2015-09-28 16:30:00

ቅዱስ አባታችን በዋዜማ ጸሎት ከቤተሰቦች ጋር


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. መስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም. በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ሰዓት አቆታጠጠር ልክ ከምሽቱ 7 ሰዓት ተኩል ፊላደፍልያያ በሚገኘው በበንጃሚን ፍራንኪሊን ፓርክዋይ ስለ ቤተሰብ ባረገው የጸሎት ዋዜማ ተሳትፈው መሪ ቃል ለግሰዋል።

ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ ውድ ቤተሰብ የሚል የሰላምታ ቃል መግቢያ በማድረግ በለገሱት ምዕዳን፦ ሕይወታቸው ለማካፈል እዚያ የተገኙትን ቤተሰቦችን ሁሉ በማመስገን፣ የቤተሰቦች ምስክርነት ማዳመጥ እንዴት ደስ ያሰኛል። ልብን የሚነካ ነው። የእነርሱ የቤተሰብ አባላት በሚያደርግ መንፈስ የሚያቀርቡት ምስክርነት ማዳመጡ አንድ ቤተሰብ ለመሆናችን የሚያረጋግጥ ጸጋ ነው ብለዋል።

ስለ ፍቅር ገዛ እራስ ማሳለፍ ቀላል ተግባር አይደለም፣ ምክንያቱም እንደ ጌታ እራስ ማሳለፍ በመስቀል የሚያልፍ ሊሆን ስለሚችል ነውና። በመስቀል ማለፍ ለኢየሱስ ክርስቶስ ጭምር ቀላልና አቋራጭ መንገድ አልነበረም። ቅዱስ አባታችን በሥራ እጦት በመሳሰሉት በተለያዩ ችግሮች የተጠቁትን አቢያተ ሰቦችን በማሰብ። ጨለማ ሁሉ ከባድ ሲሆን፣ ወላጆች ለልጆቻቸው ዕለታዊ እንጀራ ሳይዙ እቤት ሲገቡ … መጠለያይ የሌላቸው አቢያተ ሰቦች … ጤና ጥበቃ የማግኘት መብትና ክብር የተነፈጋቸው፣ ስቃያቸውና የሚኖሩት የሕይወት ከበድ መልስ ሳያገኙ የሚኖሩ ቤተሰቦችን እናስብ።

ለቤተሰብ ተገቢ ሥፍራ የማይሰጥ ኅብረተሰብ ማሰብ የማይቻል ነው። ዛሬም እግዚአብሔር ስለ ቤተሰብ የሚቆረቆር ኅብረተሰብ እንዲጸና ያልማል። የሰው ልጅ የመሬትና የሰው ልጅ ሥራ ውጤት የሆነው እንጀራ በሁሉም ቤት ለሁሉም የሚል ነው። ስለዚህ አለ ዕለት እንጀራ የሚኖር ቤተሰብ እንዳይኖር የጌታ ፍላጎት ነው።

ፍጹም የሚባል ቤተሰብ የለም፣ ይኽ ደግሞ ተስፋ ሊያስቆርጠን አይገባውም፣ ባንጻሩ ፍቅር በሕይወት የምንማረው የሚኖር ዕለት በዕለት የሚያድግ ነው። በሁሉም ውጣ ውረድ ውስጥ ፍቅር የሚወለድና የሚጎለበት ነው። ፍቅር ለዚያ ግጭት የመደምደሚያ ቃል ለሚያደርግ ቤተሰብ የሚቻል ነው። ስለዚህ ቤተሰብ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው የሚለው እውነት የሚኖርበት ነው። ችግር ስቃይ መከራ ሁሉ፣ ገዛ እራሳችንና ሌሎችን ወደ እግዚአብሔር ለማቅረብ የሚያነቃቃ መንገድ መሆኑ ቅዱስ አባታችን አብራርተዋል።

ዛሬ እዚህ እንደ ቤተሰብ ስለ ቤተሰብ ለመጸለይ መሰብሰባችን ይላሉ ቅዱስነታቸው የቤተ ክርስቲያን ፈገግተኛውን ደስተኛውና ሁሉን ተቀባይ ፊቷ ለማስተጋባት ነው። የሰውን ልጅ ለማዳን ገዛ እራሱ ሰው ሆኖ ለመምጣት ቤተሰብ ከመረጠው እግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ነው እዚህ ያተሰበሰብነው። በመካከላችን ካለው ከእግዚአብሔር ጋራ እንጂ ከገዛ እራሳችን ጋር ለመገናኘት አይደለም እዚህ ያለነው፣ በማለት ያሰመጡት ምዕዳን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.