2015-09-28 16:22:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ፦ ለወንድሞቻችን ቦታ እንሰጣለን ወይ?


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም. ነው ዮርክ ከሚገኘው ጳጳሳዊ መንበር ተሰናብተው በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በፊት ልክ 9 ሰዓት ተኩል ፊላደልፊያ በሚገኘው ዓለም አቀፍ ያየር ማረፊያ በፊላደልፊያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቻርለስ ጆሰፍ ቻፑት በፐንስይልቫኒያ አስተዳዳሪ ቶም ዎልፍና በፊላደልፊያ ከንቲባ ሚካሄል ኑተር አቀባበል ተድርጎላቸው በቀጥታ ካሊፎርኒያ ወደ ሚገኘው ካቴድራል ተዛውረ ልክ 10 ሰዓት ተኩል የፐንስይልቫኒያ ብፁዓን ጳጳሳት ውሉደ ክህነት ገዳማውያን ያሳተፈ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው በለገሱት ስብከት፦

ቅዱስ ኣባታችን በቅድሚያ የተነገራቸው የሚያስደንቅ የፊላደልፊያ ካቴድራል ግንባታ ታሪክ የቤተ ክርስቲያን ልጆች የከተሞች ጥጋ ጥግ ክልሎች የአምልኮ ሥፍራ እንዲኖራቸው ለሕንጸት ለፍቅር ለማኅበራዊ አገልግሎት የሰጡት አቢይ አገልግሎት የሚመሰክር ነው ብለው። በዚህች ከተማ የሚገኙት ቁምስናዎች አቢያተ ክርስቲያንቾ በማኅበረሰባችን መካከል የእግዚአብሔር ኅላዌ የሚናገሩ ናቸው፣ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ካህናት ደናግል ዓለማውያን ምእመናን ከሁለት ዘመና በፊት በዚህ ሥፍራ የሰጡት ወደር የማይገኝለት አገልግሎት ለእግዚአብሔር ያለህ ፍቅር አምሳያህን በማፍቀር የሚኖር መሆኑ መስክረውታል። ዛሬ በዚያ ክልል ያለችው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የዚህ አቢይ መንፈሳዊና ሰብአዊ ኃብት ውራሽ ለመሆት የታደለች ነች ብለዋል።

ቅዱስነታቸው የዚያ ክልል ልጅ የሆነቸው ቅድስት ካተሪን ድረክሰል ከር.ሊ.ጳ. ሊዮነ አስራ ሦስትሰኛ ጋር ተገናኝታ ቅዱስ አባት ልኡካን ያስፈልጋሉ ብላ ስትጠይቃቸው፣ አንቺስ ምን እያደረግሽ ነው? በማለት የሰጧውት ጥበበኛው ጥያቄአዊ መልስ፣ ምንኛ እንዳነቃቃት ያስታወሱት ቅዱስ አባታችን የተሰጣት መልስ በመከተል ካለ መታከት ተልእኮዋን ፈጸመች፣ ይኽ አተንስ አንቺስ የሚለው ጥያቄ ለሁላችን የሚመለከት ነው። እንደ ቅድስት ካተሪን ለክርስቶስና ለቤተ ክርስቲያን ያለን ፍቅር በእኛ ውስጥ መልካም ፈቃድ በላቀ አስተንፍሶ ርህሩህ ለጋስ በሆነ መንፈስ በቃልና በሕይወት እንዲኖር ያነቃቃናል። ለወንድሞቻችን ቦታ እንሰጣለን ወይ? ለመደገፋቸው ቀድመን እንገኛለን ወይ? ለጌታ ያለን ፍቅር በደስታና ለጌታ ለማገልገል በተነቃቃ በተጋ መንፈስ ተካፍለን እንኖራለን ወይ?

ወቅታዊው የቤተ ክርስቲያን ተግዳሮት በእያንዳንዱ ምእመን በቤተ ክርስቲያን ተልእኮ የመሳተፍ ኃላፊነት መንፈስ ማጎልበት የሚል ነው።

አንተስ የሚለው ጥያቄ በእናንተ ውስጥ ጌታ ላነቃቃው ጥሪና እናንተም በለጋሳነት እነሆኝ በማለት ለሰጣችሁት መልስ ጌታን አመሰግነዋለሁ።

የሚካሄደው ዓለም ዓቀፋዊ ስምንተኛው የቤተሰብ ጉባኤ ለቤተሰብ ስለ ምንሰጠው አገልግሎት እንድናስተነትን የሚደግፍ ነው፣ ስለ ቤተሰብ ትጸልዩ ዘንድ አደራ። በተለይ ደግሞ ለወጣት ትውልድ መልስ የምንሰጥበት መንገድ ነውና አደራ ከዚሁ ጋር በማያይዝ በሚቀጥለው ወር ቤተ ዙሪያ ስለ ሚካሄደው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ አደራ ጸልዩ ብለዋል።

በአመሪካ ስለምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ደስታ ተስፋና ኃይል ወደ አለም ታደርስ ዘንድ በነቢያው ምስክርነት እንድታድግ ቅድስት ድንግል ማርያም ታማልድልን፣ እርስ በእርሳችን በጸሎት እንተሳሰብ አደራ ስለ እኔ ጸልዩ በማለት ያስደመጡት ስብከት አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.