2015-09-23 16:37:00

ቅዱስ አባታችን፦ በርህራሄና በፍቅር አብዮት እናምናለን


ቅዱስ አባታችን ከቅዳሴው ስነ ሥርዓት ፍጻሜ በኋላ የግልና የጽሞና ጸሎት አሳርገው እንዳበቁ ልክ በኵባ ሰዓት ኣቆጣጠር እኩለ ቀን ከ20 ደቂቃ ወደ ኦልጊን መንበረ ጳጳስ ሕንጻ በመሄድ እዛው ምሳ ተቋድሰውም ከሰበካው ጳጳስ ተሰናብተው ወደ ሎማ ደ ላ ክሩስ እርሱም የመስቀል ኮረብታ ተብሎ ወደ ሚጠራው 261 ሜትር እርዝማኔ ያለው ቅዱስ መስቀል ወደ ቆመበት ሥፍራ በመሄድ ከዚያ ኮረብታማ ሥፍራ ሆነው ጸሎት አሳርገው ኦልጊን ከተማን ባርከው እንዳበቁም ከኦልጊን አየር ማረፊያ ተነስተው ሳንቲያጎ ከተማ ልክ በኵባ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ አምስት ሰዓት ተኩል ሳንቲያጎ ደ ኩባ በሚገኘው ኣንቶኒዮ ማቸኦ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ ደርሰው ቅዱስነታቸውን ለመቀበል እዛው ከተገኙት የከተማይቱ የመንግሥት አካላት ጋር ሰላምታ ተለዋውጠው ሕፃናት ያቀረቡላቸው መዝሙር አዳምጠው ሁሉንም ማመስገናቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ በማያያዝ የሳንቲያጎ ደ ኩባ ሊቀ ጳጳስ በጓንታናሞ ደሴት በተወለዱት ኩባዊ ብፁዕ ዲዮኒሲኦ ጉይለርሞ ጋርሲያ ኢባኘዝ ሓዋርያዊ ኖልዎ ሥር የሚመራ መሆኑ በማስታወስ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሳንቲያጎ ደ ኩባ ወደ ሚገኘው ቅዱስ ባዚሊዮስ ኣቢይ አዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት ሕንፃ ከኵባ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጋር ልክ በኵባ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ሰባት ሰዓት ተገናኝተው ሰባት ሰዓት ከ 45 ደቂቃም ከኩባ ብፁዓን ጳጳሳት ጋር በሁባሬ በዘርአ ክህነት ተማሪዎች ቤተ ጸሎት ወደ ፍቅርተ ማርያም ዘኮብረ ጸሎት ማሳረጋቸው አስታውቀዋል።

ቅዱስነታቸው በኵባ ሰዓት አቆጣጠር ልክ ከጠዋቱ ሰባት ሰዓት ተኩል ከቅዱስ ባሲሊዮስ አቢይ የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ሕንፃ ተሰናብተው ከጠዋቱ 7 ሰዓት ከ 50 ደቂቃ ሳንታይጎ ደ ኵባ ወደ ሚገኘው በ ፍቅርተ ማርያም ዘኮብረ ቅዱስ ሥፍራ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ከ ቆላሲያ ምዕ. 3 ክቍጥር 12 እስከ 17 እንዲሁም ከሉቃስ ወንጌል ምዕ. 1 ከ ቁጥር 39 እስከ 55 የተወሰደውን የዕለቱ ንባብ አስደግፈው የእምነት አብዮት የሌላውን ስቃይ መካፈል ስለ ሚሰቃየው ማሰብ የሚል የርህራሄ አብዮት ነው በሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ ስብከት መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ ገለጡ።

