2015-09-25 19:21:00

ር.ሊ.ጳ በኒው ዮርክ - በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጽ/ቤት


የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አስረኛው ዓለም አቀፋዊ ሓዋርያዊ ዑደት በተባበሩት መንግሥታት እጅግ ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ እየታከሄድ እንዳለና በሁሉም መስክ አመርቂ ውጤትና ተቀባይነት እያሳየ መሆኑ አብሮዋቸው እየተጓዙ ያሉ የቅድስት መንበር የኅትመትና ዜና ኃላፊና እንዲሁም የቫቲካን ረድዮ ጠቅላይ ኃላፊ ገልጠዋል፣ትናንትና በዋሺንግተን ዲሲ በተባበሩ የአመሪካ መንግሥታት ቤተ መንግሥት ንግግር በማድረግ በቅዱስ ፓትሪክ ቍምስና የሚረዱ ቤት አልባዎችን ጎብኝተው ከአንድሪው ወታደራዊ አየር ማረፍያ ተነሥተው በጆን ኤፍ ከነዲ የኒው ዮርክ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ በሰላም ገቡ፣ የትናንትና ዋና ዋና ዜናዎች ከዚህ ዜና በኋላ እናቀርብላችኋለን፣

ቅዱስነታቸው ትናንትና በኒው ዮርክ ሰዓት አቆጣጠር አስራሰባት ሰዓት ላይ በጀይ ኤፍ ከነዲ ዓለም አቀፍ አየር ማረፍያ ሲደርሱ የኒው ዮርክ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ዶላን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ ሊቀ ጳጳሳ አቡነ በርናርዲቶ እና የብሩክሊን ጳጳስ የኒው ዮርክ ከንቲባ የሚገኙባቸው ባለሥልጣኖች ሲቀበልዋቸው ወዲያውኑ በሄሊኮፕተር ወደ ማሀል ከተማ ተጉዘዋል፣ በማንሃተን ከሚገኘው የሄሊኮፕተር ማረፍያ ወደ ቅዱስ ፓትሪክ በመኪና ተጉዘዋል፣ እንደልማዳቸውም የዚሁ ስምንት ኪሎሜትር ጉዞ ግማሽ በክፍት ማኪና ሆነው ሕዝቡን ሲባርኩና ሰላምታ እያቀረቡ ወደ ካተድራሉ ሲደርሱ ብፁዕ ካርዲናል ዶላንና የካተድራሉ ኃላፊ ተቅብልዋቸዋል፣ በካተድራል ውስጥ ይጠባበቅዋቸው ከነበሩ አንዳንድ ሕመምተኞችና ቤተሰቦች ሰላምታ ከተለዋወጡና ከባረኩ በኋላ እቅፍ አበባ በመንበረ ታቦት አኑሮው በቅዱስ ቍርባን ፊት የግል ጸሎት ካሳረጉ በኋላ ከመላው ውሉደ ክህነት ካህናት ደናግል ገዳማውያንና ገዳማውያት እንዲሁም ምእመናን ጋር በካተድራሉ መዘመራን ተሸንተው የጸሎተ ዘርክ መዝሙረ ዳዊት ደግመዋል፣

ከቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት “በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።” (1ጴጥ 1፤6) በሚለው ቃል ተመርኵዘው የሚከተለውን ስብከት አቅርበዋል፣

