2015-09-28 16:35:00

ቅዱስ አባታችን እረኞች መሆን


የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ፊላደልፊያ በሚገኘው ቅዱስ ካርሎ ቦሮመዮ በሚጠራው የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት በሚገኘው ቅዱስ ማርቲኖ ደ ቶውር ቤተ ጸሎት በስምንተኛው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ ተሳታፍያን ብጹዓን ጳጳስት ጋር ተገናኝተው ምዕዳን ለግሰዋል።

በለጋ እድሚያቸው ጌታ ለመንፈሳዊና ሰብአዊ ጥበቃና እንክብካቤ ባስረከባቸው ሕፃናት ላይ አንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት የፈጸሙት ዓመጽና የተፈጸመባቸው ዓመጽ ጥሎባቸው ያለፈው ሰብአዊና መንፈሳዊ ጉዳት ሁሌ ያሳድደኛል፣ ስቃያቸው በልቤ ተቀርጾ ነው ያለው። እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ያነባል። የዚህ ዓይነቱ አሰቃቂው በደል ኃጢአትና ወንጀል በዝምታ የሚታለፍ አይደለም፣ ተበዳዮቹ ዛሬ መኃሪያን ሆነው ሲገኙ ማየቱ በእውነቱ ለቤተሰቦቻቸውና ለገዛ እራሳቸው ለእያንዳንዳቸው በትህትና ቀርበን አብረን በሕጻናት ላይ የሚፈጸመ የወሲብ አመጽ የሚዋጋው በክርስቶስ ትግል እናግል። ይኸንን የምላችሁ ከእናንተ ጋር ከመገናኘቴ ቀደም በማድረግ በለጋው እድሜያቸው ባንዳንድ የዘርአ ክህነት አባላት የወሲብ አመጽ ሰለባ ከሆኑት በብፁዕ አቡነ ቻፑት ከተሸኙት ጋር በመገናኘቴም ነው ብለዋል።

ይኽ በልቤ ውስጥ ያለው ሃሳብ የሚካሄደው ስምንተኛው የቤተሰብ ጉባኤ ያለው ሃሴት ላይ እንዳስተውል ስላደረገኝና ከእናንተ እረኞች ጋር ልካፈለው ስለ ወደድኩኝ ነው።

ቤተሰብ ለቤተ ክርስቲያን አጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ሳይሆን የእግዚአብሔር የበለጠው ፍጥረት የእግዚአብሔር ቡራኬ ማረጋገጫ ነው። ስለ ቤተሰብ ጸጋ በሁሉም ክልል ከምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ምስጋና ይቅረብ።

አለ ቤተሰብ ቤተ ክርስቲያንም ባልጸናች፣ መሆን የሚገባት ለመሆን ባልቻለች ነበር፣ የመላ ሰብአዊ ዘር የውህደትና የአንድነት ትእምርት ባልሆነች። ክርስቲያን ከሚኖርበት ሁነትና ከሚያጋጥሙት ለውጦች የተለየች አይደለችም፣ በዚህ ሁነት የጌታን ቃል ለማበሰርና ለማገልገል ተጠርተናል ስለዚህ ወቅታዊው ሁነት ማስተዋል ያስፈልጋል።

ማኅበራዊ ቅዋሜዎች ከቅዱሳት ምስጢራት ጋር የተጣመሩ የሚስማሙ ነበሩ። ይኽ ግን ያለፈ ታሪክ ነው። አሁን ነገሮች ተቀይረዋል እንዳለፈው አይደለም። ባንድ ወቅት ያንድ አካባቢ ወይንም ያንድ ሰፈር ሰው ይተዋወቅ ነበር መተማነንም ነበር ይኽ መተማመንም በደንበኛና በተናንሽ የሰፈር ሱቆች መካከል ይኖር ነበር፣ አሁን ግን እንዲህ አይደለም። አለ መተማመን ላይ የጸኑ አበይት የንግድ ማእከሎች ከባለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ እየተስፋፉ ናቸው። ይኽ ደግሞ የፍጆታነት ባህል የሚያንጸባርቅ ነው። በሰው መካከል ያለው ግኑኝነት ሰውን ግድ የማይል ግኑኝነት፣ አጠገብህ ያለው በደንበኛነት ዓይን ብቻ መመልከት እንጂ ታሪኩ መልኩ ግድ አለ መስጠት፣ መሆን ሳይሆን ሰው በተጠቃሚነቱ በፍጆታ ዓይን መለየት የተለመደ ሆነዋል።