የሚያንቀሳቅሰው እግዚአብሔር ነው

እውነተኛው እምነት የሚያንቀሳቅስ ነው። ቅዱስነታቸው የዕለቱ ወንጌል እርሱም ማርያም ቅድስት ኤልሳቤጥን ልትጎበኛ ሄደች የሚለውን ቃል ጠቅሰው በሕይወታችን የምንቀበለው የእግዚአብሔር ህላዌ እንዲሁ ረግቶ ለመቆም ሳይሆን እንድንቀሳቀስ ይገፋፋናል፣ እግዚአብሔር ሲጎበኘን ከቤታችን እንድንወጣ ያደርገናል። እንጎበኝ ዘንድ ይጎበኘናል፣ እንገናኝ ዘንድ ይገናኘናል። ማርያም ለማገልገል ከቤትዋ ወጥታ ትሄዳለች፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው የሚለው እምነት የሚያነቃቃው ደስታ፣ ልብን የሚያነቃቃ እግሮቻችን እንዲራመዱ የሚያደርግ ደስታ እንድንካፈል የሚያነቃቃ ነው። ማርያም መጎብኘትን መሸኘትን ትኖራለች፣ ስንት ሕዝብ በተለያየ ችግር በሚገኝበት ወቅት ከለላ ሁናለች፣ እየሆነችም ነው። የልጆቻቸው ሰብአዊ መብትና ክብር ለመከላከል የሚታገሉት ቤተሰቦች ከለላ ሁናለች።

በኵባ በአያቶች የታቀበው እምነት

የኵባ ሕዝብ እ.ኤ.አ. በ 1916 ዓ.ም. የአገሪቱ ጠባቂ ቅድስት ተባላ በር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 15ኛ የታወጀችው የፍቅር ማርያም ዘኮብረ ፍቅር አክብሮት ያደገች አገር ነች። ይኽ አክብሮት ለማርያም ያች ትንሽ የቅድስት ማርያም ዘኮብረ ቅዱስ ሓወልት እ.ኤ.አ. በ1600 ዓ.ም. በተገኘችበት ዘመን የተጀመረም ነው። ይኽ ቅዱስ ሥፍራ የዚያ ለእግዚአብሔር ታማኝ የሆነው የኵባ ሕዝብ የእምነት ተዘክሮ ኅያው የሆነበት ሥፍራ ነው። በጉዞአችን እንዳንጠፋ የእምነታችን አናስርና መለያችን የታቀበበት ሥፍራ ነው። የኵባ ሕዝብ እምነት ስቃይና ማጣት አላናወጠውም።

በርህራሄና በፍቅር አብዮት እናምናለን

በእያንዳንዷ ቀን እይታችን ወደ ማርያም ስናቀና በዚያ የርህራሄና የፍቅር ኃይል አብዮት እናምናለን፣ እንደዚያች የፍቅር እናት የሆነችው ማርያም ያንን የፍቅርና የርህራሄ ኃይል አብዮት እንድንኖር ተጠርተናል፣ አይኖቻችንና ልቦቻችንን ለሌችን ክፍ ለማድረግ ከቤታችን እንወጣም ዘንድ ተጠርተናል።

የእኛ አብዮት በፍቅር በርህራሄ በደስታ ለሌላው ቅርብ በመሆን የሌላው ስቃይ በመካፈል የሚያልፍ ነው። ለማገልገል የሚገፋፋ ኃይል ነው።

ተስፋና እርቅ ለመዝራት ከመቅደሶችዋ የምትወጣ ቤተ ክርስቲያን

እምነት ከቤታችን ወጥተን ከሌሎች ጋር ለመገናኘት በመገናኘትም ደስታና ስቃይ ተስፋና የህሙማን የእስረኞች ጭንቀት እንድንካፈል የሚያደርግ ኃይል ነው።

እንደ ማርያም የምታገለግል ከጓዳዋ የምትወጣ ቤተ ክርስቲያን ለመሆን ነው የምንፈልገው። ከመቅደሶችዋ የምትወጣ ሌሎችን የሚሰቃዩትን በተስፋ ለመደገፍ የአንድ ክቡር የተገባ ሕዝብ ውህደት ትእምርት ለመሆን ቤተ ክርስቲያን ከጓዳዋ እንደ ማርያም ለመውጣት ተጠርታለች።

ሕዝቦቻችን ቅር በተሰኘበትና በመሰናክል ሁነት መደገፍ

መውጣት ለሌልው ቅርብ መሆን የሚል ነው። ቤተ ክርስቲያን እንደ ማርያም ያንን በአደጋና በመሰናክል ሁነት የሚገኝ ሕዝባችንን ለመሸኘት ለመደገፍ የተጠራን ነን። እንደ ማርያም ሁሉንም ለማገልገል፣ ሁሉን በመደገፍና በማገልገል አብረን እንጓዝ…። በማለት ያስደመጡት ስብከት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.