 “ወንድሞቻችን ሙስሊሞች በሚመለከት ሁለት ስሜቶች ይፈራርቁብኛል፣ አንደኛው ዛሬ ዕለት የመሥዋዕት በዓል ዒል አድሃ ስለሚያከብሩ የሞቀ ሰላምታየን ለማቅረብ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በመካ ዛሬ ባጋጠመው አደራ ለተጉዱ ወገኖቻቸው ቅርበቴን ለመግለጥ ነው፣ አሁን በዚህ ጸሎታችን ሁሉ ቻይና መሓሪ የሆነ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው አብረን እንለምናለን፣ አሁን ሓዋርያ የሚለንን “ምንም እንኳ አሁን አጠር ላለ ግዜ ብዙ ፈተና ቢገጥማችሁ እጅግ ደስ ይበላችሁ!” እነኚህ ቃላት አንድ መሠረታዊ የሆነ ነገር ያሳስቡናል፣ የእኛ ጥሪ በደስታ እንድንኖር ነው፣ ይህ እጅግ ቆንጆ የሆነ የቅዱስ ፓትሪክ ካተድራል በብዙ ሴቶችና ወንዶች መሥዋዕት ከረዥም ዓመታት በኋላ የተገነባ የካህናት ደናግልና ምእመናን ሥራ ምሳሌ በመሆን እነኚህ ሰዎች የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ቤተ ክርስትያንን ለመገንባት ምን ያህል እንዳበረከቱ ያሳየናል፣ ብዙ ጀግኖች መንፈሳውም ይሁን ቍሳዊ እርዳታ ለማበርከት እስከ መሥዋዕትነት እንደደረሱም የማይዘነጋ ነው፣ ለምሳሌ ቅድስት ኤልሳቤጥ አና ሰቶን የመጀመርያ ነጻ ትምህርት ለዚህ አገር ልጃገረዶች እንደከፈተች እንዲሁም ቅዱስ ዮሓንስ ኒውማን ለመጀመርያ የካቶሊክ ትምህርት ቤት የክፈተ ሊጠቀሱ ይቻላል፣ እዚህ የመጣሁትም ከእናንተ ካህናት ገዳማውያንና ገዳማውያት ጋር አብሮ ለመጸለይ ሲሆን ምክንያቱም ጥሪአችሁ ታላቁን የእግዚአብሔር መንግሥት በዚህ አገር መገንባት እንድትቀጥሉበት ነው፣ ብዙ እንደተሳቀያችሁ አውቃለሁ፣ በአንዳንድ ወንድሞቻችን ባቈሰሉትና በሰጡት ዕንቅፋት በዮሓንስ ራእይ እንደሚለው “ከታላቅ መከራ የመጣችሁ ናችሁ” (7፡14) እላችኋለሁ፣ በዚሁ የሥቃይና ከባድ ጊዜ እጐናችሁ ሆኜ እሸኛችኋለሁ እግዚአብሔርንም በምትሰጡት አገልግሎት አመስግናለሁ፣ በማለት ስለአጠቃላይ ሁኔታቸው ከተናገሩ በኋላ ለአስተንትኖ እንዲረድዋቸው ደግሞ ከሁሉ አስቀድመው የምስጋና መንፈስ እንዲኖራቸው በተለይ መጀመርያ የተጠሩበት ሁኔታ በትምህርታቸው ያደርጉት ጉዞ ወዘተ ስለብዙ ነገር ማመስገንና ዘወትር እግዚአብሔር ያደረገላችውን ማስታወስ እንዳለባቸው፥ በሁለተኛ ደረጃ ድግሞ ልባቸው ጌታን ለማገልገል የሥራ መንፈስ እንዲሞላበትና ሁሌ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነው እንዲገኙ፣ ይህ ሁሉ ሲያደርጉ ደግሞ ከመስቀል የመሸሽ ፈተና እና ቅናት እንዳያሸንፋቸው አደራ በማለት ስብከታቸውን ደምድመዋል፣

እንደገና ስለመላው ዓለም ጸሎተ ም እመናን ቀርቦ ብፁዕ ካርዲናል ድናልድም ምስጋና አቅርበው ሓዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው በመጡበት አግባብ ወደ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቀዋሚ ታዛቢ መኖርያ ቤት ሄደው የራትና የዕረፍት ግዝያቸው እዛ አሳለፉ፣

ዛሬ ጥዋት በኒው ዮርክ ሰዓት አቆጣጠር ስምንት ሰዓት ተኵል በከተማው በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጽሕፈት ቤት ሄደዋል፣ የጽሕፈት ቤቱ ዋና ጸሓፊ የሚገኙባቸው ብዙ ሰዎች ተሰልፈው ተቀብለዋቸዋል፣ ከሕጻናት የአበባ ጉንጉን ተቀብለው ከተሰለፉ ሰዎች አንዳንዶቹ ከባረኩና ሰላም ካሉ በኋላ ከዋና ጸሓፊው ኮፊ አናንና ተባባሪዎቻቸው ጋር መጀመርያ በግል ተገኛኙ፣በመቀጠልም ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች የሚከተለውን ንግግር አድርገዋል፣