ወጣቶች የዚህ ባህል ልጆች በመሆናቸው ወጣቱን በደፈናው ማውገዝ አይገባም፣ ከእረኞቻቸው ያለፈው ጊዜ እንዴት የበለጠ ነበር የሚል ቃል የሚሰሙ መሆን አይገባቸው። አገልጋይና እረኛ መሆን ማለት ቤተ ክርስቲያን ተልእኮዋ ከገዛ እራሷ ውጥታ በሁሉም ስፍራ በሁሉም ሁነት አለ ምንም ማግለል ማበሰር የሚል ነው። አለ ምንም ልዩነት ለሁሉ ህዝቦች።

ወጣቱን የሚያገልና ቤተሰብ እንዳይጸና የሚያደርግ ባህል እየተስፋፋ ነው። በአንደኛ ደረጃ ቤተሰብ ለማጽናት በቂ ቁሳዊ ሃብት ስለ ሌለው በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ብዙ ቁሳዊ ሃብት እንዲኖርህ ብቻህ መሆን ነው የሚል ባህል ጠቅሰው። አነዚያ ሁለት ጉዳዮችም ቤተሰብ ከመመሥረት ያግዳሉ።

… ወጣቱ በሚስጢረ ተክሊል ባህል ማነጽ፣ ታሪክ የሚለወጥ ቤተሰብ ነው። አገልጋዮች እረኞች በተስፈኛንትና በጋለ መንፈስ ቃለ እግዚአብሔር ማበሰር፣ ዘወትር የነቁ እረኞች እንዲሆኑ ይጠበቅባቸዋል። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከዚህ ጋር በማያያዝም ደቀ መዛሙር ድቁና እንዲኖር ያደረጉት የነበሩበት ጊዜ በማስተዋል ነው። በመንፈስ ቅዱስ ተነቃቅተውም ድቁናን አጸኑ፣ ምክንያቱም ሁሉን ነገር ለብቻቸው ለመፈጸም ሰብአዊውና ግኡዛዊው ብቃትና አቅሙም አልነበራቸውም በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ ድቁናን አጸና። ግብረ ሓዋርያት ምዕ. 6 ቁ. 4 ያለውን ቃል እናስታውስ። አንድ አቡን በቅድሚያ እረኛ ነው። የሚጸልይ አብሳሪ ነው ሁሉም ከዚህ በኋላ የሚመጣ ነው ብለዋል።

ቤተሰቦችን የሚያገል አለ ቤተሰብ ይቀራል። አለ ቤተሰብ መቅረት እንዴት ያስፈራል። አንድ መልካም እረኛ ለብቻው አይቀርም። መልካምነት ለብቻ አያስቀርም፣ ሁሉም በዙሪያው ይስባልና። ማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 19 ቁ. 12 ስለ መንግሥተ ሰማያት ብለው ሳያገቡ የሚኖሩ አገልጋዮች እንዳሉ ይገልጥልናል። አነዚህ አገልጋዮች ብቸኞች አይደሉም። ለብቻቸው የሚቀሩ ማለት አይደለም። ሕዝበ እግዚአብሔርን የሚመሩ ናቸው። ገዛ እራሳቸውን መምራት የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል። … ያች አምስት ባሎችዋ ያልሆኑ ወንዶች የነበሩዋት ሳምራዊቷ ሴት ለመመስከር በቅታለች እርሷንና ቀራጮች እናስብ … ብለው እግዚአብሔር ይስጥልኝ በማለት ያስደመጡት ቃል አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.