2015-09-28 16:38:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፊላደልፊያ የሚገኘው የጸባይ ማረሚያ ቤት ጎበኙ


በቅድሚያ በወህኒ ቤቱ የሚገኙትና የወህኒ ቤቱ ሰራተኞችና የመስተዳድር አባላት ላደርጉላቸው አቀባበል አመስግነው እስረኞቹ የሚኖሩት ከባዱ ሕይወት እስረኞችን ብቻ የሚነካ የሚመለከት ሳይሆን የእስረኞች ቤተሰቦች ጭምር የሚኖሩት የሕይወት ገጠመኝ ነው። ከዚህ አልፎም ለማኅበርሰብ ጭምር የሚመለከት መሆኑ ያብራሩት ቅዱስ አባታችን፣ ወደ ወሁኒ ቤቱ የመጡትም እንደ እረኛና እንደ ወንድም መሆኑ ገልጠው፣ የእናንተን ሁኔታ ለመካፈልና የገዛ እራሳቸው ተመክሮ ለማድረግ በመሻት እዛው እንደትገኙም አብራርተዋል።

ኢየሱስ ቁስላችንን ሊፈውስ ይፈልጋል፣ ካለ መታከት ይፈልገናል፣ እግሮቻችንን እጆቻችንን ብቸኝነታችንን ሊፈውስ በላያችን ላይ ያለው እድፍ ለማስወገድ በመሻት ሊገናኘን ይፈልጋል። እድፋችንን አስወግዶ ዳግም ሰብአዊ ክብራችንን ሊያለብሰን ወደ እኛ ይመጣል።

መኖር መራመድ በአቧራ መቆሸሽ በታሪክ አቧራ መቆሸሽ ያጠቃልላል፣ ይኽ ደግሞ ሁላችን መንጻት እንደሚያስፈልገን ያስገነዝበናል። ሁሉችን በጌታ የምንፈለግ ነን። ለጌታ ሁላችን ምርጦቹ ነን። ጌታ የሁላችንን እግር ሊያጥብ በእርሱ ማእድ ዙሪያ እንቀመጥና እንመገብ ዘንድ ይሻል፣ ይኸንን መሻት በቃልና በተግባር ፈጽሞታል። ሁላችንን እንጂ የተለዩ ምርጦችን የሚሻ ጌታ አይደለም።

በዚህ ማረሚያ ቤት ቆይታችሁ ለለውጥና ለእርስ በእርስ መደጋገፍ የምትሰለጡኑበት ጊዜ በማድረግ አሳልፉት፣ እናንተ ብቻ ሳትሆኑ ሁላችን የመንጻት ጊዜ ያስፈልገናል። እኔ መንገድ እውነትና ሕይወት ነኝ ያለው ጌታ ሕይወትን በሙላት እናጣጥም ዘንድ ያድርገን የእርሱ የፍቅር ኃይል የትንሣኤው ኃይል ዘወትር አዲስ ሕይወት ይሁንልን።

ጌታ እንዲባርከን እንለምነው። በእያንዳንዳችን ገጽ ብርሁ መልኩ እንዲበራ ያድርግ፣ ጸጋውን ይስጣችሁ፣ ሰላሙን ይስጣችሁ ብለው… ላደረጉላቸው አቀባበል አመስግነው ተሰናብተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.