ውድ ጓደኞች እንደምን አደራችሁ! በዚሁ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉብኝቴ ሁላችሁን አመስግናለሁ፣ ላደረገላችሁኝ ደማቅ አቀባበል እንዲሁም ይህ እውን እንዲሁን ለዝግጅቱ አመሰግናለሁ፣ ሰላምታዬን ዛሬ እዚህ ለመገኘት ላልቻሉ ለቤተሰቦቻችሁና ለጓደኞቻችሁ አቅርቡልኝ፣

በዚህ ሕንጻ ከሚሠራው አብዛኛው ለዜናና ለወሬ የሚሆን አይደለም፣ ነገር ግን ብዙ ዲፕሎማስያዊ ባህላዊ ምጣኔሃብታዊና ፖለቲካዊ ግኑኝቶች እውን የሚሆኑት እናንተ በምታበረክቱት ጥረት ነው፣ ለዚህም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ፣ ሲሉ ስለጠንቃቃ ስራቸው አመስግነው ለሚመጣ ከመጭነቅ ይልቅ ዛሬውኑ አንዱ ለሌላው እንዲያስብና እርስ በእርሳቸው እንዲቀራረቡና እየተረዳዱ ድርጅቱን እንደአንድ ቤተሰብ እንዲገነቡት ለሰላምና ለፍትህ መሥራት ብቻ ሳይሆን በሰላምና በፍትህ መንፈስ እንዲሠሩ አደራ ብለዋል፣ በመጨረሻም ሁላቸውንን አመስግነው ለእነርሱና ለቤተሰቦቻቸው እንደሚጸልዩ ቃል ገብተው እነርሱም ስለቅዱስናቸው እንዲጸልዩ የማያምኑም ካሉ መልካም እንዲመኙላቸው አደራ በማለትና በቡራኬ ንግግራቸውን ከፈጸሙ በኋላ በድርጅቱ ሥር ከሚያገልግሉ በዚህ ዓመት በተለያዩ ቦታዎች የሞቱትን ለማስታወስ የአንድ ደቂቃ ጸጥታ ከተጠበቀ በኋላ ከመላው ዓለም ተሰብሰበው የሚገኙ የመላው ዓለም መሪዎቻችና ተወካዮቻቸው በሚገኙበት የድርጅቱ አደራሽ ሄድዋል፣ በቦታ የነበሩ በጭብጨባ ተቀብለዋቸውል፣ የድርጅቱ አፈጉባኤ

“ዛሬ ጥዋት የድርጅታችን የታዛቢ አባል የሆነች የቅድስት መንበር ኃላፊ የካቶሊካዊት ቤትክርስትያን ር.ሊ.ጳጳሳት ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮስን እናዳምጣለን፣ ካሉ በኋላ መልካም ምኞታቸውን ገልጠው ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን እንዲሁም ር.ሊ.ጳ በዓለማችን ስለምታበርከተው ዘርዝረው መድረኩን ለድርጅቱ ዋና ጸሓፊ አስተላልፈዋል፣ ኮፊ አናንም በበኩላቸው “እንደተባበሩ መንግሥታት ድርጅት እርስዎም ሌሎችን ለመርዳት የተገፋፋችሁ ነዎት” በማለት ሌሎችን ከመርዳት ጀምሮ እስከ የአክባቢ እንክብካቤ ያደረጉትን አስተዋጽኦ በመዘርዘር ምስጋናቸውን ካቀረቡ በኋላ “ቅዱስ አባታችን እንኳን ደህና መጡ ቃላችሁን ለመዳመጥ ዝግጁ ነን እጅግ አመሰግናለሁ” ካሉ በኋላ አፈጉባኤው እንደገና በማመስገን ቅዱስነታቸው ለጉባኤው ቃላቸውን እንዲያሰሙ ጥሪ አቅርበዋል፣ ቅዱስነታቸውም ይህን ቃል ሰጥተዋል፣

