር የመናፈቅ ባህርዩ ጋር ይገናኛል፣ ያ በልባችን ያለው ጌታን የመናፈቁ ባህርይ እባካችሁ እናጥፋ…. በማለት ያስደመጡት ስብከት እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.