2015-10-02 19:35:00

ስደተኞችን በሚመለከት ጉዳይ ግድየለሽነትና ዝም ማለት አይገባም! ር.ሊ.ጳ


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እፊታችን  ጥር 17 ቀን 2016 ዓም እ.ኤ፣አቆ. “ስደተኞችና ተፈናቃዮች እየጠየቁን ነው! የወንጌልና የምሕረት መልስ” በሚል ርእስ ለሚዘከረው ዓለም አቀፍ የስደተኛና ተፈናቃይ ቀን የጻፉት መልእክት ይፋ ሆነ፣ ቅዱስነታቸው በዚሁ መልእክት “ስደተኞች ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ናቸው፤ ከድህነት ረሓብና ጭቆና በመሸሽ የበለጠ ሕይወት ለማግኘት ነው ፍላጎታቸው” ሲሉ ከገለጡ በኋላ “በመፍለስ የሚገኙ ስደተኞች ጉዳይ በተለያዩ የአለም  ማእዘናት በቀጣይነት እያደገና እየጨመረ እንደሚሄድ አስታውቀዋል። የምሕረት ወንጌል ዛሬ ከምን ግዜም በበለጠ ሕሊያችንን እንድንጸጸትና የሌሎችን መከራና ችግር እንደዘልማድ መቀበሉ አስቸጋሪ መሆኑን አመልክተዋል።

ቅዱስነታቸው በማያያዝ በተለያዩ የአለም ዙሪያዎች በብዙ ሚልየን የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት ለስደተና ለመከራ መጋለጡ ለአለም አቀፍ ማኅበረሰብ የእርዳታ ጥሪን ሲያቀርቡ በተለይም በአብዛኛው አለማችን ብዙዎች ስደተኞችን ለመቀበል የማይፈልጉና የስደተኞች ችግርና መከራ ስሜት የማይሰጣቸው መሆኑን በማስታወቅ ይህም ትክክል አለመሆኑን ገልጠዋል። በስደተኞች ላይ በሚከሰተው አመጽ መከራና ችግር ግድ የለሽነትና ጸጥ ማለት የሚከፍተው በሌላ መንገድ የኛ በስደተኞች መከራ ችግርና ሞት መተባበር መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ስደተኛ በሚያልፍባቸው የስደት ጉዞዎች ከተለያዩ ተግዳሮች የሚጋፈጠና ለተለያዩ ችግሮች የተጋለጠ መሆኑን በመጥቀስ በዚህ ሁሉ መከራና ችግር ተፈትነው በማለፍ የተሻለ መጻኢ ለማግኘት ነው፣ይህ ሁሉ ለአስቸኳይ እርዳታና መስተናገድ የግድ ቢለንም ለመብቶቻቸውና ጌድየታዎቻቸው ልዩ ትኵረት በመስጠት እንድንቀበላቸውና ከኅብረተሰቡ እንዲዋሃዱ ማድረግ ሲሆን ዋነኛው ግን ይህንን ፍልሰት የሚያስከትል ምንድር ነው ብሎ መጠየቅም የግድ ይሆናል፣ እያንዳንዱ ስደተኛ ማንነቱን እስከሚነኩ ሁኔታዎች ሊለውጥ ይገደዳል፤ ይህም ወዶ ሳይሆን ሳይወድም ነው፣ ይህ ግዳጅ ተቀባዩ ኅብረተሰብንም ስለሚመለከት እኛ ተቀባዮቻቸውም ልንለውጣቸው ያለብን ነገሮች አሉ፣ በማለት ስደተኞችንና ተፈንቃዮችን የሚቀበሉ ማኅበረሰቦች በበኩላቸው መቻቻልና አብሮ መኖርን የሚመስሉ ከአስቸኳይ እርዳታ ባሻገር ያሉ ጉዳዮችንም መመለከት እንዳለበት አሳስበዋል፣

ስለዚህ ይላሉ ቅዱስነታቸው! ስለዚህ እነዚህን ለውጦች እንዴት አድርጎ ወደ ጥቅም ማዋል ማለት ለእድገትና ለአብሮ መኖር ዕንቅፋት ሳይሆን ዕድልና አጋጣሚ አድርገን እንድንጠቀምባቸው፣ ይህን ለማድረግ ደግሞ የዘረኝነትና መለያየት አደጋዎችን አስወግደት በምሕረት ወንጌል በመመራት ከየትም ይምጡ የወንድሞቻችንና የእኅቶቻችን እረኞች ነን በማለት በቍምስናም ይሁን ሌሎች አከባቢዎች ስደተኞችንና ተፈናቃዮችን እንደ ችግር ፈጣሪዎችና ሰላማችን እንደሚያደፈርሱ ሳይሆን እንደወንድሞቻችን ልንቀበላቸው! ሰጪዎች እኛ ብቻ ሳይሆን እነርሱም የሚለግሱንልን ብዙ ነገር ስላለ ለመቀበልም ዝግጁ መሆን አለብን ከሁሉ በላይ ደግሞ እያንዳድንዱ በክብር እንዲኖር እንዲሁም ለአገሩ ብልጽግና እንዲያበረክት ከመሰደድ ይልቅ በአገሩ የመኖር መብት አለው የሚለው መሪ ሓሳብ ቤተክርስትያንም እንደምትደግፈው በመግለጥ ቤተክርስታይን የተቸገረውን ለመቀበልና ለመርዳት በመጀመርያ ስትሰልፍ እላይ የተጠቀሰው በክብር የመኖር መብትና በአገር የመኖር መብትም እንደምተከላከለው ገለጠዋል፣ 








All the contents on this site are copyrighted ©.