“የተከበሩ ፕረሲደንት! ክቡራትና ክቡራን! እንደምን አደራችሁ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ ር.ሊ.ጳ ለዚሁ ለተከበረው የአገሮች ጉባኤ ቃል እንዲሰጡ ባቀረቡት ጥሪ መሠረት እንደልማዳችን እንደገና ቃሌን ለመስጠት እዚህ ስገኝ ታላቅ ክብር ይሰማኛል፣ በስሜናና በመላዋ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ስም ለተከበሩ ባን ኪሙን ልባዊ ምስጋናየን ለማቅረብ እወዳለሁ፣ ደስ ለሚያሰኘው ንግግራቸውም ላመሰግናቸው እወዳለሁ፣ በመቀጠልም እዚህ የሚገኙ የመንግሥታት መሪዎችን አምባሳደሮችን ዲፕሎማቶችንና እሳቸውን ሸኝተው ለመጡ ፖሎቲከኞችና ተክኒኮች እንዲሁም በዚሁ ሰበኛው አጠቃላይ ጉባኤ ለሚገኙና ሁሉንም የዚህ ድርጅት ሠራተኞች እና ሁሉንም ከድርጅቱ ጋር የሚተባበሩትን ሁሉ አመሰግናለሁ፣ በእናንተው አማካኝነትም የመላው ዓለም አገሮች ነዋሪዎችን ሰላምታየን ለማቅረብ እወዳለሁ፣ ለመላው ዘመደ አዳም በጎ ነገር ለምታደርጉት ጥረት ሁሉ አመስግናችኋለሁ፣

ር.ሊ.ጳ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሲጐበኝ የዛሬው አምስተኛ ነው፣ ከእኔ በፊት የነበሩ ብፁዕ ጳውሎስ 6ኛ በ1965ዓም ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ በ1979 እና በ1995 እንዲሁም ልሂቅ ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በ2008 ዓም ጐብኝተው ነበር፣ ሁላቸውም የዚህ ድርጅት ቁምነገርና አበርክቶ በማንኛውም ታሪካዊ ጊዜ ሕጋዊና ፖሎቲካዊ መፍትሔ እያፈላለጉ የቦታ ርቀትና ድንበሮች ተሻግሮ ብዙ እንዳበረከተ ገልጠዋል፣ ተክኖሎጂካዊ ሥልጣን በተሳሳቱ አገራዊ ርእዮተ ዓለሞችና የውሸት አለም አቀፍ እጆች የገባ እንደሆን ስንት ጥፋት እንደሚያስከትል ግልጽ ነው፣ ከእኔ በፊት የነበሩ ጳጳሳት የተናገሩትን ከመድገምና ድጋፌን ከመግለጥ እንዲሁም ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በዚህ ድርጅት ያላትን እምነትና ተስፋ አስፈላጊነት እንደገና ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፣” ሲሉ መግብያ ካደረጉ በኋላ የድርጅቱ ሰባኛ ዓመትን በማስታወስ የተገኙ ድሎችን በማድነቅ በዚሁ ሰባ ዓመታት ውስጥ ብዙ መሥዋዕትነት በመክፈል ታላቅ አበርክቶ ላደረጉ ሁሉ አድናቆታቸውን ገልጠው ስለአጠቃላይ የዓለማችን ሁኔታና ከድርጅቱ ለሚጠበቁ በተለይ ውግያ ረሃብ ስደትና አከባቢን በተመለከተ ሰፊ ንግግር አድርገዋል፣

ከዚህ በመቀጠል በግራውንድ ዜሮ የሚታወቀው በመስከረም 11 በመንታ ሕንጻዎች ውድመት የሞቱት ማስታወሻ በመገኘት ከሌሎች የሃይማኖት መሪዎች ጋር ጸሎት አሳርገዋል፣ አሁን ፕሮግራማችን በሚተላለፍበት ሰዓት ለምሳ ወደአደሩበት እየተጓዙ ነው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.